2016-05-30 16:11:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በሩሲያ አዲስ የቅድስት መንበር ልኡክ ሰየሙ


በኢጣሊያ ፒዮሞንተ ክፍለ ሀገር በምትገኘው የኩነዮ ከተማ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 1 ቀን 1952 ዓ.ም. የተወለዱ እ.ኤ.አ. በ 1977 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት የተቀበሉት በጳጳሳዊ የሥነ ቤተ ክርስቲያን ተቋም በቅድስት መንበር የሥነ ዲፕሎማሲያዊ የጥናት ዘርፍ ሊቅነት ያስመሰከሩት እ.ኤ.አ. በ 1980 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የውጭ ጉንኘቶች ጉዳይ ተመድበው በአንጎላ በግብጽ ከዛም በፖላንድ በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ቢሮ አባል በመሆን ያገለገሉ በ 1992 ዓ.ም. በኤውሮጳ አገሮች ኅብረት ምክር ቤት የቅድስት መንበር ልኡክ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው በ 1995 ዓ.ም. እስከ 2002 ዓ.ም. የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሓፊ ከዛም በ 2002 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ እንዲሆኑ በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተሰየሙት እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. ማዕርገ ጵጵስና የተቀበሉ ከ 2010 ዓ.ም. በፖላንድ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚሊዮረ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሞስኮ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሆነው እንዲያገለግሉ መሰየማቸው  የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.