2016-06-15 16:16:00

ዓንቀጸ እምነት፥ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ሥርዓት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሠረታዊ ጥምረት አላቸው


የዓንቀጽአ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሉድዊግ ሙዩለርና ዋና ጸሓፊያቸው ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊስ ላዳሪኣ ፊርማ የተኖረበት ሰነድ እ.ኤ.አ. መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዚህ ቅዱስ ማኅበር ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ቅዱስነታቸው የሰጡት ምዕዳን መሠረት በማድረግ Iuvenescit Ecclesia -  የቤተ ክርስቲያን ኅልውናዊ ተኃድሶ በሚል ርእስ ሥር በቤተ ክርስቲያን የሥርዓተ ሥልጣን ጸጋና መንፈሳዊ ተሰጥኦዎች መካከል ያለው ግኑኝነት እርሱም ሁለቱ ጸጋዎች መሠረታዊ ጣምራነት እንዳላቸው የሚተነን ሃሳብ መርህ ያደረገ ሰነድ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ጰራቅሊጦስ ባከበረችበት ቀን የተደረሰው ሰነድ እ.ኤ.አ. ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ በቅቷል።

 

ይኽ ለመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት በቀጥታ ይድረስ የሚል ሰነድ ትኵረት ያደረገበት ቅዉም ሃሳብ እላይ እንደተገለጸው ለቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በቤተ ክርስቲያን የሥርዓተ ሥልጣን ጸጋና በመንፈሳዊ ጸጋዎች መካከል ያለው ግኑኝነት መሠረታዊ ነው የሚል ሲሆን፡ የሰነዱ ጽማሬም፥

የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ሥርዓተ ጸጋና በመንፈሳውያን ስጦታዎች መካከል ያለው መሥረታዊ ቁርኝቱ በቅድሚያ ከሚሰጡት ሚሥጢረ ማዕርግ ማለትም ጵጵስና ክህነትና ድቁና ላይ የጸና ሲሆን፡ በሁለተኛ ደረጃም መንፈስ ቅዱስ በሚጸግዋቸው ስጦታዎች ላይ የጸና መሆኑ Iuvenescit Ecclesia -  የቤተ ክርስቲያን ኅልውዊና ተኃድሶ  በሚል ርእስ ሥር በተደረሰው ሰነድ ሲገለጥ፥ “ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ኃይል አማካኝነት ኅልውናዊ ታዳሽ ያላት ነች” በተለያዩ ሥርዓተ ሥልጣንና መንፈሳዊ ውህበት አማካኝንት በመንፈስ ቅዱስ ትመራለች ትታደሳለች ትታነጻለችም ይላል።

ውሁዳዊ ግኑኝነትና ተሟይነት ለመጋብያን (ለእረኞች) በመታዘዝ

ሰነዱ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና ተግባራዊነት ጥያቄዎች ላይ ሳይሆን ቲዮሎጊያዊ ጥያቄዎች ላይ በማተኮር በቤተ ክርስቲያን መዋቅሮችና በአዳዲስ እንቅስቃሴዎች (በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ) ቤተ ክርስቲያንዊ ስብስብነት መካከል ካለው ውሁዳዊና ተሟይ የሆነው ግኑኝነት ምን ተመስሎው በማብራራት ግኑኝነቱም የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች ፍርያማና ሥርዓት ያለው ሱታፌ ለቤተ ክርስቲያን ውህዳዊነት መሆን ይጠበቅበታል፡ ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ግኑኝነት እነዚያ እንቅስቃሴዎችና ስብስቦች ለቤተ ክርስቲያናዊ ሥልጣን ከመታዘዝ ኃላፊነት ገዛ እራሳቸውን ሊያገሉና፡ ሥልጣንም ሆነ ለእነርሱ ልዩ የእራስ አገዛዝ ነጻነትም ጭምር የሚያሰጣቸው አይደለም፡ እነዚህ ጸጋዎች ለቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ተልእኮ የማይታበሉ እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡ ስለዚህ እውነተኛ መንፈሳውያን ጸጋዎች ክፍት ወደ ሆነው ተልእኮ ለመጋብያን (ለእረኞች) መታዘዝ ወደ የቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚመሩ ናቸው።

