2016-04-26 10:27:00

ቅ.አ. ፍራንቸስኮ ከ 70ሺ በላይ ከሚሆኑ ከጣሊያን እና ከመላው ዓለም ከተውጣጡ ታዳጊ ወጣቶች ጋር ተገናኙ።


በሚያዝያ 17,2008 ከ13-16 የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቅዱስ አባታችን መሪነት በተካሄደው ስርዓተ ቅድሴ ላይ ያደረጉት ስብከት ትኩረቱን “ፍቅር” በሚለው ቃል ላይ ያደረገ እንደ ነበር ተገለጸ።

ከ70ሺ በላይ ለሚሆኑ ከተለያዩ የጣሊያን ግዛቶች እና የዓለም ክፍል ለተውጣጡ ወጣቶች እና አጃቢ መሪዎቻቸው “ፍቅር የክርስቲያን የመታወቅያ ወረቀት ነው” በማለት ስበከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “በእዝህ የመታወቂያ ወረቅት ብቻ ነው ክርስቲያን መሆናችንን ሊለይ የሚችለው” ብለው “ይህ የመታወቂታ ወረቀት ስይታደስ ቀርቶ ጊዜ ካለፈበት ግን የጌታችን መስካሪዎች መሆናችን ያበቃል ማለት ነው” በማለት በጉጉት ስብከታቸውን ለሚከታተሉ ወጣቶች ገልጸዋል።

“የኢየሱስን ፍቅር መለማመድ ትፈላጋልችሁ ወይ? በማለት ጥያቄ በማቅረብ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “ከፈለጋችሁ ከእርሱ መማምር ትችላላችሁ ምክንያቱም የእርሱ ቃል ፍቅርን የምንማርበት የሕይወት ትምህርት ቤት ነው” ብለኋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ወቅት ትኩረታቸውን “ፍቅር” በሚለው ቃል ላይ ያጠነጠነ ሲሆን ምንም እንኳን ፍቅር በጣም ውብ እና ወደ ደስታ የሚመራን መንገድ ቢሆንም ቅሉ ቀላል ሊባል የምችል  መንገድ አለመሆኑን በአጽኖት ገልጸው ጥረትን የሚጠይቅ አስቸጋሪ መንገድ መሆኑንም ጨምረው አስገንዝበኋል።

ጌታ በጣም ለጋስ ነው ምክንያቱም “በምንም ዓይነት ሁኔታ መልሶ የማይወስደውን ታማኝ የሆነ ጓደኝነቱን ሁል ጊዜ ስለሚለግሰን” በማለት በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ብታስቀይሙት እና ከእርሱ መንገድ ርቃችሁ ብትሄዱም እንኳ ኢየሱስ ሁል ጊዜም ለእናንተ ቅርብ መሆኑን እና መልካሙን ከመመኘት ወደ ዋኋላ አይልም፣ እናንተ ከምታምኑት በላይ እርሱ ስለ እናንተ ያምናል” ብለው “ይህንንም መገንዘብ በጣም አስፈላጊው ነገር” ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም “መልካም በሆነ ሁኔታ እንዳናድግ የምያደርገን ትልቁ ስጋት የሚመነጨው ለእኛ የምያስብ እና የሚጠነቀቅ ማንም ሰው የለም ከሚለው አስተሳሰብ በመሆኑ ነው” ብለኋል።

በስብከታቸው ወቅት ቅዱስነታቸው ለታዳጊዎች እራሳቸውን  “ሊኖራችሁ ይገባል” ከሚለው የፍጆታ እቃዎችን ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሸመትን ከምያበረታታው ባህል በደመ ነፍስ ከመሳብ እራሳችሁን እንድትጠብቁ ያስፈልጋል ብለኋል።

“ንፋስ ወደ ነፈሰበት ቦታ ሁሉ አብራችሁ እንድትነጉዱ በሚገፋፋችሁ ስንፍና አትደሰቱ ወይም ምቾት አይሰማችሁ” በማለት ታዳጊ ወጣቶችን ያስገነዘቡት ቅዱስነታቸው “በጣም አስፈላጊ ሰው መሆን ከፈለክ የፊልም አክተሮችን መምሰል አለብህ እዲሁም አዳዲስ የፋሽን ልብሶችን መጠቀም ይኖርብኋል ብለው ልያሳምኑ የምፈልጉኋችሁን ሰዎች በቀላሉ ማመን የለባችሁም” በማለት ያስገነዘቡት ቅዱስነታቸው “የእናንተ ድስታ በምንም ዓይነት ሁኔታ ሊሸመት የሚችል አይደለም፣ በተጨማሪም በስልካችሁ ላይ እንዳለው ማንኛውም ዓይነት አፕሊኬሽን የሚጫን እና ወድያሁኑ ነጻነትን እና ፍቅርን የምያጎናጽፋችሁ እንዳልሆነ ልትገነዘቡ ይገባል በማለት አሳስበኋል።

