2016-02-10 15:29:00

ኢራቅ፦ ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ርእስ ዙሪያ የሚመክር ዓውደ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የኢራቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በኢራቅ ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለማረጋገጥ በሚል ርእስ ዙሪያ በመከረው ዓውደ ጉባኤ የአገሪቱ ክርስቲያን ማኅበርሰብ የዚህ ዓይነት ተደጋጋሚ ጉባኤ ከዚህ ቀደም መታየቱና የጋራ ሰላማዊ ኖሮ ለማረጋገጥ ይበጃሉ ተብለው እቅዶች የተወጠነበት ቢሆንም እግብር ላይ ሲውሉና እግብር ላይ እንዲውሉም በፖለቲካውና በመንግሥት ደርጃ አስፈላጊ ቅስቀሳም ሆነ መልካም ፈቃድ ባለ መታየት ለይስሙላ የሚካሄድና በኢራቅ ያለው የጎሳ የሃይማኖት ልዩነት ምክንያት ያደረገው ግጭት እየባሰ እንጂ ሲሻልና ሲያበቃለትም ያልታየ  የአገሪቱ ንእሱሳን ጎሳዎችና ውሁዳን ኃይማኖቶች ለከፋ አደጋ ተጋልጠው አገራቸው ለቀው እንዲወጡ የሚያስገድድ ሁኔታ አሁንም እየቀጠለ ነው በማለት የኢራቅ ማኅበረ ክርስቲያን አለ መሳተፉ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊስ ሳኮ የሰጡትን መግለጫ የጠቀሰ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

 

በኢራቅ የከለዳዊ ስርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ሳኮ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ መሳተፍና አለ መሳተፍ ሳይሆን እስካሁን ድረስ ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ዓውደ ጉባኤዎች ያስገኘው ውጤት አለ ወይ ብሎ መጠየቁ ይሻላል፣ ማኅበረ ክርስቲያን ያዚዶችና ማንደይ ብሄረሰቦች የተጋረጠባቸው አደጋና ስደት ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ስለዚህ የጋራ ኑሮ ለመደገፍ እየተባለ የሚካሄዱት ጉባኤዎች ለይስሙላ የሚከናወኑ ናቸው ሲሉ በአገሪቱ የቴለቪዥን ጣቢያ በኩል የሰጡት መግለጫ የጠቀሰ ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፦ በኢራቅ የከላዳዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በኢራቅ በውህዳን ኅብረተሰብና የውሁዳን ሃይማኖቶች ላይ የሚጣለው ጥቃትና የሚፈጸመው አድልዎ ድምጿን ከፍ በማድረግ ከሳለች፣ በተለያየ ዓለም አቀፍ መድረክ እየተገኘችም ስታስታውቅ ቆይታለች፣ ለሚመለከተው አካል ሁሉ አቤት ብላለች፣ በዚህ ብቻ ሳትታጠር ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመገናኘትም የአገርና የሕዝቦች እንድነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ መንገድ ለማፈላለግ የሚከፋፍለውን ሁሉ ወደ ጎን በማድረግ አንድ በሚያደርገውን ክብር ላይ የጸና መቀራረብና መደጋገፍ እውን እንዲሆን የሁሉም ትብብር ያለው አስፈላጊነት አበክራ ገልጣለች አሁንም እያቀረበች ትገኛለች። ሆኖም የሚገባው ቃልና የሚደረሰው የጋራ ውሳኔ እግብር ላይ ሲውል አልታየም እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.