ቤተ ክርስትያን ሕጋዊ ሥርዓተ ቅዋሜና የግብረ ሠናይ ቤተ ክርስቲያን መካከል ተጻራሪነት የለም

ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ሥልጣን ከሆነው ጸጋና እንቅስቃሴዎችና ስብስቦች በመካከላቸው ተጻጻሪነትና ጎን ለጎን የመቀመጥ አዝማሚያ ያላቸው አድርጎ መግለጥና ማስቀመጡ አቢይ ስህተት ነው፡ ስለዚህ ቅውምተ ቤተ ክርስቲያንና የግብረ ሠናይቱ ቤተ ክርስቲያን ብሎ ማነጻጸር አይገባም፡ ምክንያቱም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቤት ክርስቲያን ስልጣናዊ ቅዋሜዎች ለገዛ እርሳቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ናቸውና። መንፈሳውያን ሥጦታዎች ትውስብነትና ቀጣይነት እንዲኖራቸውም ተቋዋማዊ ቅርጽ ሊኖራቸው ይገባል። በዚህ መልኩም ሁለቱ ስፍርቶች የክርስቶስ የማዳን እቅድና ሚሥጥር በዓለም ኅልው ለማድረግ አብረው የሚጓዙ ናቸው።

የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሥፍረትና ቤተ ክርስቲያናዊ ብስለት

አዳዲስ ክውኖች (እንቅስቃሴዎችና ቤተ ክርስቲያናዊ ስብስቦች) ምሉእ ክብርና ተቀባይነትም እንዲኖራቸውና ዘወትር ከመጋብያን (እረኞች) ጋር ውህደት ያላቸውና መጋብያኑ (እረኞች) ለሚሰጡት መመሪያ ጥንቁቆች በመሆን በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ግባት እንዲኖራቸው ወደ ቤተ ክርስቲያናዊ ብስለት ማዘገም ይገባቸዋል። ስለዚህ የአዳዲሶች ክውኖች እውን መሆን በርግጥ የቤተ ክርስቲያን ልብ በኃሴትና በምስጋና የሚሞላ ነው። ይኽ ደግሞ በቸርነት መንፈስ ተነቃቅተው በመጋብያን (እረኞች) አባታዊ ጥንቁቅነ ተሸኝተው ለቤተ ክርስቲያንና ለወንጌላዊ ልኡክነት እርባና ሲባል ከሌሎች በቤተ ክርስቲያን ህይወት ህልው ከሆኑት ጸጋዎች ጋር ግኑኝነት እንዲኖራቸው ያሳስባቸዋ። የመንፈሳዊ ተሰጥኦ ስፍረት ከቤተ ክርስቲያን ሕይወትናተ ተልእኮ በጭራሽ ሊገለሉ አይገባቸውም የሚል ነው።

እውነተኛ መንፈሳዊ ተሰጥኦ የሚለዩ መስፈርቶች

አንድ እውነተኛ መንፈሳዊ ተሰጥኦ እንዴት መለየትና ማወቅ ይቻላል? ይኽ ገምግሞ የመለየቱ ኃላፊነት የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ነው። መሥፈርቶቹም በቤተ ክርስቲያን የቅድስና መሳሪያ በመሆን ወንጌል በማስፋፋት በመጠመድ በሙላት የካቶሊክ አንቀጸ እምነት ቃለ ኑዛዜ የሚያደርጉ ከመላይቱ ቤተ ክርስቲያን በሥርወ እምነት ዙሪያ የምትሰጠው ትምህርትና የመጋብያን ትምህርትም በመቀበል ሌሎችን የቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተነቃቅተው ለተመሰረቱት ማኅበራት እውቅና በመስጠትና በማክበር የፈተና ወቅት በማስተዋል በትህትና በመቀበል ፍቅር ኃሴት ሰላም ትህትን የተሰኙት መንፈሳውያን ፍሬዎች ያስፍሆተ ወንጌል ማኅበራዊ ስፍረቱን መመልከት፡ እጅግ ለተናቁት የኅብረተሰብ አባላት ምሉእ እድገት ማሰብ የሚለው የእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ተጨባጭነት የሚያስተውል ንቁና ስኬታማ የሆነ  ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚኖሩት ሱታፌ መስካሪያን መሆን የተሰኙ ናቸው።

