2016-05-11 16:17:00

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፥ ፖለቲካ እጅግ ለተናቁትና በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ድጋፍ


ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 26, 46 “ተነሡና እንሂድ….” በሚል ቃል የተመራ መልእክት የፊሊፒንስ ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት ሮድሪጎ ዱተተ የዳቮ ከንቲባ የነበሩት የወንጀል ቡድኖችና ሙስናን በጽናት የሚዋጉ ባለ ድልና የአገሪቱ ርእሰ ብሔር እንዲሆኑ ያደረገው በአገራቸው የተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ በማስመልከ ይፋዊ መልክት ማስተላለፋቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

እግዚአብሔር የተናቁትናን በድኽነት ሥር የሚገኙትን እንድናገለግል ይጠራናል።

በተካሄደው ምርጫ በማሸነፍ አገር ለመምራት ስለ ሚጠሩ ሁሉ ለሕዝብና ላገር ጥቅም  በተለይ ደግሞ በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ኑሮ ስላልተደላደለላቸው ተነጥለው ስለ ሚኖሩት በተለየ ሁኔታ የሚደግፉ እንዲሆኑ በፊሊፒንስ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ እነርሱ እንደምትጸልይ ብፁዓን ጳጳሳቱ ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፥

በሴቶችና ላቅመ አዳም ባልደረሱት የአገሪቱ ዜጎች ላይ የሚፈጸመው በደል በዝምታ ሊታለፍ የማይገባው እጅግ እየሰፋ በመሂድ ላይ ያለው ጸያፍ ተግባር ብፁዓን ጳጳሳቱ ጠቅሰው በማውገዝ የፊሊፒንስ ያአገሬ ሰው የሚባሉትን ቀደምት ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ብዝበዛና ጭቆና እንዲሁም ተገሎ ለመኖር የሚያስገድዳቸው ሁኔታ ሁሉ ተወግዶ የዜጎች እኩልነ በማረጋገጡ ሂደት መንግሥት ተቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለበት በማብራራት፡ በተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ የተሸነፉት ለእነርሱ ድምጽ የሰጡት ዜጎች ሁሉ በተሸናፊነት መንፈስ ሳይደናገጡ ሁሉም እንደየ ኃላፊነቱ ተሸናፊው የፖለቲካው ሰልፍ ባለው ኃላፊነት የዴሞክራሲ ሚዛንና  ገንቢ የፖለቲካ ተቃዋሚ በመሆን የሕዝብና የአገር በተለይ ደግሞ በድኽንት የተጠቁት ጥቅም ለማስቀደም ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡ ስለዚህ ተሸናፊው አካልና ድምጽ ሰጪው ሁሉ በተሸናፊነት ሳይደናገጥ በተለያየ መልኩ በጋራ የእግዚአብሔ የፍትህና የሰላም የመደጋገፍና የወዳጅነት የሆነ አገር ለመገንባት መንግሥትና ዜጋ ሁሉ እንደየ ኃላፊነቱ እንዲያገለግል አደራ እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት

በፊሊፕንስ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የነቃ ተባባሪነት ለአገርናየ ሕዝብ ጥቅም እንዲረጋገጥ ድምጽ ለሌለው ድምጽ በመሆን በዚህ መንፈስ ከመግሥት ጋር በመተባበር ምእመናን ሁሉ የሕዝብና የአገር ጥቅም በማስቀደም ረገድ በመደገፍ አገር የሁሉም ለሁሉም መሆንዋ በመመስከር የቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብአዊ ትምህርት መሰረት ድምጹንና ተግባሩን በማጣመር እንዲያገለግል በማሳሰብ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደ መስራቸዋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታንጻለች ነቢይነት ትኖራለች ትገስጻለች ታርማለች። ጥሪዋም ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.