2016-04-01 16:01:00

ምኅረት ርእስ ዙሪያ የሚመክር ኤውሮጳዊ አቀፍ ጉባኤ በሮማ


ሐዋርያዊ የምኅረት ጉባኤ አዘጋጅነት ሮማ በቅዱስ አንድረያ ዘ ቫለ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁትና የተገባው የምኅረት ዓመት ርእስ ዙሪያ የተለያዩ የሥነ ቤተ ክርስቲያን የቲዮሎጊያ የሥነ መጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት አስተምህሮ የሚያቀርቡበት እ.ኤ.አ. እስከ ፊታችን ሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቀው ኤውሮጳዊ አቀፍ ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2016 ዓ.ም. የጉባኤው ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ክሪስቶፍ ሾንበርን ባስደመጡት ንግግር በይፋ ስለ ተከፈተው ዓውደ ጉባኤ በማስመልከት የምኅረት ሓዋርያዊ ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ክቡር አባ ፓትሪሰ ቾቾሊስኪይ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ በአልጀሪያ የተገደሉት አባ ክርስቲያን ደ ቸርገ ሁላችን በዚያ መለኰታዊ ምኅረት ጥማችንን ብንቆርጥና የተበቃይነት ግፊት ብናገል የምኖርበት ዓለም ከምድረ በዳነት በተላቀቀ ነበር ያሉትን ቃል አስታውሰው፡ ለእኛ ክርስቲያኖች ብቸኛው አማካያችንንና ፍጹም አማላጃችን ኢየሱስ ነው፡ በደሙ የተዋጀን ነን፡ ከእርሱ ውጭ ሌላ ምኅረት የለም ቢሆንም ቅሉ ምኅረትን የሚወስን ማንም የለም። ስለዚህ የምኅረት አፍቃሪያንና የምኅረት ፍቅር ያላቸው መሆን ይጠበቅብናል፡ ምኅረትን የሚያፈቅር መኃሪ ይሆናል ብለዋል።

አቢዩ ተአምር በማናዘዣ ቦታ የሚከወን ምኅረት መሆኑ ቅዱስ ዳርስ በሕይወቱና በቃሉ አስተምሮናል። እውነትም ነው፡ ምክንያቱም ምኅረት ውስጣዊ ለውጥ የሚያቀዳጅ ጸጋ የሚለገስበት ስፍራ ነውና። ባንድ ወቅት ይላሉ አባ ቾቾሊስኪይ በኪጋሊ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሁሉም የሩዋንዳ ዜጎች ለእርቅ እንዲጠመዱ ጥሪ በማቅረብ ሁሉም ወደ ንስሃ እንዲቀርብ በማለት በመናዘዝ ከጌታ ምኅረትን በማገኘት ከወንዱም ከገዛ እራስና ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ ያቀረበቸው ጥሪ ያስገኘው ማሕበራዊና ሰብአዊ ህዳሴ አስታውሰው፡ ስለዚ ምኅረትና እርቅ ኅዳሴ ያጎናጽፋሉ። ኅዳሴ ከልብ የሚጀምር ነው ካሉ በኋላ ይኽ በመካሄድ ላይ ያለው ኤውሮጳዊ አቀፍ ዓውደ ጉባኤ የኤውሮጳ ታሪክ በምኅረት ሥር በማንበብ ቲዮሎጊያዊ ትርጉሙን በማብራራት የምኅረት በኤውሮጳና ለኤውሮጳ ያለው መልእክት የሚገለጥበት መሆኑ ገልጠው። ቅዱስ ዓመት ልክ እንደተጠናቀቀም እ.ኤ.አ. ከጥር 16 ቀን እስከ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ደግሞ ዓለም አቀፍ የምኅረት ዓውደ ጉባኤ በማኒላ በምኅረት ሐዋርያዊ ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሾንቦርንና የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካዲናል ታግለ ተመርቶ እንደሚካሂድ በዚሁ አጋጣሚ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።     








All the contents on this site are copyrighted ©.