2016-04-23 10:00:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በሮም ሀገር ስብከት ውስጥ የሚገኘው የካሪታስ ማሕበር ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ መካፈላቸው ተገለጸ።


በሚያዝያ 14,2008  በሮም ሀገር ስብከት ውስጥ የሚገኘው የካሪታስ ምሕበር ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “በቤተ ክርስቲያን በኩል ለድሆች የምትዘረጉትን የጌታን የምሕረት እጅ ሳትሰለቹ መዘርጋታችሁን ልትቀጥሉ ይገባል” በማለት ማሳሰባቸው ተገለጸ።

“ቤተ ክርስቲያን በፍቅር እና በታማኝነት ታድግ ዘንድ አምላክ ድሆችን ለቤተ ክርስቲያን በአደራነት ሰቱዋቸኋል” በማለት በኢጣልያን በሚገኙ ሀገረስብከቶች ውስጥ በንቃት እየተንቀሳቀሰ እና ለድሆች ከፍተኛ የሆነ እገዛ በማድረግ ላይ የሚገኘውን የካሪታስ ማሕበርን አጋጣሚውን ተጠቅመው አመስግነዋል።

ቅዱስነታቸው በተጨማሪም “በድሆች ውስጥ ኢየሱስን ማግኘት እንችላለን “ ብለው “ ሁል ጊዜም ቢሆን በድሆች እና እርዳታ ፈላጊ በሆኑ ሰዎች ፊት ላይ የሚታየው የክርስቶስ ገጽታ በመሆኑ፣ እነርሱን ማገልገል ማለት ክርስቶስን ማገልገል ተደርጎ ስለሚቆጠር ሳትሰለቹ መልካም አገልግሎታችሁን ልትቀጥሉ ይገባል” ብለኋል።

“ኢየሱስ በእየ አንድ አንዳችን ልብ እና የማሕበር ቤት በር ላይ ቆሞ ያንኩዋኳል እስኪከፈትለትም በትዕግስት ይጠባበቃል፣ የእኛን ለጋሽነትም ይፈልጋል ለዝህም ምላሽ መስጠት ማለት የእግዚአብሔርን የምሕረት እጅ በቤተ ክርስቲያን በኩል መዘርጋት ማለት በመሆኑ ይህም መልካም ተግባር የእግዚአብሔርን በረከት እና ጥበቃን እንደ ምያስገኝም እርግጠኛ በመሆን መልካም ተግባራችንን አጠናክረን መቀጠል ይገባናል”  ቅዱስነታቸው ማለታቸውም ተገልጹኋል።

“እናንተ የካሪታስ ማሕበር ሰራተኞች  እየፈጸማችሁት የምተገኙት የምሕረት ተግባራት “ አሉ ቅዱስነታቸው “በግለሰብ ደረጃ እያበረከታችሁ የምትገኙት ተጨባጭ እና ብቃትን የተሞላ ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ በማሕበርም ደረጃ የምታካሂዱት ታማኝ የሆነ አገልግሎታችሁም ከወንጌል ተግባራት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በዓልም የሚገኙ ድሆችን በዝህ ተግባር እንዲሳተፉ የምታደርጉት ጥሪም ሊረሳ የማይገባው ድንቅ የሆነ ተግባር” መሆኑን ቅዱስ አባታችን መስክረዋል።

የካሪታስ ማሕበር ዋና ተግባር ሊሆን የሚገባው ሁሉም የማሕበረሰብ ክፍሎች ለድሆች እና በችግር ላይ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ መመጽወትን ልማዱ አድርጎ እንድያድግ እና ድሆችን ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመርዳት ይምያስችል መንገዶችን እንዲዘይዱ፣ በተጨማሪም በማንኛውም መልኩ ለድሆች አለኝታነታቸውን መግለጽ የምያስችላቸውን ባሕሪ እንዲላበሱ ማነሳሳት፣ ማበረታት እና በዓለም ሁሉ የሚገኙ ድሆችን ማገዝ የሚቻልበትን መምገድ መቀይስ ሊሆን ይገባል በማለት ንግግራቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.