2016-04-08 16:57:00

ሐዋርያዊ ምዕዳን Amoris laetitia-የፍቅር ሐሴት


በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እንዲመክር የተጠራው ልዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስና ቀጥሎ እ.ኤ.አ. በዚያኑ ርእስ ዙሪያ ቀዳሚው ሲኖዶስ ያቀረበው ሃሳብ መሠረት በማድረግ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲወያይ ዳግም የጠሩት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት መደበኛው ሲኖዶስ ያጸደቀው የማጠቃለያ ሰነድ የሚጨመር ካለ ጭመረው የሚታረም ካለም አርመው ካልሆነም በውሳኔ መሥረት የተለየየም ሊሆን ይችላል ለውሳኔ ቅዱስ ጴጥሮስ ውሳኔ ከተረከበ በኋላ ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሲኖዶሶቹ የተውያየበት ርእስ ዙሪያ Amoris laetitia-የፍቅር ሐሴት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ የበቃው ሲሆን፡ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ከውጭና ከውስጥ የመጡት ለተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ልኡክነታቸው በቅድስት መንበር ለሆኑት ጋዜጠኞች የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በመሩት  ዓውደ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተሰጠበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ሁለት ሲኖዶሶች በጋራ የመጓዝ ደጋፍያን

ሲኖዶስ የሚል ቃል አብሮ መጓዝ የሚል ትርጓሜ ያለው ሲሆን። ይኸው የተካሄዱት ሁለቱ አድካሚሚያን ሲኖዶሶች በተከተለው የጋራ የውይይት ጉዞ መሠረት ያረቀቀው የፍጻሜ ሰነድ በጥልቀት የመረመሩ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የፍቅር ሐሴት በሚል ርእስ ሥር ቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የምታስተላልፈው ሥልጣናዊ ትምህርት የአዘል የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ይፋ ሆኗል።

ቤተሰብ በጨለመው ዓለም ብርሃን መሆኑ የሚገልጥ የመጀመሪያው ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በወቅታዊው ዓለም ይዘት የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በሚል ርእስ ሥር ደግሞ ቀጥሎም እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በቤተ ክርስቲያንና በወቅታዊው ዓለም ውስጥ የቤተሰብ ጥሪና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ የተደገላቸው በተለያዩ የሥነ ቤተ ክርስቲያን የምርምር ዘርፍ ምሁራን ካህናት ገዳማውያን ደናግል አንዳንድ ባለ ትዳሮችና አንዳንድ የሥነ ቤተሰብ ሊቃውንት ዓለማውያን እንዲሁም የሌሎች ኃይማኖቶች ተወካዮች በታዛቢነት በማሳተፍ ለአምስት ሳምንታት ተካሂዷል።

በነጻነት ሃሳብ የሚግለጥበት ጉባኤ

እንደሚታወሰውም የመጀመሪያው የ 2014 ዓ.ም. ሲኖዶስ ከመካሄዱ ቀደም ተብሎ የሲኖዶሱ የማካሄጃ ሰነድ ለማጠናቀር በሚል ዓላማ ስለ ቤተሰብና ስለ ምሥጢተ ተክሊል በወንድና በሴት መካከል የሚጸናው የማይሻር ምሥጢር ነው የሚል መሠረታዊ ትምህርት ጀርባ በማድረግ በዚሁ ርእስ ዙሪያ በዓለም ወደ ሚገኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን የመጠይቅ ሰነድ ተልኰ የተሰበሰበው ሃሳብና ጥያቄ አንድ ወጥ በማስያዝ እንደ ቀደም ተከተሉ ተደርሶ ሲኖዶሱ ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር በነጻነት ሃስብ የሚገለጥበት ጉባኢያዊ ሂደት በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ በመከተል በዓለም የታዩትን የሚከሰቱትን ያንድ ኅብረተሰብ የባህሎች መለዋወጡ ሂደት ሁሉ ግምት በመስጠት በቀጥታ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ገጥሞ ተገቢ መልስ የተሰጠበት መሆኑ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ ኦንዳርዛ ገልጧል።

