2016-05-19 11:13:00

በመካሄድ ላይ ያለው 69ኛው የጣሊያን የጳጳሳት ጉባሄ በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።


69ኛው የጣሊያን መደበኛ የጳጳሳት ጉባሄ በግንቦት 8/2008 እንደ ተጀመረ የሚታወቅ ሲሆን በጉባሄው ላይ የተገኙት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንዳሳሰቡት አንድ ካህን ቢሮክራት መሆን ሳይሆን የሚገባው፣ ነግር ግን መሆን ያለበት “ፍቅር ሁሉንም ነገር እንደሆነ ማወቅ እና የሁሉም ወዳጅ እንደ ሚያደርግ መገንዘብ ይኖርበታል መለታቸው ተገለጸ።

በእዚህ ጉባሄ ላይ በርከት ያሉ ሐሳቦች የተነሱ ሲሆን አጽኖት ተሰጥቶ የነበረው ሐሳብ ግን “ካህናት ሕዳሴ ያስፈልጋቸዋል የሚለው ጽንሰ ሐሳብ በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ አጽኖት የተሰጠው እና በቀጣይነትም ካርዲናል አንጄሎ ባኛስኮ በእዚሁ አርዕስት ላይ ተንተርሰው ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንደ ሚሰጡም ይጠበቃል።

ሙሴ ተመልክቶት የነበረው ይቃጠል ይመስል የነበረው ቁጥቋጦ፣  በአንድ ካህን ልንመስለው እንችላለን ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ከሚነደው ቁጥቋጦ ውስጥ በምስጢር የሚታየው እውነታ የእዚህ እሳት ሕልውና ኢየሱስ ሕልውና መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በጉባሄው ወቅት ዘውትር እንደሚያደርጉት በካህናት ሕይወት ዙሪያ ማብራሪያን መስጠት ሳይሆን በወቅቱ የፈለገት ተጨባጭ ከሆኑ ሁኔታዎች እና ከሕይወታቸው ልምድ በመነሳት በሰጡት ማብራሪያ እንዳስገነዘቡት ካህናት በየቁምስናቸው በር ላይ ቆመው የሚጠብቁዋቸውን ምዕመናን ቀርበው ማዳመጥ እንደሚጠበቅባቸው አጥብቀው አሳስበዋል።

በጉባሄው ላይ ለተሳተፉ ብፁዐን ጳጳሳት ቅዱስነታቸው በማበረታቻ ንግግራቸው እንዳሳሰቡት ጳጳሳት ካህናቶቻቸውን ማዳመጥ እና ከእነርሱ መልካም ሕይወት መማር እንዳለባቸውም ጨምረው ገልጸዋል። “በዛሬው ዕለት” አሉ ቅዱስነታቸው “በካህናት ሕይወት ዙሪያ ስልታዊ የሆነ አስተንትኖ እንድታደርጉ አልጋብዛችሁም፣ እስቲ ይልቁኑ በእራሳችን ላይ ያለውን አመለካከት ለመፍታት እንሞክር፣ ካህናቶቻችሁን ለማዳመጥ ዝግጁ ሁኑ። በግንባር ቀደምትነትም ካህናቶቻችሁን ቅረቡ-- የእኛ ጉስቁልናን በልባችን ዓይን እንድያልፍ በማድረግ በታላቅ ትህትና በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ እራሳቸውን እና ሕይወታቸውን የለገሱ በርካታ ካህናት መካከል አንዱን እንዲህ ብለን እንጠይቅ፣ ‘ለሕይወትህ ጣዕም የሚሰጠው ነገር ምን ድነው? ለማን እና ለምንድነው ይህንን ታማኝነትን የሚጠይቅ አገልግሎት እየሰጠህ የምትገኘው? እርሱ እራሱን ለእዚህ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስገደደው ዋነኛው ምክንያት ምንድነው?’” የሚሉትን ጥያቄዎች ክህናቶቻቸውን መጠየቅ እንደሚገባቸው በአጽኖት ገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን እነዚህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለብፁዐን ጳጳሳት ባቀረቡበት ወቅት ሊከተሉ የሚችሉትን መልሶች ከግንዛቤ ያስገቡ ሲሆን ጳጳሳት ከካህናቶቻቸው ጋር የጠበቀ እውነተኛ ግንኙነት እንዲመሰረቱ፣ ካህናት በተለይም ደግሞ የሀገረ ስብከት ካህናት መሰረታዊ የሆነ ጠቅላላ ሚሲዮናዊ  የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች የሁሉም ክርስቲያኖች የሕይወታቸው ማዕከል እንዲሆን፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ መጨረሻ አድማስ ወይም የሕይወታቸው ግብ አድርገው እንዲቆጥሩ፣ የቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ አገልግሎት እና እንዲሁም ሁሉም ክርስቲያኖች እንደ አንድ ካህን ለአገልግሎት መጠራታቸውን እንድያውቁ የምያደርገውን የመሪነት ሚና ካህናት መልሰው እንዲጎናጸፉ ማገዝ ያስፈልጋል” ማለታቸውም ተወስቱዋል።

በቀጣይነትም በእዚህ በብፁዐን ጳጳሳት ጉባሄ ላይ በክለሳ ላይ የሚገኘው እየተሻሻለ የሚገኘው የቤተክርስቲያን የፍርድ አሰጣጥ ሂደትን የተመለከት ሕግ በአጀንዳ ውስጥ የተካተተ የሚቀርብ ሲሆን፣ የሀገረ ስብከቶች የኢኮኖሚ ሀብት አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የተለያዩ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ ክንውኖች በቀጣይነት እንደ ሚነሱ እና ውይይት እንደ ሚደረግባቸውም እና በዛሬው እለትም ጠለቅ ያሉ ውይይቶች ከተካሄዱባቸው ቡኋላ የጋራ አቁዋማቸውን ገልጸው 69ኛው መደበኛ ጉባሄ እንደ ሚጠናቀቅም ለመረዳት ተችልዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.