2016-02-05 15:41:00

የአባ ሳንቶሮ ሰማዕትነት ዝክረ 10ኛ ዓመት


የዛሬ 10 ዓመት በፊት የኢጣሊያ የሮማ ሰበካ ካህን የዚያ ፒዮስ 12ኛ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 21 ቀን 1957 ዓ.ም. ፊደይ ዶኑም የእምነት ጸጋ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት በምዕራቡ ዓለም የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ካህናት ዲያቆናት ዓለማውያን ምእመናን ከቁምስናዊ አጥርት ወጣ ብለው የወንጌላዊ ልኡካን እጥረት ባለበት ክልል እንዲሳተፉ ጥሪ የሚያቀርብ ዓዋዲ መልእክት መሠረት በማድረግ የሰበካ ካህናት በተልእኮ ወንጌል ወደ ተለያየ የዓለማችን ክልል ለሚልከው ማኅበር አባል በመሆን በቱርክ በትራብዞን ለምትገኘው ቅድስተ መርያም ቤተ ክርስቲያን ቆሞስ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት አባ አንድረያ ሳንቶሮ መጽሓፍ ቅዱስ እያነበቡ እያሉ የከፈሉት የደምስ ሰማዕትነት ዝክረ አስረኛ ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ የቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራኖ ባሲሊክ የሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ የመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ ማረጉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

የአባ ሳንቶሮ እህት ፕሮፈሰር ማዳለና ሳንቶሮ የወንድማቸው አባ ሳንቶሮ ዝክረ 10ኛ ዓመተ ሰማዕትነት ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ከወንድማቸው ጋር በቤተሰብ ውስጥ ይኖሩት የነበረው የአብሮ መኖር ሕይወት በማስታወስ ወንድማቸው ካህን ከሆኑ በኋላና ከደም ሰማዕትነት በኋላ ቢሆን ያልተቋረጠ እንዳውም እጅግ ከፍ ባለ ጥልቅ መንፈሳዊ የተካነ ሆኖ እየቀጠለ ነው። በእግዚአብሔር ቃል ጸኖት መኖር የሚል የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት ያደረገ ሕይወት የኖሩ አባ ሳንቶሮ ከዚህ ዓለም ቢለዩም የከፈሉት የደም ሰማዕትነት በመካከላችን እንዲኖሩ አድርጓቸዋል። የጌታ ቃል እያነበቡ እያሉ ነው የተገደሉት። የከፈሉት የደም ሰማዕነት ወንጌላዊ ልኡክነት የሚያበረታታ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.