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ለተገኙ ታዳጊዎች “ብርታት እንዲኖራቸው እና በውሳኔያቸው ጸንተው መኖር እንዳለባቸው ተማጽነው ይህንን በማድረግ ብቻ ነው ህልማችሁን እውን ማድረግ ይምትችሉት” ብለው  በተጨማሪም “በእናንተ እድሜ ክልል ያለ ሰው ሕልም የሌለው ከሆነ ልክ በጡረታ እንደ ተገለ ሰው በመሆኑ ይህንን የማይጠቅም አስተሳሰብ ማስወገድ ይኖርባችኋል” ብለኋል።

“ፍቅር የሚጸናው ስለ ፍቅር ስለ አወራን ብቻ አይደለም” በማለት አስምረው የተናገሩት ቅዱስ አባታችን “ፍቅርን ልንኖርበት ይገባል” ብለው “ወደ ላይ የመውጣት ጥበብ  የሚለካው ምንም እንኳን ብንወድቅም መሬት ላይ መቅረት አስፈላጊ አለመሆኑን በመሆኑ ሁል ጊዜም ከውድቀታችን ተነስተን ወደ ፊት ለመራመድ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል” ብለኋል።

በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ቅዱስነታችው ለታዳጊ ወጣቶች እንዳሳሰቡት “በቂ የሆነ ዝግጅት ካደረጋችሁ አስደናቂ ነገሮችን ማከናወን ትችላላችሁ” ብለው “ከአሁኑ ጀምራችሁ የወጣትነት ሕይወታችሁን እና ተስጦኋችሁን የሥራ ከባድነት ስያስፈራችሁ ሙሉ በሙሉ መተግበር ይጠበቅባችኋል” ብለው “ልክ ብዙ ልምምድ እና ጥረትን በማድረግ ወጤታማ እንደ ሚሆን  እስፖርተኛ ልትሆኑ ያስፈልጋል” በማለት በዕለቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የነበረው ዝግጅት ቡራኬን እና ሰላምታን በማስከተል ተጠናቀኋል። 

ይህ በዝህ እንዳለ በተመሳሳይ ቀን ለእነዝሁ ከመላው ጣልያን እና ከመላው ዓለም ለተውጣጡ ታዳጊ ወጣቶች በኦሎፒኮ እስታዲየም በቀጣይነት ልዩ ቅዱስ የምህረት ዓመትን አስመክቶ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ በመገኘት በድጋሜ ሰላምታን ለታዳጊ ወጣቶች እና ለአጃቢዎቻቸው ካቀረቡ ቡኋላ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ጥዋት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት ስርዓተ ቅድሴ በመከታተላቸው እና ንስኋ በመግባት በቅዱስ በር በማለፋቸው ድስ እንደ ተሰኙ አውስተው አሁንም በኦሎፒኮ እስታዲየም ስርዓትን በጠበቀ መልኩ በመሰብሰባቸው ከፍ ያለ ምስጋናን አድርሰኋል።

“ያለፋችሁበት የምህረት በር የእግዚአብሔርን ፍቅር ካስተማረን ከክርስቶስ ጋር የምያገናኛችሁ እንደሆነ  ልትረሱ አይገባም” ብለው “ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ደግሞ እርሱ መሐሪ እንደ ሆነ እኛም ምህረት አድራጊዎች እንድንሆን ያስተምረናል” ማለታቸውም ተዘግቡኋል።

“ቸሮች እና ርኅሩኆች መሆን ማለት ይቅርታን የማድረግ ችሎታን ማዳበር ማለት ነው፣ ይህ ግን ቀላል ሊባል የሚችል ነገር አይደለም” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በተለያዩ አጋጣሚዎች የበደሉንን ሰዎች ቂም ይዘን መቆየት እንደ ማይገባም” አሳስበኋል።

“ይቅርታን ማድረግ እና በደልን መርሳት ትክክለኛ ክርስቲያን እና መስካሪዎች እንድንሆን ይረዳናል” በማለት ወደ ንግግራቸው ማጠቃለያ የተቃረቡት ቅዱስነታቸው “የቅርታን የምናደርግበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ደስተኞች እንድንሆን ስለ ምያደርገን ነው” ብለው “በቤታችን ውስጥ፣ በትምህርት ቤት እና በቤተ ክርስቲያን በተለያዩ አጋጣሚዎች የበደሉን ሰዎች ካሉ ይቅርታን ልናደርግላቸው ይገባል” በማለት ቡራኬን እና ሰላምታን ለግሰው መሰናበታቸው ተዘግቡኋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.