2016-03-25 16:13:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የሚገፉና የሚሳደዱ ማሕበረ ክርስቲያን እንዳይረሱ


ለሚሰቃዩት አቢያተ ክርስቲያን ረጅ ማኅበር ቅርንጫፍ በኢጣሊያ አስተዳዳሪ አለሳንድሮ ሞንተዶ በኢጣኢያ የቨቲሚሊያና ሳን ረሞ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ሱወታ እንዲሁም የቦሎኛ ርእሰ ሰበካ ካህን አባ ማሲሞ ፋብሪና የካፕሪ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ካቪና በኢራቅ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጋልጠው ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ለሚዳረጉት ኢራቃውያን በኩርድስታን ክልል የሚኖሩትን ለማበረታታትና የሰብአዊ ደገፍ ለማቅረብ በሚል መርሃ ግብር መሠረት እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 1 ቀን እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ የሰሙት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለብፁዕ አቡነ ካቪና ስልክ በመደወል ለስደት የተጋለጠው ማኅበረ ክርስቲያን ለከፋ አደጋ ለተጋለጠው ኢራቃዊ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ቅርበትና ጸሎት እንዲያረጋግጡላቸውና በዚያ ክልል ለስደት የተጋለጠችው ቤተ ክርስቲያንና ማኅበረ ክርስቲያን መርጃ የሚውል የገንዘብ እርዳታ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ለስደትና ለመፈናቀል ለሞት አደጋ የተጋለጠው የኢራቅ ማኅበረ ክርስቲያን አደራ እንዳይረሳ ያሉት ቅዱስ አባታችን የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰየመው ዓለም አቀፍ ማኅበር ለዚያች ተሳዳጅዋ ቤተ ክርስቲያን እየሰጠው ያለውን ድጋፍና ትብብር ቅዱስ አባታችን አመስግነው ለዚያ ሕዝብ ቅርብ እንሁን አደራ። የሰው ልጅ የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት የሆነው የኃይማኖት ነጻነት እንዲከበር ጥሪም አቅርበው፡ በስቃይና በመከራ በስደት ክርስትናቸውን የሚኖሩ ማኅበረ ክርስቲያን ለመላ ቤተ ክርስቲያንና ማኅበረ ክርስቲያን በዚህ የፋሲካ ምስጢር እንድናስተውል ለሚያደርግ ሕይወት አብነት ናቸው። ከዚህ ጥልቅ ምሥጢርም ለአንድ አዲስ ሰብኣዊነት ክዋኔ የሚደገፍ ኃይልና ብርሃን እንጎናጸፋለን እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ተራ ግብረ ሠናይ ማቅረብ ሳይሆን ለአካለ ክርስቶስ ቅርብ መሆንን እንመስክር

ምኅረት ጉልበታችንን አጠፍ በማድረግ ተንበርክከን የወንድሞቻችንና የእህቶቻችን እንባ ለማበስ የደረሰባቸው አካላዊና ግብረ ገባዊ ጉዳት ልንፈውስና ልናጽናናቸው ይጠራናል፡ ስለዚህ ለወንድሞቻችን የምናቀርበው ትብብርና ድጋፍ ተራ ግብረ ሠናይ ሳይሆን ለአካለ ክርቶስ ቅርብ የመሆን ተግባር ምስክር መሆን አለበት። ለተጎዳው የምናቀርበው ድጋፍ ሁሉ ለአካለ ክርስቶስ ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያዞ፥ የዚያ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን ረጅ ማኅበር ልኡካን በአንካዋ ክልል ከማኅበረ ክርስቲያንና በኤርበል የከለዳዊ ሥርዓት ከምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባሺር ማቲ ዋርዳን ጋር በመገናኘት በዚያ ጳጳሳዊ ዓለም አቀፍ ረጅ ማኅበር መሥራች አባ ወአንፍራይድ ቫን ስትራተን ስም የሚጠራው 150 የተፈናቃዮች መኖሪያ ቤት ያቀፈ መንደር ሌላውም 7 ሺሕ ተማሪዎች የሚያስተናግድ ትምህርት ቤት በማኅበሩ እርዳታ የተገነባውን መርቀው በመቀጠልም በሞሱል የሶሪያ ሥርዓት ከምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አብረው ከምእመኖቻቸው ጋር ገዛ እርሱን እስላማዊ አገር ብሎ በሚጠራው አሸባሪው ታጣቂው ኃይል አሳዳጅነትና ክልሉም በአሸባሪው ኃይል በመያዙ ምክንያት ተገደው ሞሱልን ለቀው በኤርበል በስደት ከሚግኙት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሙቸን ጋር እንደሚገናኙ ገልጦ፥ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን ረጅ ማኅበር እ.ኤ.አ ከ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በአቢይ ጾም ወቅት ለኢራቅ የእርዳታ አቅርቦት መርሃ ግብር እያከናወነ ሲሆን እስካሁን ድረስ ለግብረ ሠናዩ ማስፈጸሚያ 15 ሚሊዮን ከግማሽ ኤውሮ ሲያቀርብ በአሁኑ ወቅት የኢጣሊያው ጨንፈር ለ 250 ሺሕ የኢራቅ ስደተኞች ምእመናን የሚውል እርዳታ ለማሰባሰብ ከካፕሪ ከቨንቲሚሊያና ሳን ሬሞ ሰበካ ጋ በመተባበር የሚሰደዱትን ማኅበረ ክርስትያን እንርዳ በሚል መርሆ ሥር የተለያዩ የቅስቀሳ መርሃ ግብሮች እያካሄደ መሆኑ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.