2016-05-18 16:34:00

የማላዊ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፥ የኑሮ ደረጃ ልዩነትና ድኽነት እንዲቀረፍ


በማላዊ የካሮንጋ ሊቀ ጳጳስ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. የድኾ አገሮች የብድር ጫና ስረዛ የተሰየመው ዘመቻ ተከትሎ የተመሠረተው የአገሪቱ የፍትኅ ኤኮኖሚ አውታረ መረብ አባል ብፁዕ አቡነ ማርቲን ምቱምቡካ  በድኻውና በኃብታሙ የኅብረተሰብ መካከል ያለው የኖሮ ደረጃ ልዩነት እጅግ ከፍ እያለ በመሆኑ የኤኮኖሚ ሊቃውንት የኽ ቅጥ ያጣው ደረጃዊ ልዩነት እንዲቀረፍ በማድረጉ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ እንዲሰጡ ማሳሰባቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አያይዘውም ይኽ የድኾች አገሮች የብድር ጫና ስረዛ ቅስቀሳ የሚያካሂደው መንግስታዊ ያልሆነው ማኅበር አንድ ሺሕ አባላት እንዳሉት ገልጠው፥

ኤኮኖሚና ፖለቲካ ኅዳጌ በማስወገድ ሁሉንም የሚያሳትፍ ስለ ሁሉም የሚያስብ ሁሉንም የሚያጠቃልል የፖለቲካና የኤኮኖሚ ሥልት በማረጋገጥ ድኽነት ለመቅረፍ የሚደግፍ መንገድ መከተል እየከፋ በመሂድ ላይ ያለው የኑሮ ልዩነት እንዲገታና የተስተካከለ ኑሮ ለሁሉም ሰዎች ለማረጋገጥ እንደሚቻል ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ ምቱብኩካ በማላዊ እየተስፋፋፋ ያለው ድኽነት ለመቅረፍ በሁሉም መስክ በተለይ ደግሞ የኤኮኖሚና የፖለቲካ ዓለም ያገለላቸው ዜጎች የሚያሳትፍ ፍትኅ በሚያስቀድም ፖለቲካና ኤኮኖኢ መተካት ያስፈልጋል። ተገሎ ስለ ሚኖረው ዜጋ ማሰብና መደገፍ እራሱን እንዲችል ማደራጀት ለአገር እድገት ግፊትና ፍትኃዊ ተግባርም ነው እንዳሉ ፒሮ ያመለክታሉ።

የዜጎች የመብትና ክብር እኩልት እንዲረጋገጥ

ብፁዕ አቡነ ምቱምቡካ በማላዊ ብዙ ህዝብ የጤና ጥበቃ አገልግሎት የማያገኝ መሆኑ ገልጠው የአገልግሎት መስጫ ለሁሉም ዜጋ መዳረስ ያለበት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክርብ ጉዳይ የሚመለከት  ነውና ለጥቂቱ ብቻ መሆን የለበትም ብለው በመጨረሻም የደሞዝ ክፍያ የሚመለከተው ኤኮኖሚያዊ ቁጠባ ካለው የተዛባ ሂደት ተላቆ ዜጎች ከድኽነት ለማላቀቅ በሚደግፍ የአገሪቱ ኤኮኖሚ ለማንቀሳቀስ ባለመ ኤኮኖሚ አማካኝነት መታደስ ይኖርበታል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዘጠኛ ፒሮ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.