2016-04-11 16:52:00

አባ ስፓዳሮ፥ የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ግብረ ኖላዊ የቤተ ክርስቲያን የአንቀጸ ሃይማኖት ትምህርት


የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በማኅበሩ በየሁለት ሳምንት አንዴ ለሚታተመው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ ለተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው የመጽሔቱ የመጨረሻው ኅትመት ዘንድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የደረሱት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ የበቃው የፍቅር ኃሴት የተሰየመው ሓዋርያዊ ምዕዳን ላይ በማተኰር ባቀረቡት ሐታት ሐዋርያዊው ምዕዳን ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለት ሲኖዶስ ላይ የተመሠረተ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ጽማሬ መሆኑ በስፋት ያብራሩ ሲሆን። በዚህ አጋጣሚም አባ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፥ ፍቅር በኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ወይንም ፍቅር በተመለከተ በአንቀጸ ሃይማኖት ሥር ያለው ትምህት የሚቀይር ሳይሆን ያንን ትምህርት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እግርብ ላይ ለማዋል የሚደገፍ መሆኑ ነው፡ ስለዚህ ስለ ቤተሰብ የሚመለከተው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የማይጨበጥ ረቂቀ ሃሳብ ሆኖ የሚቀር ሳይሆን ተጨባጭ መሆኑ የሚተነትንና በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል የሚመራ ስልጣናዊ ትምህርት መሆኑ አብራርተው። ከዚህ ጋር በማያይዝም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቃልና ሥጋ ነው ስለዚህ ቃል ሲባል ተግባር ያካተተ ነው ብለዋል።

በቅዱስ ኢግናዚዮስ መንፈሳዊነት ልይት ሲባል በሕይወት ውስጥና ጉዞ እግዚአብሔርን ማግኘት ማለት ነው፡ ባጭሩ ወንጌላዊ ኅሊና የሚያነቃቃና አንቀጸ እምነቱም ወንጌል መሆኑ የሚያበክር ወንጌልን በዕለታዊ ሕይወት መኖር የሚል ነው። ቅዱስ አባታችንም ይኸንኑ መርህ በማድረግ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ጥልቅ ውይይት እርሱም ወንጌላዊ እውነት በሰው ልጅ ሕይወት እንዴት ቅርጽ መያዝ እንደሚገባው ያስተምራሉ።

ልይት ሲባል ወንጌላዊ ሕይወት በሰው ልጅ ሕይወት ባጠቃላይ በኅልውና ውስጥ እንዴት እንደሚሰገው ማስተዋል የሚል ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ብዙውን ጊዜ በተለያየ ምክንያት የተለየውን የተነጠለውን በገዛ እራሱ ግድፈት ወይም በሌሎች ምክያን የራቀው የተለየውን ሁሉ ማስተናገድ የሚለው ወንጌላዊ ትምህርት ሲያስተጋቡ ነው የሚሰማው። ምክንይቱን ቤተ ክርስቲያን እናት ነች። ሁሉንም ልጆችዋ የምታስታስተናግድ እናት ነችና።

ቤተሰብአዊ ሕይወት ሁሌ በጎዞ ላይ ነው፡ ቤተ ክርስቲያን እናት ነች ሲባል ነጻነት የምትገታ ሰውን እንደ ግዛትዋ የምትቆጣጠር ፈላጭ ቆራጭ እናት አይደለችም እንዲህ ሲባል ለልጆችዋ እድገት የበሰለ ነጻነት የምታስብ መሆንዋ ነው የሚያረጋግጠው፡ ከዚህ ጥልቅ ሃሳብ በመንደርደርም የተፋቱ ቃል ኪዳን ያፈረሱ ቅዱስ ቁርባን ይፈቀድ አይፈቀደ የሚለው አነጋገር ትርጉም የለውም። ቅዱስ አባታችን ይኸንን በማስተዋል ነው የእያንዳንዱ የተፋታው ጉዳይ በልይት አማካኝነት እንደየ ተጨባጭ የፍቹ ምክንያት በማስተዋል ምላሽ የሚሰጡበት በብፁዓን ጳጳሳቶቻቸው ተምርተው ጉድዩን ቀርበው የሚያጤኑ መጋግብያን ማለት እረኞች ናቸው የሚል ነው፡ ያንን እግዚአብሔር ሁሉም እንዲድኑ ነው የሚለው ቤተ ክርሲያን በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አማካኝነት ደጋግማ ያበከረቸው ሥልጣናዊ ትምህርት የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ትምህርት በመከተል እንዴት እግብር ላይ መዋል እንዳለበት የሚመራ ሐዋርያዊ ምዕዳን ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.