2016-04-29 15:37:00

ካቶሊክዊ ሥልጣኔ መጽሔት፥ የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ድንጋያማ ሐወልት ሳይሆን ህያው አካል ነው


Civiltà Cattolica-ካቶሊካዊ ሥልጣኔ የተሰየመው በሁለት ሳምንት እንዴ በኢየሱሳውያን ማኅበር ዋና አዘጋጅነት የሚታተመውና በማኅበሩ በሚተዳደረው መጽሔት በመጨረሻው ቁጥር ኅትመቱ ዘንድ የኢየኡሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ቶማስ ራኡሽ “የቤተ ክርስቲያ አንቀጸ እምነት ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት” በሚል ርእስ ሥር ባወጡት ጥናታዊ ጽሑፍ፥ የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ያንን በሕይወት ገጠመኝ የሚኮነውን ሕያውነቱንና የሚለውጠው ህያው ለበስ ባህርዩን በማግለል መቆጣጠሪያና ማስታወቂያ እንደሆነ አድርጎ አሳንሶ መመልከት አይገባም፡ ስለዚህ አንቀጸ እምነት ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አገልግሎት መርህ መሆኑ አብራርተው፥ በአምስተኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረ ቅዱስ ቺንቸንዞ ሎሪኖ፥ “በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት በየጊዜው የሚራመድ ነውን? ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ጠቅሰው ጥያቄውን ለየት ባለ አነጋገርም፥ ያንን እጹብ ድንቅ የሆነው የእምነት ቀመጡ አቅቦና በጊዜ ውስጥ እንዴት ማስተላለፍ ይቻልል፡ የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ዘገምታዊ ለውጥ ብሎ ለመናገር ይቻላልን?  በሚል አነጋገር ተንትነው።

የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ካንድ ወጥ ድንጋይ የተቀረጸ ሕይወት አልቦ ሐወልት አይደለም

እኚህ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የቲዮሎጊያ ሊቅ፥ ቅዱስ አባታችንን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ከዚሁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ከሆኑት  አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ጋር አካሂደዉት በነበረው ቃለ ምልልስ፤ በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ቅዱስ ቪንቸንዞ ለሪኖ  የሰው ልጅ ሥነ ሕይወታዊ ዘገምተኛ ለውጥና ካንድ ዘመን ወደ ሌላው ዘመን የመሸጋሩ በዘመን የመሆን ለውጥ ከdepositum fidei-ቅሙጠ እምነት ትልልፍ ጋር ያለው ግኑኝንት በማለት አቅርቦት የነበረውን ሃሳብ አስታውሰው ከዚሁ ጋር በማያያዝም ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያን የአንቀጸ እምነት ራእይ ካንድ ወጥ ድንጋይ የጠረበ ሐወልት ካለ ምንም ቅልም መመልከት ስህተት በሚል ሃሳብ ያብራራታል።

የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ከታሪክ ጋር የተቆራኘ በቤተ ክርስቲያን ህያው ሆኖ የሚኖር ነው

ኣባ ራኡሽ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ድንጋጌዎች ውስጥ አንዱን ቃለ እግዚአብሔር በሚል ርእስ ሥር ሕገ እምነት የሚመለከተው ድንጋጌ የቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ባህርይና በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ቤተ ክርስቲያን በሁለ መናዋ እንደምታድግ እንደምትራመድ የሚያብራራ መሆኑ ጠቅሰው ስለዚህ ይላሉ አንቀጸ እምነት ተንቅውሳቃሽ ወይንም ታታሪነት ባህርይ ያለው የቤተ ክርስቲያን በታርክ ውስጥ ህልውናዋ በማበሰርም ይኽ ደግሞ  በእቃቤ እምነት ባህርይዋ በመንፈሳዊነትና በቲዮሎጊያዊ ጥናት ሥር የምታክሂድበት ጥልቅ ምርምር የሚመለከት ነው፡ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ በይፋ ሲከፍቱ ጉባኤው በአንቀጸ እምነት ዙሪያ የሚያካሂደው ጥልቅ ጥናትና ዳግመ ቅምጠቱ የቤተ ክርስቲያን እንቀጸ እምነትና ወንጌላዊ ልኡክነት መካከል ያለው ህያው ግኑኝነት ግምት የሰጠ መሆን አለበት በማለት የገለጡት ሃሳብ አስታውሰው፡ ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ሐሴት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ዓዋዲ መልእክት ሥር በስፋት ያብራሩት ነው ብለዋል።

ክርስትያናዊ አንቀጸ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

አባ ራውሽ በደረሱት ጽሑፍ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ፊረንዘ ከተማ በተካሄደው አምስተኛው ብሔራዊ የቤተ ክስቲያን ጉባኤ ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር ክርስቲያናዊ አንቀጸ እምነት አንድ ዝግ ጥያቄ የሌለው ሰብአዊ መጠራጠር የመሳሰሉትን ጉዳዮች የማያስከትል ስርዓት ሳይሆን  አስተንፍሶ የሚሆንና አለ ማረፍን የመሳሰሉት የሰው ልጅ ለማሰላሰል ለመመራመር የሚገፋፉት ባህርያት የሚያነቃቃ ነው ስለዚህ ህያው ነው። የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት እድገታዊ ሂደቱም አካል መሆኑ  ያረጋግጥልናል። ስለዚህ አንቀጸ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይኽ ደግሞ የእግዚአብሔርን ምሥጢር በጥልቀት የሚነካና ወደ እግዚአብሔር ምሥጢር ዘልቆ የሚገባ መሆኑ ያስገነዝባል፡ የሕዝበ እግዚኣብሔር ዕለታዊ ተጋርጦ የሚጋፈጥ ማለት ነው። ከተጋርጦዎቹ አንዳንዶቹም የሃይማኖት ነጻነት የሚል ድኅነት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሊኖር እንደሚችል የሚተነትን፡ አዳዲስ ባርነት የመሳሰሉትን በወቅታዊው ዓለም የሚከሰቱት ሁሉ ጠቅሰው ካብራሩ በኋላ አያይዘው፥

የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሠረት

ቤተ ክርስቲያን ሓዋርያዊ ልእክት ነች። ይኽ ሲባል ደግሞ በሐዋርያዊ ግብረ ኖላዊነት ደረጃ ብቻ ሳይሆን በስነ እሳቤና በእውነት ደረጃም ጭምር መሆን አለበት። ቅዱስ አባታችን በአቢይ ደረጃ ትኵረት የሚያደርጉበት ጉዳይም አንቀጸ እምነት በቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ጋር ዳግም ማስማማት የሚል አመለካከትና ተግባር የሚል ነው፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ለተሰጣት ወንጌላዊነት ታማኝ በመሆን አንቀጸ እምነት በዘግምታዊ ሂደቱናና በእርማቱ ሂደት ጭምር ትመራለች። ቅዱስነታቸው እንዲህ ባለ አገላለጥም እይታቸው የአንቀጸ እምነት ሓዋርያዊ ግብረ ኖላዊነቱን ግጽታው ላይ መሆኑ ነው የሚያመለክቱት፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ልኡል ትእዛዙም የሰዎች ድህነት የሚል መሆኑ ነው የሚያረጋግጠው በማለት ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፋቸውን አጠቃለዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.