2016-06-10 15:26:00

ፈረንሳይ፥ ብፁዓን ጳጳሳት የመምኅርነትና የማስተማር ዜዴ ነጻነት ጥሰት ጸረ የሰብአዊ መብትና ክብር ነው


እ.ኤ.አ. ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. የፈረንሳይ የትምህርት ጉዳይ ሚኒስትር ቢሮ የአገሪቱ የምምኅርነትና የማስተማር ዘዴ አዳሽ የሕግ ንድፍ በማለት መግለጫ የሰጡበት የትምኅርት ህዳሴ እቅድ ከሚጠቅሳቸው አንዱ የመንግሥት ትምህርት ያልሆኑት አቢያተ ትምህርት ቅዋሜ ዙሪያ የሚገለጠው ሃሳብ አሳሳቢ መሆኑ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በትምህርት ጉዳይ ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር የብሮድዋክስ ሊቀ ጳጳስት ብፁዕ ካርዲናል ዣን ፒየር ሪካርድ አማካኝነት በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሊዛ ዘጋሪኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

አክራሪነትና ጸንፈኛነት የማስተማር ዜዴ ነጻነት በመወሰን መዋጋት አይቻልም

የፈረንሳይ የትምህት ጉዳይ ሚኒ. አዲሱ የመምኅርነትና የማስተማር ዘዴ ኅዳሴ በማለት ያቀረበው ሃሳብ ምክንያታዊ ከሚያደርገው አንዱ እክራሪነትና ጸንፈኛነትን ለመዋጋት ነው በማለት የገለጠው ሃሳብ ብፁዕ ካርዲናል ዣን ፒየር ሪካድ መሠረት የሌለው ነው በማለት ጸንፈኝነትና አክራሪነት የግል ትምህርት ቤቶች ቅወሜ በመወሰን መዋጋት አክራሪነትና ጽንፈኝነት ማባባስ ነው የሚሆነው እንጂ እንዲወገድ አያደርግም ብለው አዲሱን የትምህርት ኅዳሴ ሕገ ንድፍ ተቃውመው፡ መሠረታዊ ያደርገዋል ተብሎ የሚገለጠ ምክንያት አመክንዮ አልቦ ነው እንዳሉ የጠቆሙት የቫቲካ ረዲዮ ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ አያይዘው፥ ብፁዕነታቸው የሚበጀው የትምህርትና ትምህርት ቤቶች የሚመለከተው የነበረው ሕግ ሙሉ በሙሉ ገቢራዊ ማድረግና ደካማውን ጎኑን ማስተካከልና ማሳየል እንጂ ኅዳሴ ብሎ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ከሆኑት ውስጥ አንዱ እርሱም የማስተማር ዘዴ ነጻነትና የትምህርት ዘዴ ነጻነት መወሰን መፍትሔ ሊሆን አይችልም እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.