2016-02-09 10:30:00

የቅዱስ ጲዮና የቅዱስ ሌሆፖልዶ ማንዲች ቅዱስ አጽምን በየቀኑ ከ10 ሺ ሰዎች በላይ እየተጎበኘ ይገኛል።


እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር ከየካቲት 5-11. 2016 የሁለት የሚስጢረ ንስሓ አፍቃሪ ቅዱሳን ቅዱስ አጽም፣  ቅዱስ የምሕረት አመትን አስመልክቶ ምዕመናንን ወደ ሚስጢረ ንስሓ ለመሳብ በማሰብ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዝልካ ለእይታ ክፍት መሆኑ በተከታታይ መዘገባችን ይታወቃል።

የነዝህን ታላቅ ቅዱሳን ማለትም የቅዱስ ጲዮና የቅዱስ ሌሆፖልዶ ማንዲች ቅዱስ አጽምን በመጎብኘት፣ የቅዱሳኑ መንፈሳዊ በረከትና ትሩፋትን ለምቋደስ በማሰብ ከተለያዩ የዓለም ክፍል ከተውጣጡ በየቀኑ ከ10 ሺ ሰዎች በላይ እየተጎበኘ ይገኛል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የምሕረት አመትን አስመልክቶ በተዘጋጀውና እንዚህ ሁለት ታልቅ የሚስጢረ ንስሓ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ቅዱሳን፣ ሓጥያተኝ በሓጥያቱ ተጸጽቶ በንስሓ ሓጥያቱን በማጠብ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ ከፈተኛ ጥረትና ድካም በማድርጋቸው ቤተ ክርስትያን ሁል ጊዜ ስትዘክራቸው እንደ ምትኖርና ምዕመናንም በዝህ ወሳኝ በሆነ መንፈሳዊ በረከትን አብዝቶ በምያስገኘው ሚስጢር ንሳሓን እንድያዘውትሩ አጋጣሚ የፈጠረ ዝግጅት ሆኖ እየቀጠል መሆኑ ታውቋዋል።

የቅዱስ ፒዮንና የቅዱስ ሌሆፖልዶ ማንድቺን ለመዘከር ለተገኙት ምዕመናንን ጋዜጠኛችን ማሪያና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት ለአንድ አንድ ምዕመናን ባቀረበችላቸው ጥያቄ መርደት እንደትቻለው በተለይም ራቅ ካለ ስፍራ ወደ እዝህ በመምጣት የሁለቱን ቅዱሳን ቅዱስ አጽም ለመጎብኘት ያስገደዳቸው ምክንያት ስገልጹ “እነዝህ ሁለት ቅዱሳን ለማየት ብዙ ወጪ አውጥተው ወደ ሮም ከተማ በመምጣት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ የተገኙበትን ምክንያት ስያብራሩ እነዝህ ሁለት ቅዱሳን በሕይወት ዘመናቸው ብዙ ሓጥያተኞችን ወደ እግዚአብሔር መንገድ የመለሱ በመሆናቸው መሆኑን ገልጽው የኢየሱስን ፍቅር ቀስ በቀስ በሕይወታችን እንድንለማመድ ያስተማሩን በመሆናቸው በሕይወታችን ከፍተኛ ቦታ ስለምንሰጣቸው ነው እዝህ የተገኘንው ብለዋል።

በአብዛኛው የወጣቶች ስብስብ የምታይበትና ከሮም ከተማ ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ እርቃ ከምትገኘው ካታንያ ረዥም ጉዞን በማድርግ የመጡ ምዕመናን ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዝሊካ የቅዱሳኑን ቅዱስ አጽም ለማየት የመጡበትን ምክንያት እንደገለጹት “እነዝህ ሁለት ቅዱሳን  እግዚአብሔር የምህረት አምላክ መሆኑን በሕይወታቸው የመሰከሩና ብዙ ምዕናንን ከተሳሳተ የሕይወት ጎዳና እንድመለሱ በማድርግ በትክክለኛውና በብርሃን በተሞላው ጎዳና እንዲመላለሱ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ በመሆናቸው፣ የእነርሱ ትሩፋት ለኛም እንድደርሰን በመፈለጋችን ነው ረዥም መንገድ ተጉዘን የመጣነው ብለዋል።

በተጨማሪም በዝህ በያዝነው የምሕረት አመት በንስሓ ወደ እግዚአብሔር መመለስ እንድንችል በነዝህ ሁለት ቅዱሳን አማልጅነት የእግዚአብሔር ፀጋ ልባችንን ይነካ ዘንድ ልንማጸንና ትሩፋታቸውን ጭምር ለመጠየቅ ጭምር ነው የመጣነው በማለት አሳባቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.