2016-05-27 15:10:00

የብፁዕ ካርዲናል ካፖቪላ ዕረፍት


የቅዱስ ዮሓንስ 23ኛ ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት በኢጣሊያ በርጋሞ ከተማ በሚገኘው ክሊኒካ ዲ ፓላዞ በሕክምና ሲረዱ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ሎሪስ ፍራንቸስኮ ካፖቪላ በ 100 ዓመት እድሜያቸው እ.ኤ.አ. ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቁሞ፥ በሳቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያትም በአሁኑ ሰዓት የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ አባላት በሕገ ቀኖና መሠረት 114 የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የመምረጥ መብት ያላቸውና እንዲሁም ሌሎች 99 ደግሞ በእድሜ መግፋት ምክንያት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የመምረጥ መብት የሌላቸው በጠቅላላ 213 ብፁዓን ካርዲናሎች የሚያቅፍ መሆኑ ያመለክታል።

ብፁዕ ካርዲናል ሎሪስ ፍራንቸስኮ ካፖቪላ በኢጣሊያ ፓዶቭ ክፍለ ሃገር በምትገኘው ፖንተሎንጎ ከተማ  እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 1915 ዓ.ም. የተወለዱ በዚያች ከተማ በሚገኘው በቅዱስ አንድሪያስ ቤተ ክርስቲያን ህዳር 7 ቀን 1915 ዓ.ም. ጸጋ ጥምቀት የተቀበሉ የሎረተ ልዩ ጳጳስን የላውረታኖ ቅዱስ ሥፍራ የቅዱስ ጴጥሮስ ወኪል የነበሩ መሆናቸው ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ፥ በቨነዚያ ሰበካ ፓትሪያርክ ዘርአ ክህነት ተማሪ በመሆን ለክህነት የሚያበቃቸው መንፈሳዊ ሰብአዊና ፍልስፍናዊ ቲዮሎጊያ ሕንጸት አጠናቀው እ.ኤ.አ. ግንቦት 23 ቀን 1940ዓ.ም. ማዕርገ ክህንት ተቀብለው በቅዱስ ዘካሪያስ ቁምስናና በሰበካው መንበረ ፓትሪያርክ ውጥ በተለያዩ ሐዋርያዊ ኃላፊነቶች ተመድበው ያገለገሉ በቨነዚያ ለሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የሊጡርጊያና በዓላት ጉዳይ ኃላፊነት፡ በሁለተኛና በከፍተኛ ትምህርት ቤት የትምህርተ ክርስቶስ መምህር የወዛደሮች መንፈሳዊ ተንከባካቢ በፖርቶ ማርገራ ለሚገኘው ወህኒ ቤት፡  የሕጻናት የማረሚያ ቤትና እንዲሁም የተላላፊ በሽታ ማከሚያ ቤት ቆሞስ በመሆን እንዳገለገሉ ይጠቁማል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በብሔራው ውትድርና ጥሪ መሠረትም የአየር ኃይል አባል ከዛም ከጦርነት ፍጻሜ በኋላም በብፁዕ ካርዲናል ፒያዛ እ.ኤ.አ. በ1 945 ዓ.ም. በቨነዚያ የራዲዮ ስርጭት በየእሁዱ  ለሚተላለፈው ስብከት አቅራቢ ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጠው በዚህ አገልግሎትም እስከ 1953 ዓ.ም. የቆዩ የቅዱስ ማርቆስ ድምጽ ተለተሰኘው የቨነዚያ ፓትሪያርክ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና አቨኒረ ለተሰየመው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ለቨነዚ ክልል ልኡክ አቀነባበሪ በመሆን ያገለገሉና ከ 1950 ዓ.ም. በኢጣሊያ የጋዜጠኞች ማኅበር አባል ለመሆን የበቁ  ከ 1953 እስከ 1958 ዓ.ም. ለቨነዚያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ጁዜፐ ሮንካሊ ልዩ ጸሓፊ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ የቨነዚያው ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ጁዜፐ ሮንካሊ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 28 ቀን 1958 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙ በኋላ በር.ሊ.ጳ. ፍላጎት ወደ ቫቲካን ተዛውረው ለእኚህ ዮሓንስ 23ኛ የሚል የር.ሊ.ጳ. መጠሪያ ስም ለመረጡት ር.ሊ.ጳ. ሮናክሊ ዋና ጸሓፊ በመሆን ሲያገልግሉ ቆይተው ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ እ.ኤ.አ. ሰነ 3 ቀን 1967 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ በአዲሱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በተሾሙት ጳውሎስ ስድስተኛ አማካኝነትም የኪየቲ ቫስቶ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የጵጵስና ማእርግ ከጳውሎስ ስድተኛ እጅ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 1967 ዓ.ም. ተቀብለዋል።

እ.ኤ.አ. መስከርም 25 ቀን 1971 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ ውሳኔ መሠረትም የሎረቶ ልዩ ጳጳስና በላውረታኖ ቅዱስ ሥፍራ የር.ሊ.ጳ. ወኪል በመሆን እንዳገለገሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ ከ 1988 ዓ.ም. በኋላ ቅዱስ ዮሓንስ 23ኛ ትውልድ ሶቶ ሞንተ ከተማ በመሄድ እዛው ስለ ቅዱስ ዮሓንስ 23ኛ ሰብአዊነት መንፍሳዊነት ታሪክ የሚያወሱ መጽሐፍቶች ለንባብ ያበቁ መሆናቸም ገልጦ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. አዳዲስ ካርዲናሎች እንዲሾሙ ከመረጡዋችው ውስጥ አንዱ ሲሆኑ በእድሜ መግፋት ምክያትም እ.ኤ.አ. መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ቅዱስ አባታችን ለመረጧቸው ሊቃነ ጳጳሳት የካርዲናል ማዕርግ ለመስጠት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመሳተፍ ባለመቻላቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቡፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ እጅ የካርዲናልነት ማዕርግ እንዲቀበሉ በማድረግም በሮማ የቅድስተ ማሪያም በትራስተቨረ ቤተ ክርስቲያን ስዩም ጳጳስ ተብለው መሾማቸው በምስታወስ ይገልጣል።








All the contents on this site are copyrighted ©.