2016-04-18 16:34:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ስደተኛ ቁጥር ሳይሆን ሰብኣዊ ፍጡር ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለስቦ ግሪካዊቷ ደሴት የሚገኙትን ስደተኞችና ተፈናቃዮች ከቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ጋር  በመሆን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ያካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስደገፍ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ሁላችን እንምደናውቀው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከሌላው ጋር አለ ምንም መሰናክል በቀጥታ መገናኘት የሚወዱ ናቸው። በዚህ በለስቦ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት እያንዳንዱን ስደተኛ ቀርበው በመጨበጥ ለተናቀው ለተነጠለው የሚል ፍቅር በእውነቱ የክርስትናን ቀጥተኛ ትርጉሙን በተግባር መስክረዉታል፡ በዚህ በተካሄደው ሐዋርያዊ ጉብኝት የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ያላቸውን ውህደትንም አረጋግጠዋል።

ከቃላት በላይ እጅግ መልእክት የሚያስተላልፈው ተግባር ነው። በመሆኑም ቅዱስ አባታችን እዛው ለስደተኞችና እዛው ለተገኙት በጠቅላላ መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ መልእክት ያስደመጡ ቢሆንም ቅሉ ቀርበው እያዳንዱን ስደተኛ ሰላም በማለት የእያንዳንዱ ችግር ብሶት ስቃይ በማዳመጥ ያሳዩት ፍቅር በከፍተኛ ደረጃ ለዓለምና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እንዲሁም መንግሥታ ታላቅ መልእክት ነው፡ ስደተኞቹ ከመካከለኛው ምስራቅና ከተለያዩ የዓለማችን ክልሎች በተለያዩ ችግሮች ተገፋፍተው የመጡ ናቸው።

ስደተኛው ቁጥር ሳይሆን ሰብአዊ ፍጡር መሆኑ የመሰከረ ተግባር ነው ያሳዩት። ስደተኛው ከገዛ አገሩ በግጭትና ጦርነት ምክንያት ሲሰደድ ተሰዶ ከገባበት አገር ወደ ሌላው አገር መስተንግዶ ለማግኘት ሲል እንዱ አገር ሲያባረው የግንብ አጥር በማንሳት ሲያግደው ሲንገላታ ማየቱ ያሳዝናል። ስለዚህ በዚያ ለስቦ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ሠፈር የሃይማኖት መሪዎች ተገኝተው ያሳዩት የፍቅር ምልክት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲከበርለት አደራ የሚል ጥሪ በተግባር ያስተግባ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት መሪዎች ግብረ ገባዊ ኃላፊነት ያላቸው ናቸው። ስለዚህ የሚያስተላልፉት መልእክት የፖለቲካ አካላትና መንግሥታት እጅግ አስቸጋሪና የተወሳሰበውን የሰብአዊ ሁነት ሰብአዊ ልክነት ባለው ሂደት አማካኝንት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እንዲወጡ የሚያሳስብና ለሰው ልጅ ሰላም እንዲተጉ የሚያነቃቃ ነው፡ የምንኖበት ዓለም ሰላማዊ ለመሆን እንዲችል ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልሱ ምንም መሆን እንደሚገባው የሚያስገነዝብ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነበር በማለት አባ ሎምባርዲ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.