እንደ ሕገ ቀኖና መሠረትም ሕጋቂ እውቅና ማግኘት

ሰነዱ አክሎም እንደ መስፈርት፥ ለሚቋቋሙት እንቅስቃሴዎችና የቤተ ክርስቲያን ስብስቦች  የቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና በሚያዘው መሠረት ሕጋዊ እውቅና ለመስጠት፡ በቅድሚያ የእያንዳንዱ ማኅበርና ቤተ ክርስቲያናዊ ስብስቦች የተቀበሉት መለያቸው የሆነው የመንፈሳዊ ጸጋዎቻቸውን ማክበር፡ እንዲህ ባለ መንገድም አዳዲስ ክውኖችን የሚጎዳ ሕጎችን እንደሚበጅህ የማሽከርከሩ ጉዳይ እንዳይከሰት ለማድረግ ያግዛል። ሁለተኛው መመዘኛውም ደግሞ የአዳዲስ እንቅስቃሴዎችና ቤተ ክርስትያናዊ ስብስቦች በመንፈሳዊ ተሰጥኦዋችው ንቁ በሆነ ሁኔታ  የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን እንደ ተመሳሳይ ተጨባጭ ሁነት ማስተዋል የሚለውን የቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ሥልጣን ጸጋ ዋቢ ያለ ማድረግ አዝማሚያ እንዳያሳዩ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሥልጣን ያላቸው ሆነው እንዳይታሰቡና እንዳይኖሩም በቤተ ክርስቲያን ገብ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያመቻችውን ለቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ጸጋ መሠረታዊ ክብር መስጠት ይገባቸውል የሚል ነው።

በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና በክልላዊቱ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነ አልቀሬ ነው

በቤተ ክርስቲያን ጸጋ በሆነው ሥልጣናዊ ስርዓትና በመንፍሳዊ ተሰጥኦ አማካኝነት የሚጸኑት እንቅስቃሴዎችና ቤተ ክርስቲያናዊ ስብስቦች መካከል ያለው ግኑኝነት ያ አይቀሬ የሆነው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና በክልላውያን ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነት ግምት የሚሰጥ መሆን ይጠበቅበታሆል። ይኽ ሲባል ደግሞ መንፈሳውያን ጸጋዎች የሚሰጡ መሆናቸው በማረጋገጥ ነው፡ ስለዚህ የሚሰጡትም ለመላይቱ ቤተ ክርስቲያን ነው። ቢሆንም ባላቸው ታታሪነት በአንድ ተጨባጭ ሰበካ በሚሰጡት አገልግሎት የሚከወኑ ናቸው፡ በዚህ ብቻ ሳይታጠርም አእያንዳንዱ ክርስቲያናዊ ወይንም ክህነታዊ ገዳማዊ ወይንም ለድቁናና ሌሎች በቤተ ክርስቲያን የሚኖሩ ጥሪዎች ለመኖርና ለማሳደግ የሚደግፉ የእውነተኛ አማራጭ መገዶች ናቸው። በተጨማሪም ውፉይ ሕይወት በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ተሰጥኦ ስፍረት ዘንድ ቅዉም እንደሚሆን ያረጋግጥልናል። ምክንያቱም ያለው መንፈሳዊው ተሰጥኦው ዓለማዊው ምእመንም ይሁን ውሉደ ክህነት ሁለቱም የሚለያቸውን የየራሳቸው ጥሪ እንዲኖሩ ለመደገፍ በቤተ ክርስቲያን ስፍረት ዘንድ የሚቋቋሙ በመሆናቸው ነው።

በማርያም አብነት ላይ ማተኮር

ሰነዱ፥ የቤተ ክርስቲያን እናት የሆነቸው ለመንፈስ ቅዱስ በሙላት ታዛዣ የመሆንና ጥርት ላለ ትህትና አርአያ የሆነቸውን ማርያም መመልከት ያለው አስፈላጊነት በማብራራት፡ ሁሉም በምእመናን አትረፍርፎ መንፈስ ቅዱስ ለሚሰጠው መንፈሳዊ ጸጋ  በተአዝዞ እንዲያስተነገዱና ለቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ተልእኮና ለመላ ዓለም መልካምነት እንዲውል እርሷን በሚማለድ ሃሳብ ይጠቃለላል።








All the contents on this site are copyrighted ©.