2016-05-31 14:21:00

ቅዱስነታቸው "ቤተ ክርስቲያን ትንቢት የመናገር ነፃነት አላት፣ በሕግ ብቻ መመራት የሕግ ባሪያ ያደርጋል" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 22/2008 ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን በክርስትና ሕይወት ውስጥ ስለሚገኙ ሦስት ዋና ዋና ገጽታዎች ላይ ያጠነጠነ ሲሆን እነዚህም ሦስት የክርስቲያን ሕይወት ገጽታዎች ማሳታወስ፣ የነቢይነት መንፈስ እና እርግጠኛ ተስፋ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው የስብከታቸው ማዕከል አድርገው የወሰዱት በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል (12,1-12) የተነበበው እና ኢየሱስ በጊዜው ለነበሩት ካህናት፣ ለሕግ መምህራን እና ለፈሪሳዊያን፣ የወይን ስፍራ የተከራዩ ገበሬዎች ምሳሌ ላይ አጠንጥኖ የነበረ ሲሆን የወይን እርሻ ባለቤት ወይን አስተክሎ እና እርሻውን አደራጅቶ ካበቃ ቡኋላ እንዲከባከቡለት በማሰብ ለገበሬዋች አከራይቶ የነበረ ሲሆን የምርት መሰብሰብያ ወይም የመኅር ወቅት በደረሰ ጊዜ የድርሻውን ይልኩለት ዘንድ አገልጋዮቹን በላከበት ወቅት ተከራይ ገበሬዎቹ ለማመጽ በማሰብ የተላኩ አገልጋዮችን ሰድበው፣ ደብድበው እና አገልጋዮችን ገድለው በመጨረሻም የወይን እርሻውን እንወርሳለን በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ላይ ተመስርተው አንድኛ ልጁን እንደ ገደሉት አውስተዋል።

የወይን እርሻው ባለቤት አገልጋዮች እና አንደኛ ልጁ መግደላቸው  ይህ ምሳሌ በመጻሐፍ ቅዱስ አገላለጽ  የሚያወሳው ስለ ነቢያት እና ስለ ክርስቶስ እራሱ መሆኑን ገልጸው እራሳቸውን በእራሳቸው ዝግ ያደረጉ ሰዎችን፣ ለእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል እራሳቸውን ያልከፈቱ ሰዎችን፣ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል እስኪፈጸ ድረስ በተስፋ የማይጠባበቁ ሰዎችን፣ ዝንጉ የሆኑ ሰዎችን፣ በአጠቃላይ ያለ ትንቢት  እና ያለ ተስፋ የሚኖሩ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸው የሕዝብ መሪዎች የሆኑ ሰዎች በተለየ ሁኔታ የሕግ ቅጥር ግንብ በመገንባት ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ እራሳቸውን “ዝግ በሆነ የሕግ መዋቅር” ውስጥ እንደ ምያስገቡ አስረድተዋል።

 “ማህደረ ትውስታ ለእነርሱ ምንም አሳሳቢ ነገር አይደለም፣ ስለ ነቢያት---ነቢያት ባይላኩ ይመርጣሉ። የሕግ ሰዎች እና የነገረ መለኮት ምሁራን ብዙን ጊዜ የተምታታ መንገድ ላይ ይሄዳሉ መንፈስ ቅዱስ በነጻነት ሥራውን ያከናውን ዘንድ አይፈቅዱም፣ ለእግዚአብሔር ስጦታ እውቅናን አይሰጡም፣ መንፈስን ይገድባሉ ምክንያቱም የተስፋ ትንቢትን ስለማይፈቅዱ ነው ብለው እነዚህን መዋቅሮች በመጠቀምም ተግባራቸውን ሕጋዊ እንዲሆን ያደርጋሉ፣ የመጀመሪያው ምንባብ እንደ ምያወሳው ሙስና፣ ዓለማዊነት እና ምኞት. . . ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመሪያ ምንባብ ለእደነዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ መዋቅር ነው ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ጠለቅ ብለው በመግባት “ኢየሱስ እራሱ ለትንቢት መንገድ ላለመስጠት እና ተስፋ ከማድረግ ይልቅ ለእርሱ ደህንነት እንዲጨነቅ በሚያደርግ የእራሱን የተልዕኮ ምንጭ እንድያጣ ተፈትኖ ነበር” ይህም ማለት በረሃ በነበረበት ወቅት ያጋጠሙትን ሦስት ፈተናዎችን ያስታውሰናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም “ኢየሱስ መፈተን ምን ማለት መሆኑን እራሱ ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበር እነዚህን ሰዎች የቀረባቸው ‘ወደ ዓለም በደንብ ዘልቆ በመግባት ወደ አይሁድነት የምለወጥ አዲስ ገቢ ሰው ይፈልጋሉ ስያገኙትም ባሪያቸው ያደርጉታል’። በዚህ መንገድ የተደራጄ ሕዝብ፣ በዚህ መንገድ የተደራጄች ቤተ ክርስቲያን ባሪያ ያደርጋል። ከዚህ በመነሳት ቅዱስ ጳውሎስ የሕግ ባርነት እና ነፃነት የሚሰጠውን ፀጋ፣ ተስፋ የማይቆርጥ እና ለነቢያት ቦታ የሚሰጥ ነፃ ሕዝብ፣ ነፃ ቤተ ክርስቲያን ያደርጋል ያለውን ቃል መገንዘብ ይቻላል”ብለዋል።

 ቅዱስነታቸው አጥብቀው እንደ ገለጹት በጥሩ ሁኔታ የተደራጀው የወይን እርሻ ቦታ አብ “በከፍተኛ ፍቅር እና ርኅራኄ” ጥንቃቄ የምያደርግለት “የእግዚአብሔርን ሕዝብ፣ የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በነፍሳችን ልመስል ይችላል”  ካሉ ቡኋላ በእርሱ ላይ ማመጽ ማለት ልክ የወይኑን እርሻ እንደ ተከራዩ ገበሬዎች ከእግዚአብሔር የተሰጠን “ስጦታን መዘንጋት ማለት ነው” ካሉ ቡኋላ “ለማስታወስ እና ስህተት ላለመፈጸም ወደ ሥር መሰረታችን መመለስ” በጣም አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።

“እግዚአብሔር በሕይወቴ የፈጸመውን ድንቅ ነገር አሁንም አስታውሳለው? የእግዚአብሔርን ስጦታ ማስታወስ እችላለሁ? ይህ ነገር አይሆንም፣ ከእዚህ የበለጠ መሄድ ይኖርብኋል፣ አትስጋ ወደ ፊት ሂድ? ለሚለኝ ጌታ ልቤን፣ ለነቢያት ማለትም ለእርሱ ለመክፈት ይቻላል ወይ? በመጨረሻም ወዴት እንደ ሚሄድ እንኳን ሳያውቅ በእግዚኣብሔር ላይ ብቻ ተስፋውን በማድርግ ቤት ንብረቱን ትቶ እንደ ሄደው አብርሃም አባታችን  እግዚአብሔር በሰጠኝ የተስፋ ቃል እታመናለሁ? እነዚህን ጥያቄዎች እራሳችንን መጠየቅ ተገቢ ነው” ብለው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.