የቆሰሉ ቤተሰቦች

ሲኖዶሱ የቆሰሉ ቤተሰቦች ጉዳይ የመከረ ሆኖ እያለ የዓለም የመገናኛ ብዙኃን በጠቅላላ ለማለት ይቻላል፡ ቃል ኪዳን ላፈረሱ ተፋተው ዳግም ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ትዳር መሥርተው ለሚኖሩ የቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ማለትም ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ መፍቀድ አለ መፍቀድ በሚል ጥያቄ ሥር አጣበው በመመልከት በዚሁ ርእስ ዙሪያ የሚመክር ሲኖዶስ እንደሆነ አድርገው ሲተነትኑት ታይቷል፡ ሆኖም ቤተ ክርስቲያን በተካሄዱት ሲኖዶሶች አማካኝነ ባስቸጋሪ ሁነት የሚገኙት ቤተሰቦች ሁሉ የቆሰሉት ቤተሰቦች በሚል መለያ በመግለጥ በዚህ ብቻ ሳትታጠር በዓለም የቤተሰብ ውበትን ውህበት በሚመሰክሩ ተጨባጭ ሁነቶች በማብራራት የአያቶች የሕጻናት የህሙማን ቤተሰብ ላደጋ የሚያጋጡ አክራሪነት ግለኝነት ስግብግብነትና ከሁለት ዓይነት ባርህያዊ የጾታ መለያ ውጭ ሌላ ዓይነት ጾታ አለ የሚል አዲሱ የሥነ ጾታ ትምህርት፡ ሥራ አጥነት ስደተኞችና ተፈናቃዮች ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ማቀብና ማክበር የሚለው የሕይወት ባህል የሚመለከቱ ርእሰ ጉዳዮች ሁሉ በስፋት ተወያይቷል። ቤተ ክርስቲያን የቤተሰብ ማኅበረሰብ በማለት ሲኖዶሱ እንደገለጣት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተሰመረበትም የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አያይዘው፥

ወንጌል ሌላውን ለመጉዳት የሚወረወር ሙት ድንጋይ አይደለም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዳሉትም የተካሄዱት ሲኖዶሶች ቤተሰብ ለሚያጋጥመው ምንናውም ዓይነት ተጋርጦዎች መልስ የሌለው ቢሆንም ተጋርጦዎቹን በእምነት ዓይነት እንዲታዩ በማድረግ አለ ፍርሃትና አንገትን ካለ መቅበር ተውያይቶባቸዋል፡ ስለዚህ በተካሄዱት ሲኖዶሶች አማካኝነትም የቤተ ክርስቲያን ሕያውነት ተመስክረዋል። ቤተ ክርስቲያን በጋለ ስሜት የምትወያይ እንጂ አይ እጄን እላቆሽሽ አትልም። ይኽ ደግሞ አብራ ከሕዝብ ከማኅበረሰብና ከቤተሰብ ጋር በወቅታዊው ዓለም የምትጓዝ መሆንዋ የመሰከረ ሲኖንዶስ መሆኑ በደረሱት የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ በማብራራት ወንጌል ለቤተ ክርስቲያን ማለቂያ ለሌለው ዘለዓለማዊ ኅዳሴ መሠረትና ምንጭ ነው። ስለዚህ ወንጌል ሌላውን ለመምታት ለማድማት የሚወረወር ሙት ድንጋይ አይደለም። ወንጌል ለቤተ ክርስትያን የሕይወት ምንጭ ነው። ይኽ ሲባል ደግሞ ወንጌል እነዚያ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጀርባ የሚደበቁ የተዘጉ ልቦች መልካም እሳቢነት በሚል ሽፋን የሚሸሸጉትን በሙሴ ስልጣናዊ ወንበር በመቀመጥ ለመፍረድ የሚሹትን እጅግ ከባድ የሆነው ቤተሰብን የሚያቆስል ጥያቄና ሁነት በገረፍ ገረፍ አለ ምንም ኃላፊነት በመመልከት ለመፍረድ የሚያገለግል መሣሪያ እንዳልሆነም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን እንዳመለከቱት ኦንዳርዛ ገልጠዋል።

የእግዚብሔር ፍላጎት ሌላ ነገር ሳይሆን የሁሉም ድኅነት ነው

የተካሄዱት ሲኖዶሶች ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያወጁት ቅዱስ የምኅረ ዓመት በሳቸው አማካኝነት አርቆ ያስተዋለ እንደነበርም ሲታወቅ። በምንም ተአምር በተዛማጅ ባህል ላይ ሳይወደቅ በሙሉ ልብ በሙላትና በብርታት ያንን ሰብኣዊው ስሌት ተሻግረን የሁሉም ድኅነት ከሚመኘው የእግዚአብሔር ደግነትና መኅሪነትት ጋር ለመገናኘት ጥረት የተደረገባቸው መሆኑ ቅዱነታቸው በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ይፋ አድርገዋል።

