2016-04-13 17:31:00

የር.ሊ.ጳ ሳምታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ለተገኙ በብዙ ሺዎች ከሚቆጠሩ ነጋድያንና ምእመናንን ተገናኝተው ሰላምታ ካቀረቡና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ ለዕለቱ ኣስተምህሮ መግብያ ይሆን ዘንድ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ዘጠኝ ‘ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።  በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።  ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው።  ኢየሱስም ሰምቶ። ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤  ነገር ግን ሄዳችሁ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።’ የሚለው ከተነበበ በኋላ በጣልያነኛ ቋንቋ ሰፊ ኣስተምህሮ ኣቅርበዋል፣ የሚከተለው ማጠቃለያም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ቀርበዋል፣

በዚሁ የምሕረት ዓመት በተከታታይ በምናቀርበው ትምህርተ ክርስቶስ በዛሬው ኣስተንትኖ ከወንጌለ ማቴዎስ የተነበበውን እንመለከታለን፣ ጌታ ኢየሱስ በሕዝቡ እንደሓጢኣተኞች ይቈጠሩ የነብሩትን ተከታዮቹ እንዲሆኑ መጥራት ብቻ ሳይሆን ለፈሪሳውያን ዕንቅፋት እስከመሆን ድረስ ከሓጢኣተኞች ጋር በማእድ ኣብሮ በመብላትና በመጠጣትም ነበር፣  የማቴዎስ ጥሪ ጌታ ተከታዮቹ ኣድርጎ ሊልከን ሲፈልግ ያለፈውን ታሪካችን ሳይሆን ወደፊት የምንሆነውን እንደሚመለከት ያስረዳናል፣ ጌታ ሲጠራን ማድረግ ያለብን ኣንድ ነገር ብቻ ነው፣ በትሁትና ንጹሕ ልብ ኣብየት በማለት መልስ መስጠት ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ከእርሱ ጋር በቅዱስ ቊርባን ማእድ እንድንሳተፍ ጥሪ ያቀርብልናል፣ በዚህም በቃሉ ሃይል ኣንጽቶን በምስጢራቱ ወደ እርሱ በመቅረብ ከእርሱ ጋር ኣንድ እንድንሆን ያደርገናል፣ ኣስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ሆሴእ ነቢይ ያለውን በመጥቀስ የእግዚኣብሔር ፍላጎት ‘ምሕረት እንጂ መስዋዕት ኣለመሆኑን’ በማመልከት ደግሞ እውነተኛ የልብ መቀየር እንጂ ላይ ላዩን ብቻ የሚታይ ሃይማኖታዊነት እንደማያስፈልግ ይነግረናል፣ ሁላችን ሓጢኣታችን በማመን ለዚሁ የጌታ ጥሪ በለጋስነት እንድንመልስ እንዲሁም ከጌታና ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በቅዱስ ቊርባን ማእድ በመቅረብ ለሰጠን ወደር የልሽ ምሕረትና ኣድኝ ፍቅር ታላቅ ምስጋና  እናቅርብለት፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.