2016-04-04 16:26:00

የነፍሴ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ኮቲየር የቀብር ሥነ ሥርዓት


እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓርብ ሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በ 93 ዓመት እድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቤተ ጳጳስ የቲዮሎጊያ ሊቅ በመሆን ለአረዥም ዓመታ ያገለገሉ የስዊዘርላንድ ተወላጅ  የበነዲክታውያን ገዳም አባል ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ ማሪየ ማርቲን ኮቲየር የቀብር ሥነ ሥርዓት የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ በመሩት የፍትኃት ቅዳሴ መፈጸሙ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል ሶዳኖ ፍትኃተ ቅዳሴውን መርተው ባሰሙ ስብከት፥ ነፍሴ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ኮቲየር በነበራቸው የቲዮሎጊያ ሊቅነት የክርስትና እምነት እጹብ ዘማሪ እግዚአብሔር በሁሉም እንዲታወቅ ያገለገሉ የስነ ቅዱስ ቶማስ ቲዮሎጊያ ሊቅ ታሪክና ስነ ምርምር በቲዮሎጊያ ዓይን በጥልቀት በማጤን በዚሁ ዘርፍ አቢይ የቲዮሎጊያ ሃብት ያወረሱ በማለት እንደገለጡዋቸው የጠቆመው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የኃዘን መግለጫ መልእክት እኚህ የስዊዘርላንድ ተወላጅ የቤተ ክርስቲያንና የሕዝበ እግዚአብሔር አገልጋይ በእምነት ብርቱ በአባትነት መንፈስ ለሁሉም ቅርብ በመሆን የቲዮሎጊያና የሥነ ቤተ ክርስቲያን ሊቅነታችውን በነበራቸው እውቀት ብቻ ሳይሆን ቲዮልጊያን ጉልበትን አጥፎ በመኖር ጭምር የመሰከሩ ሊቅነታቸው ለቤተ ክርስቲያን ያዋሉ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካለ መታከት ያገለገሉ መሆናቸው በማስታወስ። ታማኝ ለእምነት ታማኝ ለቤተ ክርስቲያን በማለት እንደገለጧቸውም ጠቅሶ በብፁዕ ካርዲናል ኮቲየር ዕረፍት ምክንያት የካርዲናሎች ጉባኤ ብዛት 116 የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የመረጥ መብት ካላቸው ጋር በጠቅላላ ወደ 215 መውረዱንም ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.