2016-06-07 13:20:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ስታኒሳልውስን እና ሜሪ ኤሊሳቤጥን ቅድስናቸውን ማወጃቸው ታወቀ።


በግንቦት 28/2008 በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የሚሰጠውን ሳምንታዊ የጠቅላል አስተምህሮ ለመከታተል መገኘታቸው የታወቅ ሲሆን በእለቱም ቅዱስነታቸው ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ቡኋላ የፖላንድ ተወላጅ የነበረውን እና የኢየሱስ ማሪያም ማህበር አባል የነበረውን ስታኒሳልውስን እና ሜሪ ኤሊሳቤጥን  “ቅዱስ” ብለው ማወጃቸው እና ወደ ቤተክርስቲያን የተቀላቀሉ አዳዲስ ቅዱስን መሆናቸውን ማብሰራቸው ታወቀ።  

ቅዱስ ስታኒሳልውስ የተወለደው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር 1931 በፖላንድ ሲሆን በጊዜው በነበረው ፒያሪስት በተባለው ማህበር አባል በመሆን ማህረገ ክህነትን መቀበሉ የተወቀ ሲሆን ከቆይታዎች ቡኋላ ያላዳም ኋጥያት የተጸነሰች ማሪያም የተባለ ማህበር ማቋቋሙምን ለማወቅ ተችሉዋል።

በመቀጠልም የሲውዲን ተወላጅ የነበረችሁ እና የቅድስት ብርጅትን ማህበር በድጋሚ የመሰረተችሁ በተጨማሪም የስዊድን ሀገር ጠባቂ ቅድስት የሆነችው ቅድስት ሜሪ ኤሊዛቤት ኤሴልብላድ ቅድስና በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የታወጀ ሲሆን በእለቱ ከአርባ ሺ በላይ ለሚሆኑ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎኚዎች ቅዱስነታቸው ባሰሙት ስብከት እነዚህ ሁለት አዳዲስ ቅዱሳን የክርስትና እምነትን ሕይወታቸው ባሳዩት ግሩም ምሳሌ በማሳየታቸው እና በመከራዎቻቸው ወቅት ሁሉ ያሳዩትን ታታሪነት ማድነቃቸውም ተወስቱዋል።

“በክርስቶስ መከራ አማካይነት ተስፋ በምያስቆርጥ መከራ ውስጥ ሆነን ለምናለቅሰው ለቅሶ እና ወደ ሞት ከሚያመራን መከራ ለመላቀቅ ለምናድርገው ጥሪ እግዚአብሔር መልስ ይሰጠናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ማናችንም ብንሆን ከመስቀል ማምለጥ አንችልም፣ ነገር ግን በመስቀሉ ሥር ተግተን እንደ እናታችን ማሪያም መቆም ይጠበቅብናል” ብለው “ከኢየሱስ ጋር በመሰቃየቷ ከሁሉም በላይ ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋን የማድረግ ፀጋ አገኘች ይህም ደግሞ በቅዱስ ስታኒሳልውስ እና በቅድስትር ማሪያ ኤልዛበት ሕይወት ውስጥ የተንጸባረቀ እውነት ነበር” ማለታቸውም ታውቁዋል።

“በመከራቸው ወቅት ሁሉ ከኢየሱስ መከራ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነትን ፈጥረው ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ምክንያት የኢየሱስ ትንሳኤ በእነርሱ መገለጹን” አውስተው የቀኑን ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.