2016-05-30 17:00:00

ሢመተ ጵጵስና


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጧት የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለንና የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ ጽ/ቤት ኅየንት ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ ፐልን ተቀብለው እንዳነጋገሩ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚምባብወ የሙታራ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አለክሲዮ ቹሩ ሙቻባኢዋ በእድሜ መግፋት ምክንያት ያቀረቡት የልኂቅነ ጥያቄ በመቀበል በምትካቸው የቀርመለሳውያን ገዳማውያን ማኅበር አባል የአየር ላንድ ተወላጅ በዚምባብዌ በሙታራ ሰበካ ሐዋርያዊ መሥተዳድር ሥር ለሚገኝው በሩሳፐ ክልል የሚገኘው የክሪስተ ሞምቦ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤት ዋና አሥተዳዳሪ አባ ፓውል ሆራንን መሰየማቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ኣባ ሆራን በአየር ላንድ እ.ኤ.አ.  ጥቅምት 17 ቀን 1962 ዓ.ም.  በድራንጋን ከተማ መወለዳቸው ገልጦ፥ ከ 1990 እስከ 1995 ዓም. በዱብሊን በሚገኘው ሚልታውን ተቋም የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው በ1995 ዓ.ም. የመጨረሻ ማኅላ ፈጽመው ሰኔ 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት የተቀበሉ መሆናቸውም ጠቅሶ፥ ወደ ቀርመለሳውያን ገዳም ማኅበር ከመግባታቸው በፊት በአየር ላንድ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተለያየ ተልእኮ ከዛም በ 2001 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዋሽንግተን በሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጥበብ በቲዮሎጊያ ሥነ መንፈሳዊነት ሊቅነት አስመስክረው  በዚያኑ ዓመት ወደ ዚምባብወ ተልክው ከ 2001 እስከ 2004 ዓ.ም. በሩሳፐ የቀርመለሳውያን ተማሪዎች አለቃ ከ 2006 እስከ 2008 ዓ.ም. የቀርመለሳውያን ተመካርያን አለቃ በሩሳፐ በማኮኒ ቅዱስ ኪሊኣን ቁምስና ረዳት ቆሞስ በ2008 ዓ.ም. በሩሳፐ የክሪስተ ሞምቦ ካቶሊክ ትምህርት ቤት ዋና አስተዳዳሪ በመሆን እንዳገለገሉም ከገለጠ በኋላ አያይዞም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የፊሊፒንስ የባቮምቦንግ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ራሞን ቪለና በዕድሜ መግፋት ምክንያት ያቀረቡት የሊኅቅነት ጥያቄ መቀበላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.