2016-02-13 10:47:00

ር.ሊ.ጳጳስ ፍራንችኮ 12ኛውንና የሓዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ ሜክሲኮ ጉዞ ጀመሩ።


ዛሬ ጥዋት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ለስድስት ቀን ያህል የምቆይ ታሪካዊ 12ኛ ሓዋሪያዊ ጉብኝትና ር.ሊ. ጳጳስ ሆነው ከተመረጡ ቡኋል የጎበኙዋቸው ሀገሮች በቁጥር 20ኛው ወደ ሆነችው ሜክስኮ ለመጓዝ እገረ መንገዳቸውን በኩባ ዋና ከተማ ሀቫና ለአንድ ቀን ያህል ጎራ በማለት ከሞስኮና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ከሆኑት ፓትርያርክ ኪሪሊ ጋር በግል በመገናኘትና ከዝያም ወደ ሜክሲኮ ለማቅናት ጉዞ መጀመራቸው ታውቋል።

ይህንን ጉብኝት ታሪካዊ የምያደርገው በሜክሲኮ የምያደርጉት የመጀመሪያው ጉብኝታቸው ሳይሆን ከሞስኩና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ኪሪሊ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከዝህ በፊት በታሪክ ተከስቶ በማይታውቅ ሁኔታ ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመንጋገር መወሰናቸውና ይህንንም እውን ለማድረግ ቀን ቆርጠው ለመገናኘትና ስለ ወደፊቱ በሁለቱ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያንት መካከል ልኖር ስለ ምገባው መልካም ግንኙነት ለመነጋገርና አንድ የጋራ የአቋም ወይም መግለጫ ለማውጣት  መወሰናቸው ነው እንግዲህ ታሪካዊ የምያደረው። ይህንን ታሪካዊ ጉብኝት አስመልክቶ የምነሱ ጥያቄዎች ይኖራሉ…

ለነዝህ ጥያቄዎች መልስ ይሆነብን ዘንድ የተለያዩ የዜና ምንጮችን በተለይም ዚነት እና ሴዶክ የረድዮ ቫቲካን የውስጥ የዜና ምንጭን በመጠቀምና በተለይም ደግሞ  በሩስያ “የቼርች ኢን ኒድ” ወይም (በስቃይ ወይም በስደት ላይ የምገኙ አብያተ ክርስትያናት የምረዳ ማህበር) አላፊ የሆኑ ፒተር ሄሜንክ የሰጡትን ማብራርያ ላይ ተንተተርሰን የምከተለውን ምላሽ አጠር ባለ መልኩ አጠናክረነዋል።

 

ለምንድነው እነዝህ ሁለት የበተክርስቲያን መሪዎች በዝህ በተጣበበ ጊዜ ለምገናኘት የውሰኑት? ምንድነው እርሱ ምክንያቱ? የሚለው ቀዳሚ ጥያቄ ነው።

ለዝህ ታሪካዊ ግንኙነት እንደ ዋንኛው ምክንያት የምቀመጠውና የምፈረጀው በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን የምታየው አስከፊውና ከመቸውም ጊዜ በላይ ደግሞ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ እየተስፋፋ የምገኘው በክርስትያኖች ላይ የምፈጸመው ስደትና መከራ ከፍተኛውን ስፍራ ይይዛል ምክንያቱም …ታሪካዊ የጸሎት ቤታችው እየወደመና መኖርያ ቤታቸው እየፈረሰ ለአስከፊ እልቂት እና ስደት እየተዳረጉ መሆናቸው ይታወቃል። በኢራቅ የሚገኙ ጥናትዊ ክርስትያኖች እና ቤተ መቅደሳቸው፣ በስሪያ የሚገኙ ክርስትያኖች እንደዚሁ…ለሞት እና ለስደት ተዳርገዋል..

ከወራት በፊት እንደ ምናስታውሰው በሊቢያ ክርስትያን በምሆናቸው ብቻ በአስከፊ እና በአስቃቂ ሁኔታ ሕይውታቸውን ያጡትን ከ30 በላይ ኢትዮጲያውያን እንደነበሩ ይታወሳል….ይህንን የመሳሰሉ በተለያዩ አካራሪ የሙስሊም ታጣቅዎችና በፖለቲካዊ አመለካከት ልዩነት ምክንያት እየደረሰ ያለውን ስደትና መከራ በጋራ እንዴት ከተቻለ ማስቆም ካልሆነ ደግሞ ለመቀንስ ወሳኝ ጊዜው አሁን በመሆኑ ቅድምያ የምያስፈልገው ጉዳይ በመሆኑ ነው።

ይህ ታሪካዊ ግንኙነት የራሻ ማህበረሰብ እና በጠቅላላው የወንድሞቻችን የኦርቶዶስ ቤተክርስትያን ምዕመናን ላይ ምን ዓይነት አስተያየት ወይም መልከታ ይፈጥራል ?