እውነተኛው የቤተ ክርስትያን አንቀጸ ትምህርት የሚከላከል ሲሆን ይህ ማለት ደግሞ ሕገ ቃሉ ሳይሆን መንፈሱን የሚከላከል መሆኑ ለማስገንዘብ ነው፡ የቤተ ክርስቲያን ሥርወ ትምህርትና ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ በሚመለከት ጉዞ ብዙ ፈተና አጋጥሟል ማጋጠሙም አይቀርም፡ በሕግ ውስጥ በሕጎች ቃል ላይ ገዛ እራስ ለመዝጋት የሚሹ የባህል አክራሪያንንና እንዲሁም ሁሉ መቀየር አለበት የሚሉት ነጻዊነታውያን በመጥቀስ ለዚሁ ጉዳይ መጀመሪያ ቁስል ማዳን በሚል አነጋግር መልስ ሰጥትዉበታል፡ ሲኖዶሱ የእውነተኛው የቤተ ክርስቲያን ሥርወ ትምህርት ተሟጋችና ጠባቂ ተክለ ሰውነት በስፋት ገጦልናል። ማን መሆኑ አሳይቶናል፡ ስለዚህ ሕግንና ቃልን የሙጥኝ የሚል ሳይሆን ቃሉና ሕጉ ያጸናው መንፈስ የሚከተሉ መሆናቸው ከሲኖዶሱ ለመረዳት እንችላለን። ትኵረት የሚደረግበት ቃልና ሕግ ለቀመርና ለአስተሳስሰብ ሳይሆን ትኩረት ሊያገኝ የሚገባው ሰው ነው፡ በሌላው አነጋገ መስተዋልና መኖር የሚገባው ሁሉን በነጻ የሚያፈቅር የእግዚአብሔር ፍቅርና መህረቱ መሆኑ ለማበከር ነው፡ እንዲህ ሲባል ቀመር ያለው ክብር ለማሳነስ ሳይሆን መለኰታዊ ሕግ ሥርዓትና ትእዛዛት አስፈላጊዎ መሆናቸው ካለ መዘንጋት የእግዚአብሔር ታላቅነቱ እኛን በብቃታችን ሳይሆን በምኅረቱ በዋህነቱ የሚመለከተን መሆኑ ለማስገንዘብና፡ ማንም ብቁ በመሆኑ እንዳልዳነ ቅዱስ አባታንች ይኸንን ሃሳብ በስፋት በሐዋርያዊው ምዕዳኑ ኣማካኝነት እንዳብራሩትም ኦንዳርዛ ገልጠዋል።

የቤተ ክርስቲያን በሮች ክፍት ናቸው

ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ ውይይት ያካሄዱት ሲኖዶሶች ቅዱስ አባታችን እንደሚሉት ቤተ ክርስቲያን አንድ በመስተዋት በተገነባ ሕንፃ ላይ ወጥታ ሰብአዊ ፍጥረት ላይ ለመፍረድ በሩቁ የምትመለከት ሳትሆን እጅጌዋን ሰብሰባ ጎንበስ ብላ የሰው ልጅ ቁስል ቅዱስ ፈዋሹን ዘይት በማፈሰስ የምታብስ እውነት መንገድና ሕይወት የሆነውን የምታሳውቅ ነች። ለሙሽራዋና ለአንቀጸ እምነት ታማኝ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሲባል ባመንዝራዎች በመጸብሓንና ቀራጮች ማእድ ዙሪያ ለመገኘት የማትፈራ ለጻድቃን ወይንም ፍጹማን ነን ለሚሉት ብቻ ሳይሆን ለድኾች ለሚጸጸቱት ክፍት የሆነ በር ያላት ቤተ ክርስቲያን ማለት መሆኑ ቅዱስ አባታችን በሐዋያዊው ምዕዳን ያመለከቱት ሃሳብ ያካተተ ሐዋርያዊ ምዕዳን መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ኦንዳርዛ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.