2016-04-20 16:27:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ስደተኛው ጸጋ እንጅ ሸክም አይደልምና በር አንዝጋባቸው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢየሱሳውያን ማኅበር የተመሠረተውና በማኅበሩ የሚመራው የአስታሊ የስደተኞች መርጃ ማእከል በኢጣሊያ የፖለቲካ ጥገኛ ጠያቂዎችና ተፈናቃዮች ሁኔታ ላይ ያተኮረ የ2016 ዓ.ም. የጥናት ሰነድ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ ወደ በዳበቃበት ዓውደ ጉባኤ ዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 25 ከቍጥር 31 እስከ መጨረሻ ባለው ቃል ላይ በማተኰር ባስተላለፉ የድምጸ-ራዕይ መልእክት፥

እንግዳ ሆኜ (መጻእተኛ) ተቀብላችሁኛል የሚለው ቃል ለየት ባለ ሁኔታ በመጥቀስ በቅድሚያ የአስታሊ ማእከል ለስደተኞና ለተፈናቃዮች የሚሰጠው አገልግሎ አመስግነው፥

በሮቻችን የሚያንኳኵ ስደተኞች የጌታ መልክ ያላቸው ናቸው

ከጦርነት ፍትህ ከተጓደለው የተፈጥሮ ሃብት የማስዳረሱ ጉዳይ አስገድዷቸው የሚሰደዱ ወንድሞቻን ናቸው። ያለንን እንጀራም ይሁን ቤትና ሕይወት ተቋድሰን መኖር ይገባናል። እያንዳንዱ በዓውደ ጉባኤ የተገኙትን ስደተኞችን በማሰብም እናንተ በሮቻችን የምታንኳኩ ዜጎች የጌታ አካል ናችሁ። የጌታ መልክ ያላችሁ ናችሁ። የእናንተ ስቃይን መከራ በዚህ ምድር ሁላችን ስደተኞና ነጋዲያን መሆናችን ያረጋጋጥልና።

ኅብረተሰባችን የሚኖረው ዝግታማነትና ግዴለሽነት ማስወገድ

እያንዳንዱ ስደተኛ የተለያዩ እሩቅ ካሉ ሕዝቦች ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው። የባህሎች የተለያዩ ኃይማኖቶች በማገናኘት የጋራ የሆነውን ሰብአዊነታችን ጋር ለመገናኘት የሚያበቃ ጸጋ እንጂ ሸክም አይደለም። ስለዚህ ስደተኛው ሸክም ችግርና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ ሳይሆን ጸጋ መሆኑ መስተዋል ይኖርበታል፡ እናንተ ያሳለፋችሁት ኢፍትሐዊነትና ያጋጠማችሁ ክፋት ሁሉ የሚለውጠው ጌታችን ቸርና መሐሪ መሆኑ የምትመሰክሩ ናችሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ በሮቻችንን ስለ ዘጋንባችሁ ይቅርታ አድርጉልን። ኅብረተሰባችን የስደተኛው ጸአት ሊከስተው የሚችለውን ማንኛውም ዓይነት ለውጥ በመፍራት ለሚያሳያችሁ ዝግታማነትና ግዴለሽነት መንፈስና ተግባር ይቅርታን ከእናንተ እንጠቃለን፡ ቸሩና መሐሪው አምላካችን ኢፍትሃዊነትና ክፋት ሁሉ ለሁሉም የሚበጅው መልካምነት የሚለወጥ መሆኑ መስካሪያን ናችሁ።

መገናኘት ያለው ውበት መመስከር፡ የስደተኛው ድምጽ ማዳመጥ

የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ በነበሩት በአባ ፐድሮ አሩፐ ነቢያዊ ራእይ አማካኝንት የተመሠረተው ይኽ የኢየሱሳውያን ማኅበር የስደተኞችና ተፈናቃዮች መርጃ ማእከል ለስደተኛውና ለተፈናቃዩ የሚሰጠው አገልግሎት የጠቀሱት ቅዱስ አባታችን አክለው በዚህ ማእከል የሚያገለግሉትን ሁሉ በማመስገን። የበጎ ፈቃድ ሠራተኞችን ሁሉ በሚሰጡት አገልግሎት ዘወትር በጋራ መኖር የሚቻል መሆኑና ታርቆ በጋራ ለመኖርም ብቸኛ መንገድ መሆኑ የሚያስተውል አገልግሎት አቅርቡ አደራ በማለት በአገልግሎታችሁ በርቱ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ጠቁሞ፥ እናንተ መገናኘት ለሌላው ቅርብ መሆን ያለው ውበት መስካሪያን ናችሁ። ኅብረተሰባችን የስደተኛውና ተፈናቃዩ እሮሮ ያዳምጥ ዘንድ ደግፉ። በብርታት ከስድተኛውና ተፈናቃዮ ጎን በመሆን ተጓዙ ምርዋችው እነርሱም ይመሩዋችሁ ዘንድ ፍቀዱ። ምክንያቱ የጦርነት አስከፊውን ገጽታ በሚገባ የሚያውቁ ናቸውና በሰላም መንገድ ይመሩናል ሲሉ ያስተላለፉት መልእክት እንዳጥቃለሉ አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት አማካኝነት የ2016 ዓ.ም.  የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂው ስደተኛና ተፈናቃይ ሁኔታ ርእስ ዙሪያ አስታሊ ማእከል ያወጣው የጥናት ሰነድ ለንባብ ለማብቃት ያስጀመሩት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የኤውሮጳ ኅብረት የቀድሞ ሊቀ መንበርና የኢጣሊያ ነበር መራሔ መንግሥት ሮማኖ ፕሮዲ የኢጣሊያ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፒየትሮ ግራሶ መሳተፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገልጠው፥ በ2015 ዓ.ም. 154 ሺሕ ስደተኛ ወደ ኢጣሊያ የገባ ሲሆን ከ 2014 ዓም. ጋር ሲነጻጻር በ 20 ሺሕ ክፍ ብሎ መገኘቱም በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ መገለጡ አስታውቀዋል።

