2016-04-22 16:37:00

የኔታ ጁዜፐ ሎሪዚዮ፥ የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ተቀብሎ እግብር ላይ ማዋል


ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የአንቀጸ ቲዮሎጊያ መምህር የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ጁዘፐ ሎሪዚዮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን አስደገፈው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የሐዋርያዊ ምዕዳኑ ስልጣናዊ ትምህርት ላይ በማተኮር በቤተ ክርስቲያን ብዙ ጊዜ እንደሚታየውም አንድ አዲስ ነገር ሲቀርብ ለመቀበሉ ያስቸግራል ወይንም ደግሞ አዲሱ ነገር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ባህር ያለው ነው ተብሎ በማለት በደፈናው ይገለጣል፡ ይኽ ደግሞ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወቅት የታየ ጉዳይ መሆኑ አስታውሰው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያመጣው ኅዳሴ መቀበል ያቃተው ለውጡን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ባህርይ ያለው ነው ብሎ ለምእመናን በዚሁ መልክ በማስረዳት ያንን ስልጣናዊ መልእክቱና ትምህርቱን ለማሳነስ ተሞክሯል ብለው፥

ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የእምነት አንቀጸ ትምህርት ያካተተ ነው

አንድ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ሲኖዶስ ወይንም ሐዋርያዊ ምዕዳንና ዓዋዲ መልእክት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ባህርይ ያለው ነው ሲባል የእምነት አንቀጽ ያካተተ ሥልጣናዊ ትምህርት ማለት ነው፡ ስለዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከአንቀጸ እምንት መነጠል ወይንም ነጥሎ መመልከት አይቻልም። አንድ ሲኖዶስ ሲጠራ ቀድሞ ተሰጥቶ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ለመሻር ወይንም አንቀጸ እምነት ለመቀየር ታልሞ አይደለም። ወቅታዊ ሁነት ግምት ሰጥቶ በዚያ በነበረው ሥልጣናዊ ትምህርት የሚታከል ወቅታዊነት በቅዱስ መጽሓፍ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሥልጣናዊ ትምህርትና በቲዮሎጊያ ሥር በማንበብ ሥልጣናዊ ትምህርት ለማቅረብ ነው። ስለዚህ ከነበረው ሥልጣናዊ ትምህርት ለየት ያለ የሚያቀርበው አንድ አዲስ ገጽታ ይኖረዋል ማለት ነው፡ ቤተሰብ ርእስ ዙሪይ የተካሄዱት ሁለቱ ሲኖዶሶች አብነት ናቸው ብለዋል።

በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ወደ ፊት ለመራመድ

የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን  ከዚያ በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1981 ዓ.ም. ቤተሰብአዊ ማኅበር በሚል ርእስ ሥር ከደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ጋር የተስተካከለ ክብር ያለው ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሐዋርያዊ ምዕዳኑ ላይ የሚያሳስቡት ጋብቻ ወይንም ቃል ኪዳን ያንን በግልጸት የተሰጠው መልእክት የሚያብራራ ነው፡ ሆኖም ምሥጢር ተክሊል በተመለከተ የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ወቅታዊ ሁነት ግምት የሰጠ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዝብ ሥልጣናዊ ትምህርት አዘል ነው፡ አጠር ባለ አነጋገር ግልጸት በወቅታዊው ዓለም የሚልና የሚያብራራ ነው፡ በመሆኑም መላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት በጠቅላላ ምእመናን እግብር ላይ የማዋል ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

የፍቅር ሐሴት ዓዋዲ መልእክት አዲስ አንቀጸ እምነት አዘል አይደለም

በርግጥ ይኽ የፍቅር ሐሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን የእምነት ሕግ ማለት ዶግማ አይደለም። የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ስለ እምነት ሲናገሩ አይሳሳቱም የሚለው ውሳኔ ለበስ ምዕዳን አይደለም። ነገር ግን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሮማ ጳጳስ ምዕዳን በመሆኑ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ውህደት ያላቸው ለመንበረ ጴጥሮስ ባላቸው ታዛዥነት መሠረት በሱታፌና በታማኝነት ምዕዳኑን በሁሉም አገሮች በሚገኙት ሰበካዎች ቁምስናዎችና ማኅበራና ገዳምት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እግብር ላይ የማዋል ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.