2016-04-22 16:33:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ለአዲስ አድማስ ማኅበርሰብ መሥራች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮ የአዲስ አድማስ ማኅበር መሥራች ኪያራ አሚራንተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይኽ ማኅበር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በይፋ ለሕጋዊነት መታቀፍ የሚያበቃው በቤተ ክርስቲያን ሥር የሚመራ ባለ ሙሉ መብት የቤተ ክርስቲያን ማኅበር መህኑ እውቅና የሚያሰጠው የማኅበሩ ሕግ በቤተ ክርስቲያን በሚመለከተው ጳጳስዊ ምክር ቤትና ቅዱስ ማኅበር አማካኝነት ጥልቅ ጥናትና አዳዲስ ሃሳብ መታከል ከተደረገበት በኋላ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሠረት በመጽደቁ ምክንያት የማኅበሩ መሥራች አሚራንተ ለቅዱስነታችው ያስተላለፉት የምስጋናና የውሉዳዊ መልእክት ምክንያት ቅዱስነታቸው  በተራቸው  ባስተላልፉት የመልስ መልእክት፥ የማኅበሩ የመመሪያ ደንብ በመጽደቁ ምክንያት የተሰማቸው ደስታ ገልጠው፡ ይኽ ማኅበር በዚህ በዓለማዊ ምቾት እንዲሁም ለብ ያለ ሕይወት በሚመርጥበት ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ብርኃን አማካኝን የሚመራ እምነት የሚጸግወው መልካም ፍሬ በማካፈል ዓለም በጌታ ብርኃን ማብራት የሚል ዓላማ ያለው መሆኑ ኪያራ አሚራተ ባስተላለፉት መልእክት ያሰፈሩት ሃሳብ ጠቅሰው፥ ይኽ ማኅበር ለዚህ የላቀ ዓላማ ብቃት ያለው ሆኖ በምንኖርበት ዓለም በምህረት በደስታ በወንጌል ላይ ጸንቶ የእምነት ሐሴት እንዲመሰክር አደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ኪያራ አሚራንተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት የማኅበሩ ሕግ በማጽደቋ ለማኅበሩ አቢይ ደስታ ነው። ደስታውም ያንን የትንሣኤ ሐሴት ማበሰር የሚለው የማኅበር መፈሳዊው ዓላማ በበለጠ ለማስተጋባትና በዕለታዊ ሕይወት ወንጌላዊ ሕይወት በመኖር የዓለማችንን ጨለማዎችና ሌሊቶች በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ለሚፈጠረው በእምነት መዛል የሚያስከትለው አለ የእምነት ብርሃን የመኖር ጉዳይ በዚያ የትንሣሴ ብርሃን ቦግ ብሎ ደስተኛ ሕይወት እንዲኖር መደገፍ ነው፡ ገዛ እራስ በእምነት ብርኃን ቦግ ብሎ ሌላው የዚህ የእምነት ብርኃን ተቋዳሽ ብቻ ሳይሆን በእምነት ብርኃን መኖር የሚሰጠው ደስታ የገዛ እራሱ ገጠመኝ እንዲያደርግ መደገፍ የሚል ነው፡ ይኸንን መንፍሳዊነት ቤት ክርስቲያን እውቅና ስትሰጥበት አቢይ ጸጋ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.