ከተለያዩ የሩስያ የዜና ተቋማት ለመረዳት እንደቻለው የብዙሀኑ ሕዝብ አስተያየት መልካም እንደሆነ ይገመታል.….እንድሁም በሩስያ የብዙሓን መገናኛ የሰሞንኛው ዋና ዜና ይህ ጉዳይ ነው…በተጨማሪም የሁለቱ አብያተ ክርስታያን መሪዎች በተመሳስይ ወቅት ስለ ግንኙነቱ አስፈላጊነት በብዙሀን መገናኛዎች በማስታወቃቸው ከፍተኛን ትኩረትን ስቦ ሰንብቱዋል። ከራሻ ውጭ ደግሞ የኮንስታንትኖፕል ፓትርያርክ የሆኑትና ሁል ጊዜም በሓይማኖቶች መካከል የምደረግውን ውይይት በቀዳምነት የምደግፉ ፓትርያርክ በርቴሎሜዎስ የህንን ታሪካዊ ግንኙነት በመካም ጎኑ እንደተመከቱትና እርካታም እንደትሰማቸው ለመረዳት ተችሏል።

በጠቅላላ የነዝህ ሁለቱ የበተክርስትያን መሪዎች ግንኙነት በአብዛኛው የሩስያ ማህበረሰብ እና በአንድ አንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መሪዎች ዘንድ በልካም ጎኑ እየተአየ መሆኑ እምርታን የምፈጥር ጉዳይ ተደርጎ እንደተወሰደ ያሳያል።

ከእነዝህ ሁለት የበተክርስቲያን መሪዎች ወይይት ቡኋላ የሁለቱን አብያተ ክርስትያናት ቀጣይ ግንኙነት ላይ ምን አይነት ለውጦች ወይም ተጽኖ ለውደፊቱ ልፈጥር ይችላል? የምሉት እና የመሳሰልት ትያቄዎች በአብዛኛው ነዝህ ወቅት እየተነሱ ይገኛሉ።

ለአስርተ አመታት በሁለቱ ታላላቅ አባያተ ክርስትያናት መካከል ስካሄዱ የቆዩ ውይይቶች እና ግንኙነቶችን ፍጻሜ መስጫ ጌዜ ወይም መደምደምያ ይሆናል ተብሎ ነው የምታሰበው። ምክንያቱ ባለፉት ጊዜያትም ሁለቱ አባያተ ክርስትያናት በጋር ድምጻቸውን ያሰሙበት ጊዜ እንደነብረ ይታወሳል።

ለምሳሌ በ2013 በመስከረም ወር ላይ ሁለቱም መሪዎች የሶርያን የሰላም እቅድ በመደገፍ በአንድነት ለዓለም ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወቃል። በዝያን ጊዜ ፓትርያርክ ክሪሊ የሰላም ጥረቱን አስመልክተው ለአመሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ደባዳቤ ስጽፉ ር.ሊ.ጳጳስ ፍራንቸኮ በበኩላቸው ደግሞ ለራሻው ፕሬዝደንት ቪላድሚር ፑቲን የሶሪያን ሰላም ጥረትን እንዲደግፉ የምያበረታታ ደብዳቤ መጻፋቸው ይታወሳል።

ስለዚህም አሁን የምደረገው ግንኙነት የሁለቱን አብያተ ክርስትያናት አንድነት የምያጠናክር እና በተለይም ስለ ዓለም ሰላም እና እድገት በጋር ድምጻቸውን እንድያሰሙ ከፍተኛ እገዛ እንድምያደርግ የታሰባል ።

እንግድህ ይህ ታሪካዊ ግንኙነት ለወደፊቱ ለምደርጉ ውይይቶች በር ከፋች እንደመሆኑና ለውደፊቱ በዓለማችን ለምፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ ለምስጠት ከፍተኛ የሆነ ጉልበት የምሰጣቸው በመሆኑ በተለይም በክርስትያኖች ላይ የምደረግውን አሬሜንያዊ ጭፍጨፋና ስደት በጋራ ለመከላከልና እንድሁም ደግሞ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጥያቄ እየሆነ የመጣውን ቤተሰብ ሁኔታ ማለትም በተመሳሳይ ጾታዎች መካከከል የምፈጸመውን ጋብቻ በጋር ለመዋጋት፣ አንድ የምያደራቸውን የክርስትና ህሴቶችን በጋራ ለዓለም ሕዝብ ለመመስከር አቅም የምፈጥሩበት አጋጣሚ እንድምሆን ይታሰባል።

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.