2016-05-30 16:08:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. የሲንጋፑር ርእሰ ብሔር ተቀብለው አነጋገሩ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ለይፋዊ ጉብኝት ሃገረ ቫቲካን የገቡት የረፓብሊካዊት ሲንጋፑር ርእሰ ብሔ ቶንይ ታን ከግ ያምን በሐዋርያዊ መንበራቸው ተቀለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ። በተካሄደው ክሌኣዊ ግኑኝነትም በአገረ ቫቲካንና በሲንጋፑር መካከል ያለው ግኑኝነት የተወዋጣለት ከመሆኑም ባሻገር በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በሲንጋፑር መንግሥት መካከል ያለው ግኑኝነት የሚመሰገንና ቤተ ክርስቲያን በማኅበራዊ ዘርፍ የምትሰጠው አገልግሎት በመንግሥትና በአገሪቱ ሕዝብ የሚመሰገን መሆኑ ርእሰ ብሔር ከግ ያም ማረጋገጣቸንው ጠቅሶ፥ በደቡባዊ እስያ የሰብአዊ መብትና ክብር እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ያለው የጋራው ግኑኝነት ርእስ ዙሪያ ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥ ቅድስት መንበር እነዚህ እሴቶች በማነቃቃትና በተለያዩ ባህሎች መካከል የጋራው ውይይት ለአገሮች መረጋጋት ለፍትህና ሰላም መሠረት መሆኑ ታምና በዚሁ ዘርፍ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አገልግሎት የተከናወነው ክሌአዊ ግኑኝነት አውቅና እንደሰጠበትም አስታወቀ።

የሲንጋፑር ርእሰ ብሔርም ከቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ተሰናብተው በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ፓውል ሪቻርድ ጋላገር ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር  መገናኘታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.