2016-02-10 15:19:00

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሐዋርያዊ መሥተዳድር መዋቅር ኅዳሴ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ቀን ወዲህ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እጅግ ያስፈልጋል በማለት ያነቃቁት ሐዋርያዊ የበላይ መዋቅሮች ኅዳሴ ለማረጋገጥ በዚሁ ተልእኮ ተባባሪዎች እንዲሆኗቸው እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. ታህሳስ ወር በ 9 ብፁዓን ካርዲናሎች ያቆሙት የህዳሴ ምክር ቤት ጉባኤ እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ያካሄደው 132ኛው ጠቅላይ ስብሰባውን እ.ኤ.አ. የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ማጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ ገልጠው፣ ስብሰባው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የብፁዓን ጳጳዊ ሲኖዶስ ቅዋሜ ዝክረ 50ኛውን ዓመት ምክንያት ያስደመጡት ስልጣናዊ ንግግር ርእሰ ጉዳይ በማድረግ መወያየቱ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው ያመልክታሉ።

አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱትም፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በተገኙበት የተካሄደው 132ኛው ጠቅላይ ስብሰባ አጭር እንደነበርና ብፁዕ ካርዲናል ጋርሲያ በህመም ምክንያት በስብሰባው አለ መገኘታቸውና ስብሰባው አጭርና በተፋጣኝ እንዲካሄድ ያስገደደውም በላቲን ሥርዓት የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓቢይ ጾም መግቢያ ሥነ ሥርዓትና በዚሁ እለት ቅዱስ አባታችን በዚህ በምህረት ዓመት ምክንያት ልኡካነ ምህረት ላይ ባተኰረ የሚሰጡት የዕለተ ረቡዕ ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መርሃ ግብር መሆኑ በማብራራት የተካሄደው ስብሰባ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ቅዋሜ ዝክረ 50ኛ ዓመት ምክንያት ያስደመጡት ሥልጣናዊ ንግግር ላይ እንዲያተኵር ያሻበት ምክንያትም በዚያ ሥልጣናዊ ንግግር ዘንድ ለመሠረተ ኅዳሴ ቤተ ክርስቲያን የሚሆን መሪ ቃል ያካተተ በመሆኑና ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም አራት ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች በዓለማውያን ምእመናን ቤተሰብና ሕይወት እንዲሁም የፍትህ ሰላምና የስደተኞች ጉዳይ በሚመለከቱ በሁለት ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች እንዲጠቃለሉ ለማድረግና ብሎም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊና የሥርዓተ አምልኮና ቅዱሳት ሚሥጥራት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ጉዳይ ሊኖረው የሚያፈልገው ህዳሴ ማእከል በማድረግ ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥ የሚያስፈልጉ አስተያየቶችን ለማጠናቀር መቻሉንም አባ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለማወቅ ተችለዋል።

ይኽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በማሳተፍ የተካሄደው በ9 ብፁዓን ካርዲናሎች የቆመው የኅዳሴ ምክር ቤት ስብሰባ በብፁዕ ካርዲናል ኦመልይ የሚመራው ላቅመ አዳድም ያልደረሱ ዜጎች ተንከባካቢ ድርገትና በብፁዕ ካርዲናል ፐል የሚመራው የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ በመጨረሻም የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ፍርድ ቤት መዋቅር ርእስ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ፣ በእያንዳንዱ ሰበካ ያለው የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ሚሥጥረ ተክሊል በሚመለከት ርእስ ጉዳይ የሚመለከተው ኅዳሴ እግብር ላይ እንዲያውል በሚያደርጉት ጥረት ድጋፍና ትብብር እንድሚያሻቸውም ስብሰባው አበክሮ፣ በመጨረሻም ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ቀጣዩን ስብሰባ  ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ በመያዝ መጠቃለሉ አባ ሎማርዲ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.