2016-02-05 18:42:00

እ.ኤ.አ በየወሩ የመጀመርያ እሁድ በግዕዝ ሥርዓት የሚያርግ መ.ቅዳሴ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓም


ማሳሰቢያ ክቡራትና ክቡራን ኣድማጮቻችን፡ እ.ኤ.አ በየወሩ የመጀመርያ እሁድ በጳጳሳዊ ኢትዮጵያዊ ኮለጅ ካህናት ከቫቲካን ረድዮ ጣቢያ በቀጥታ የሚተላለፍ፤ በግዕዝ ሥርዓት የሚያርገው ጸሎተ መሥዋዕተ ቅዳሴ እሁድ ተነገ ወዲያ እ.አ.አ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓም ከእኩለ ቀን ተኵል እስከ ሰባት ሰዓት ከ50 ደቂቃ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ደግሞ ከ10:30 እስከ 11:50 እንደሚተላለፍ እናሳስባለን።

መሥዋዕተ ቅዳሴው የሚተላለፍበት ሞጎዶች ደግሞ በ15,595 ኪሎ ሄርዝ ወይም በ19 ሜትር ባንድ በ17,590ሎሄርዝ ወይም በ17 ሜትር ባንድ በሮማና ኣከባቢው ለምትገኙ ኣድማጮቻችን ደግሞ በ103.8 ሜጋ ሄርዝ dab በተሰኘው ማለት ዲጂታል አውድዮ ብሮድካስቲንግ አር ቫቲካና ዎርልድ፡ በአይ ኦ ሲ ማለትም በአትላንቲክ ኦውሽን ረጅዮን ሳተላይቶች በአንደኛ በሁለተኛ እና በሶስተኛ መስመሮች፤ በሶስት በዳብልዩ ኤል አይ ማለት በወብ ላይቭ በሁለተኛው መስመር በአንድሮይድ ደግሞ በራድዮ ቫቲካና አፕሊከይሽን አር ቪ አፕስ በሁለተኛ መስመር በቀጥታ ይተላልፋል፣ ክቡራትና ክቡራን አድማጮቻችን በኢንተርነት ለመከታተል www.radiovaticana.va በመክፈት በቋንቋዎች ዝርዝር አማርኛ የሚለውን መገናኛ ስትነኩ በቀጥታ ለመከታተል እሚለው መገናኛ ከነካችሁ ዝግጅቱን ለመከታተል ትችላላችሁ እንዲሁም በአንድሮይድ አፕሊከይሽኑን ለመጠቀም የምትፈልኩ በድረገጹ በስተታች በኩል ካሉ አገልግሎቶች መርጣችሁ በአይፎናችሁ ወይንም በአይፖዳችሁ ለመጠቀም ትችላላችሁ፣

እንዲሁም በናይል ሳት 7 ወስት ኤውተልሳት 7ኤይ ወስት በ11.354 ጊጋሄርትዝ ፖላራይዘይሽን ቨርቲካል ስይምቦል ረይት 27.500 ኤፍ ኢ ሲ 5 እስባር 6 ራድዮ ቫቲካና ወይንም ቫቲካን ረድዮ በሚል ስም ስለሚተላለፍ እንድትከታተሉትና ኣብራችሁ እንድትጸልዩ ኣደራ እንላለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.