Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ የአለም ዜናዎች

በመጋቢት 27.2016 የፋሲካ በዓል በጦርነት በወደመችው እና ክርስቲያኖች በቁጥር አናሳ በሆኑባት አሌፖ ከ5 ዓመት ቡኋላ ለመጀምሪያ ጊዜ በድምቀት ተከበረ።

“ክርስቶስ ሞትን ድል ባደረገበት በዛሬው ዕለት ክርስቲያኖች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ህብረት ለማሳያት ወደ ቤተ ክርስቲያን መተኋል"። - AFP

31/03/2016 11:51

ባለፉት 5 ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት እየማቀቀች በምትገኘው ሶሪያ የምገኙ ክርስቲያኖች፣ በተለይም ደግሞ እስላማዊ መንግሥት እመሰርታለው በምለው ISIS በተባለው የአሸባሪዎች ቡድን ቁጥጥር ስር በምገኙት ግዛቶች የምገኙ ክርስቲያኖች፣ ከፍተኛ የሆነ ስደት እና መከራ እየደረሰባቸው እንደ ምገኝ የምታወቅ ስሆን በተለይም በቅርቡ ከእዝህ አሸባሪ ቡድን ስር ነጻ በውጣችው አሌፖ ክርስቲያኖች የፋሲካን በዓልን በታላቅ ደስታ ማከበራቸው ተገለጸ።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 27. 2016 በተከበረው የፋሲካ በዓል ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገረ ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ መንፈሳዊ በዓላትን አስመልክቶ በምያስተላልፉት “Urbi et Orbi” በአማርኛው ለከተማው (ለሮም) እና ለመላው ዓለም  በተሰኘው ልማዳዊ  ነገር ግን ወቅታዊ በሆነው  መልዕክታቸው “የዓለማችን ቁስል” በማለት የገለጹትን በዓለም ዙሪያ የምታየውን በአካል እና በመንፈስ መከራ የምሰቃዩትን ሰዎች ትኩረት ባደረገው መልዕክታቸው በተለይም ደግሞ  ከአምስት ዓመታት በፊት የተጀመረው እና የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው፣ ብዙዎችን ደግሞ ለስደት የዳረገው፣ አውዳሚውን የሶርያን ጦርነት ማውገዛቸው የምታወቅ ስሆን “ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ተነስቱኋል፣ ከሞት በመነሳቱም የጥልን ግድግዳ አፍርሱኋል፣ ሕይወት ሞትን አሸንፉኋል፣ ብርሃን ጨላማን አጥፍቱኋል” ማለታቸው እና በተለያየ መጥፎ የኑሮ ሁኔታ የምገኙ ክርስቲያኖች ተስፋ እንድይቆርጡ ማሳሰባቸው ይታወቃል።

የፋሲካ በዓልን በጦርነት በፈራረስችው የሶሪያ ከተማ  አሌፖ የምገኙ ክርስቲያኖች ምንም እንኳኋን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብሆኑም ይህንን ችግር በመቋቋም ከሞት በተነሳው ኢየሱስ ላይ ተስፋቸውን በመጣል በፍርስራሽ መኋል ሆነው ስርዓተ- ቅድሴ መከታተላቸው ታውቁኋል።

የኢየሱሳዊያን ማህበር ካህን የሆኑት አባ ጋሳን ሳሆይ እንደገለጹት “ከአምስት ዓመታት ቡኋላ ይህንን ስርዓተ ቅዳሴ ለማድረግ በመብቃታችን ከፍተኛ የሆነ ድስታ ተስምቶናል” ብለው “አሌፖ እየተረጋጋች በመሆኗ ከፍተኛ የሆነ ተስፋ በውስጣችን የጫረ ዕለት እንደ ነበረ” ጨምረው ግልጸኋል።

“በእዝህ ክርስቶስ ሞትን ድል ባደረገበት ዕለት ክርስቲያኖች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ህብረት ለማሳያት እና ተስፋቸውን ለማደስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄዳቸው፣ በቁጥር አናሳ የሆኑ ክርስቲያኖች አሁንም በሕይወት መኖራቸውን የመሰከረ ድርጊት እንደ ነበረ ገልጸው፣ በከፍተኛ መከራ ውስጥ በነበሩበትም ወቅት ሁሉ ለእምነታቸው ታማኝ ሆነው እስከ ዛሬ መቆየታቸው ታላቅ የሕይወት ምስክርነት መሆኑንም ገልጸዋል።

የምግብ እና የውሃ ችግር በከፍተኛ መልኩ በአሌፖ የምታይ ብሆንም የክስቶስ ከሙታን መነሳት ግን ተስፋ ሳይቆርጡ መጭውን ጊዜ በተስፋ እንዲጠባበቁ ብርታት እንደሆናቸው ጨምረው የገለጹት አባ ጋሳን ሳሆይ በተለይም ደግሞ በህማማት ሳማንት ክርስቲያኖች ምንም መከራ ሳይበግራቸው ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ዝግጅት ማድረጋቸው እና እግዚአብሔር ስለ አደርገላቸው ጥበቃ፣ ተዓምር፣ መንፈሳዊ በረከት እና ፀጋ ምስጋናን  ማቅረባቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ አስከፊ ወቅት ተወግዶ ሰላም እና ብልጽግና ይመጣ ዘንድ የዓለም ማህበርሰብ የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበው በተለይም ደግሞ ተስፍችን ከሙታን በተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በመሆኑ ሳንሰልች ለሰላም ልንፀልይ ይገባል ብለው ንግግራቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

31/03/2016 11:51