2016-03-16 16:41:00

ቤኒን፥ መሠረት የሌለው ዜና


በአገረ ቤኒን እ.አ.አ. መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ተካሂዶ በነበረው የርእሰ ብሔር ምርጫ ተቀራራቢ ድምጽ ያገኙትን ወዳሪዎች መካከል አሸናፊውን ለመለየት እ.ኤ.አ. መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ዳግመ ምርጫ እንደሚካሄድ ፊደስ የዜና አገልግሎት ገልጦ፥ አንድ የአገሪቱ ጋዜጣ የበኒን ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት ምእመናን ወዳሪው የፖለቲካ አካል ለርእሰ ብሔር እጩ ሊኦነል ዚንሱን እንዲመርጡ ቅስቀሳ እያካሂደ ነው በማለት ያወጣው ዜና ብፁዓን ጳጳሳቱ በምክር ቤቱ ሊቀመንበር የኮቶኑ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አኖቶይነ ጋንየ ፊርማ በተኖረበት ባስተላለፉት የጋራ መልእክት አስተባብለው፡ በቤኒን የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የራሷ ተመራጭ የላትም፡ የፖለቲካ መዋቅርም አይደለምችም እንዳሉ ያመለክታል።

ቤተ ክርስቲያን ኅሊና የምታንጽ ሕዝብ እንደ የኅሊናው ድምጽ ይስጥ ነው የምትለው

የቤኒን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የምክር ቤቱን መልእክት በይፋ ለሕዝብ በማንበብ፥ ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ያንን ምረጡ ሳትል ከማንም ፖለቲካ ጋር ሳትቦድን የሕዝብ ሕሊና በማነጽ የአገርና የሕዝብ ጥቅም እንዲቀድም የምታስገነዝብ ነች የሚል መልእክት አዘል ከምርጫው በፊት “ሕዝባዊ ምርጫ በእግዚአብሔር እይታ” በሚል ርእስ ሥር የተላለፈውን ሐዋርያዊ መልእክት ብፁዕ አቡነ ጋየ በማስታወስ የቤኒን ዜጎች በእግዚአብሔር ብርሃን ተመርተው እንደየ ሕሊናቸውና ለአገር ባላቸው ፍቅር ተደግፈው ድምጽ ይሰጡ ዘንድ ነው ቤተ ክርስቲያን ጥሪ ያቀረበቸው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎ አስታወቀ።

ርእሰ ብሔር የመሆን መመዘኛው ፈሪሃ እግዚአብሔር የማኅበራዊ ጉዳይ ለማኅበራዊ ጥቅም ባቀና መንገድ የማስተዳደር ብቃት የተካነ፡ መልካም አስተዳደር የሚያነቃቃ የአገረ ቤኒን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጠንቅቆ የሚያውቅና የሚተነትን በሳልና ምሁር አገር ወዳድ ሕግ እንዲከበር ሕጎችን በማክበር ረገድ አብነት ሆኖ የሚመራ የተሰኙት ሓሳቦች በርግጥ ቤተ ክርስቲያን ታስተጋባለች ነገር ግን ይኸንን ያንን ምረጡ ብላ እታውቅም እትልም የራሷ ተመራጭ የሌላት ነች ሊኖራትም አይችልም እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግልት ይፋ አደረገ።








All the contents on this site are copyrighted ©.