2016-04-26 10:55:00

ቅ. አ. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሳምንታዊውን የጠቅላላ አስተምሮ ለመከታተል ከተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ጋር ተገናኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው ዕለት ማለትም በሚያዝያ 17,2008 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምሮ  ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ሶሪያ የታገቱ ካህናት እና ገዳማዊያን ይፈቱ ዘንድ ጥሪ አድርገው “መሐሪ የሆነ እግዚአብሔር የአጋቾቻቸውን ልብ ያራራ ዘንድ” የተማጽኖ ጸሎት ማድረጋቸውም ተገለጸ። በተመሳሳይም ቅዱስነታቸው እስፔን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት የተገደሉትን ወጣት ሰማዕታት ብጽዕና፣ ቡርጎስ በተባለው የእስፔን ከተማ መታወጁንም በማውሳት ለእነዝህም ብጹኋን ሰማዕታት የመታሰብያ ጸሎት በዕለቱ  ማድረጋቸውም ጭምር ተገልጹኋል።

በእለቱ ልዩ ቅዱስ የምህረት ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለጠቅላላ አስተምሮ ተጋብዘው የነበሩ እድሜያቸው ከ13 እስከ 16 ለሆነው እና ከመላው ጣሊያን እንዲሁም ከመላው ዓለም ለተውጣጡ ታዳጊ ወጣቶች እምነታችወን እንዲለማመዱ እና አንድነታቸውን ለማጠናከር ታስቦ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ለተገኙ ታዳጊ ወጣቶች “ምንጊዜም ሐሳቤ ከእናንተ ጋር ነው” ብለው በተጨማሪም “እዝህ በደስታ ተሞልታችሁ እና ድንቅ በሚባል አቀራረብ ተላብሳችሁ በመምጣታችሁ አማሰግናችኋለው፣ በእዝህ ወኔያችሁ ወደ ፊት በርታታችሁ መጓዝ አለባችሁ” መለታቸውም ተውስቱዋል።

ቅደም ሲል በዕለተ ቅዳሜ በእስፔን ቦርጎስ በተባለው ስፍራ እስፔን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት ለእምነታቸው ብለው ነብሳቸውን አሳልፈ ለሰጡት ለአባ ቫሌንቲና ፓሌንቺያ እና አራት ወጣት ተከታዮቻቸው  የብጽዕና ማዕረግ እንደ ተሰጣቸው ያስታወሱት ቅሱስነታቸው ለእዝህ ዓይነቱ ጠንካራ ምስክርነት ያበቃቸውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁኝ ብለው በእነርሱ አማላጅነት ዓለም ከብጥብጥ ነጻ ትሆን ዘንድ አማጸናለሁ ብለኋል።

በሶሪያ ውስጥ ከረጅም ጊዜ በፊት ታግተው የሚገኙ  ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ገዳማዊያን ካቶሊኮች እና ኦርቶዶክስ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጉዳይ ሁል ጊዜም ያሳስበኛል ብለው መሐሪ የሆነ እግዚአብሔር በምህረቱ የአጋቾቻቸውን ልብ አራርቶ ከታገቱበት በአስቸኳይ ይፈቱ ዘንድ እና ወደ ነበሩበት የማሕበረሰብ ክፍል ይመለሱ ዘንድ ጥሪ በማቅረብ እና እንዲሁም ሁሉም ምዕመናን ጸሎት ያደርጉላቸው ዘንድ አጋጣሚውን ተጠቅመው ተማጽነኋል።

በመጨረሻም “ሁሉንም ምኞቶቻችንን እና ተስፋችንን የምሕረት እናት በሆነችው በእናታችን ማሪያም አማላጅነት ጸሎታችንን ወደ እግዚአብሔር እናቀርባለን” ብለው “የሰማይ ንግሥት ሆይ” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ደግመው፣ በእዝያ የሚገኙትን ምዕመናንን ባርከው እና ሰላምታን አቅርበው ለዕለቱ የነበረው ዝግጅት መጠናቀቁን የቫቲካን የውስጥ የዜና ምንጭ ዘግቡኋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.