የስደተኛው ጸአት ለኢጣሊያ ብቻ ሳይሆን ለዓለማችን ፖለቲካዊ ኤኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳይ አቢይ ተግዳሮት ነው፡ ስደተኛውን ተቀብሎ የሚያቀርበው የጥገኝነት ጥያቄ በሚገባ አጢኖ ምክንያታዊ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መልስ ለመስጠ አለ መቻሉ በእውነቱ ስደተኛውን ለተለያየ ዘርፈ ብዙ አደጋ እያጋለጠው መሆኑ ሰነዱ ያመለከተው ሃሳብ በስፋት መብራራቱ የገለጡት የቫቲካ ራዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ አያይዘው የስደተኛው ጉዳይ የሚመለከተው የአሥተዳዳር ስልት ብዙ ግድፈት ብቻ ሳይሆን እጅግ ዘገምተኛ በመሆኑም ለዚያ ከጦርነት ከእርሃብ ያመለጠው የተለያዩ ችግሮ በመጋለጡ ምክንያት ኢጣኢያ የገባው ስደተኛ ከሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሌላ የሥነ ልቦና የህክምና ድጋፍ የሚያስፈግለው ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም ከገባበት ሕዝብና አገር ጋር ተዋውቆ ለመኖ የሚደግፈው ሕንጸት ማግኘት ይገባዋል። ከዚህ አንጻር ሲታይ የስደተኛው ችግር ዘርፈ ብዙ መሆኑ ለማስተዋል የሚያዳግት አለ መሆኑ ለጉባኤው ንግግር ያስደመጡት የማእከሉ አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ካሚሎ ሪፓሞንቲ ማብራራታቸው አስታውቀዋል።

የኢጣሊያ የውስጥ ጉዳይ  ሚኒ. የማስታወቂያና ግኑኝነት ጽሕፈት ቤት እንዳመለከተውም በ 2015 ዓ.ም. በባህር ጉዞ በኩል ወደ ኢጣሊያ የገባው የስደተኛው ብዛ 150 ሺሕ መሆኑ ሲታወቅ፡ ይኽ ደግሞ የአስታሊ ማእከል ካጠናቀረው ሰነድ ጋር የሚስማማ ሲሆን፡ በሮማ 21 ሺሕ ሲቀሩ የተቀሩት ወደ ተለያዩ የኢጣሊያ ከተሞችና ወደ ሌሎች የኤውሮጳ አገሮች መዛወራቸው አባ ሪፖሞንቲ ገልጠው፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለስቦ ግሪካዊቷ ደሴት የሚገኙትን ስደተኞችና ተፈናቃዮች ከቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ጋር በመሆን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያንን በለስቦ ደሴት ያዩት የሰደተኛውና የተፈናቃዩ ሁኔታ ለመላ ሰው ልጅ የህልውና ጥያቄ ከመሆኑም ባሻገር የስደተኛው ሁኔታ ሁሉንም ጠቅለል ያደረገ መልስ የሚሻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ስደተኛ ሁኔታ ማወቅ እንደሚያስፈልግ ገልጠው፡ በተለይ ደግሞ የሰውን ልጅ ለስደተና ለመንፈናቀል አደጋ የሚዳርገው ችግር ለይቶ መትሔ እንዲያገኝ ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ገልጠውልናል። የጦር መሣሪያ ንግድ አንዱ በዓለማችን ጦነርነት እንዲኖ የሚያደርግ ለስደትና ለመፈናቀል የሚዳርግ ችግር ጠቋሽ መሆኑ በአጽንኦት ገልጠዉታል። ስለዚህ ጦርነት እንዲኖ እያደረግክ ሕይወቱን ለማዳን ለሚሸሸ በርን መዝጋት አቢይ ክፋት ነው፡ ስደተኛው ቁጥር ሳይሆን ሰው ነው፡ አጨናንቆ ባንድ ክልል ማጎር ሳይሆን ወደ ተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች በማዳረስ የተሟላ ድጋፍ ማቅረብ የሁሉም አገሮች ግዴታና ሰብአዊ ኃላፊነት መሆኑ በጥልቀት ገልጠዉታል እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ ይፋ አድርገዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.