Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ የአለም ዜናዎች

የቅድስት መንበር የልዑካን ቡድን በስታንቡል ሚካሄደውን የመጀመሪያው የዓለም ሰብዓዊ ጉባሄን ለመካፈል መላኩ ተገለጸ።

የመጀመሪያው የዓለም ሰብዓዊ ጉባሄ በስታንቡል ተካሄደ። - AFP

24/05/2016 11:42

አንድ ከፍተኛ የቅድስት መንበር የልዑካን ቡድን ከግንቦት 15 እስከ 16 በቱርክ ዋና ከተማ በስታንቡል ለሁለት ቀን ለሚካሄደውን የመጀመሪያው የዓለም ሰብዓዊ ጉባሄን ለመካፈል መላኩ ተገለጸ። ይህ ጉባሄ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ በሆኑት በባን ኪ-ሙን መሪነት እንደ ሚካሄድ የታወቀ ሲሆን  አሁን ዓለማችን እየተጋፈጠች የምትገኘው እና ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወዲህ የተከሰተ የከፍ ሊባል የሚችል እና በአሁኑ ጊዜም ዓለማችን እያሰተናገደች የምትገኘው ከፍተኛ ሰባዊ ቀውስ ላይ  ይህ ጉባሄ ትኩረቱን እንደ ሚያደርግ የታወቀ ሲሆን ጉዳዩ የሚመልከታቸው የመንግሥት አካላት፣ የሰብአዊ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች፣ በእዚህ ሰባዊ ቀውስ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች እና እንዲሁም ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ አዳዲስ አጋሮችም በጉባሄው ላይ እንደ ሚሳተፉ ተውቁዋል።

የእዚህ ጉባሄ ዋንኛው ዓላማ እንዲሆን የታቀደው ለሰው ልጆች ሁሉ ሰባዊ ጥበቃ እንዲደረግ፣ መብታቸው እንዲከበረ እና በተጨማሪም ለሰው ልጆች ሁሉ ብልጽግናን ይጎናጸፉ ዘንድ የተጠናከረ ሥራ ማድረግ ያስፈልጋል በሚል ሐሳብ ዙሪያ ጉባሄው እንደ ምያጠነጥን እና ዓለማቀፋዊ ውሳኔ ሰጭነትንና ታማኝነትን ለማጠናከርም እንደ ሚወያይም ለመገንዘብ ተችሉዋል።

በአሁን ወቅት በጦርነት ምክንያት ከሀገራቸው የተፈናቀሉ  ከ3.4 ሚልዮን በላይ የሶሪያ ስደተኞች በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደ ሚገኙ እና በእዚህ ዓመት መጨረሻም ቁጥራቸው ወደ 4.7 እንደ ሚያሻቅብ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን የእዚህ ጉባሄ ዋንኛው የመነጋገሪያ አርዕስት የሚሆነው ይህ የስደተኞች ቀውስ እንደ ሚሆን እና የሕግ አውጭ አካላትም ይህንን ቀውስ ከግምት በማስገባት እና በተለይም ከግማሽ በላይ የሚሆኑ እነዚህ ስደተኞች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውን፣ ትምህርት ቤቶቻቸውን በአጠቃላይ ቤት ንብረቶቻቸውን ያጡ እና ተስፋ የቆረጡ ታዳጊዎች እና ሕፃናት ስለሚገኙበት ከፍተኛ ትኩረት እንዲስጣቸው አጋጣሚውን ተጠቅመው እንደሚያሳስብ ለመረዳት ተችልዋል።

በመቀጠልም የጉባሄው አጀንዳ እንዲሆን የተመረጠው የአየር ንብረት ለውጥ፣ ወደ ከተሞች የሚደረገው የሰዎች ፍልሰት፣ የዓለም ሕዝብ ብዛት እና አሁን በዓለማችን ላይ ያለው አዲሱ የቴክኖሎጂ እድገት እንዴት ለብዙኋኑ ጥቅም መዋል ይችላል የሚሉ ሐሳቦች እንደ ሚነሱ እና ለአዳዲስ አስተሳሰቦች እና ምልከታዎች በር ሊከፍቱ የሚችሉ ጉዳዮችም በተጨማሪም በእዚህ ጉባሄ እንደ ሚዳሰሱ ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅድስ መንበር የእዚህን ጉባሄ አስፈላጊነትን በሚገባ በመረዳት  የቅድስት መንበር ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑትን ካርዲናል ፕትሮ ፓሮሊን፣ በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ በርናርድ ሁዛ እና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የቅድስት መንበርን በመወከል በጄኔቫ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ ታዛቢ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ቶማዚ ሲልቫኖን ያካተተ ሦስት ከፍተኛ የሉዑካን ቡድን እንደ ላከች ለማወቅ ተችሉዋል።

 

የሃይማኖት ድርጅቶች እና በእምነት ላይ መሠረታቸውን ያደረጉ ድርጅቶች ለሰላም የሚጫወቱት ሚና እና እሴት ሰባዊ እርዳታን ለማድረግ፣ ዘላቂ የሆነ ሰላምን ለማምጣት ከፍተኛ እንደሆነ በመረዳት ይህ እየተካሄዴ የሚገኘው ጉባሄ ለእዚህ ተግባር እውቅናን እንደ ሚሰጥ ይጠበቃል።

24/05/2016 11:42