2016-05-25 09:22:00

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፥ የማርያም ዘፋጢማ መልእክት


አንዳንድ ዕለታዊ ጋዚጦች ፕሮፈሰር ኢንጎ ዶሊንገር እንዳሉት በማለት ቅዱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. በፋጢማ ማርያማዊ ግልጸት እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 1917 ዓ.ም. የታደሉት ሦስት እረኞች እነርሱም ሉቺያ ዶ ሳንቶስ 10 ዓመት ዕድሜ የነበራት 9 ዓመት ዕድሜ የነበረው ፍራንቸስኮ ማርቶና ጃቺንታ ማርቶ 7 ዓመት ዕድሜ የነበራት ከማርያም የተቀበሉት በእነርሱ አማካኝነት ለቤተ ክርስቲያን የተላለፈው ሦስት ግልጸታዊ መልእክት ጉዳይ በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስነታቸው አማካኝነት ገሃድ ያደረገችው ሆኖ እያለ ነገር ግን ገሃድ የሆነው መልክት ምሉእ አይደለም በተለይ ደግሞ ሦስተኛው ሚሥጥር በሙሉ ታትሞ ለንባብ አልበቃም በማለት የሰጡበት ሃተታ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር የዜና ኅትመ ክፍል በኩል የማስተባበያ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት መእልእክት ጋዜጦች ዶሊንገር እንዳሉት በማለት የሰጡት ዜና እውነታ የሌለውና ስለ የማርያም ግልጸት በፋጢማና የተላለፈው ምሥጢራዊ መልእክት በተመለከተ ከፕሮፈሰ ዶሊንገር ጋር እንዳልተወያዩበት በማብራራት ጋዜጦች ፕሮፈሰሩን ጠቅሰው ያሰራጩት ዜና መሰረት የሌለው ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅድስት ድንግል ማሪያም ዘፋጢማ ለቤተ ክርስቲያን በተገለጸችላቸው አማካኝነት የተሰጠው ምሥጢራዊ መልእክት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስነቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አማካኝነት በሙሉ ገሃድ እንዳደረገ ገልጦ ምሥጢሩ ተሰንዶ በሚገባ በሳቸው ፈቃድ አማካኝነት ለንባብ በቅቷል ስለዚህ ጋዜጦቹ የሰጡት ዜና ፈጠራ ነው ሲል በነዲክቶስ 16ኛን ጠቅሶ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.