2016-02-05 15:35:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ውገዳ ለማጥፋት የሚደግፍ ሕንጸት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ የመሠረቱትና ከዛም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው ከተመረጡ በኋላም በሳቸው ውሳኔ መሠረት ጳጳሳዊ መብት በማልበስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጸና ያደረጉት የጳጳሳዊ የአቢያተ ትምህርት ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር አባላት እ.ኤ.አ. የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ተቀብለው፦ ሕንጸት ለሰው ልጅ ስብእና ለማጣጣምና ምሉእና ውሁድ እድገት ማጎናጸፍ የሚል ቅዉም ሓሳብ ላይ ያተኰረ ስልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋዉስታ ስፐራንዛ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ውህደት ስምምነት መጣጣም የሚል ሃሳብ በመደጋገም ሕንጸት ሲታሰብና ስለ ሕንጸት ሲነገር ያንን የሰው ልጅ ምሉእ ስብእና ማስተዋል እንደሚያስፈልግ አሳስበው ሕንጸት ሰው ያለውን ሰብአዊ ክብሩ የሚደግፍ ፍቅር እንዲኖርና ከሌላው ጋር ለመገናኘት የሚያነቃቃ መሆን አለበት ብለው፣ ወጣት ትውልድ የወጣትነት ውህበትና ውበት በሚገባ እንዲያስተውልና አስተውሎም የወጣጥትነት እድሜው ባክኖ እንዳይቀር በሁሉም ዘርፍ በትምህርት በጥናት በስነ ጥበብ በስፖርት በተለያዩ የሕንጸት ዘርፎች አማካኝነት ገዛ እራሱ ከሌላው ጋር እያገናኘ እንዲኖር ሊደገፍ ይገባዋል። ስለዚህ ወጣት ነጣይ ሌላውን የሚያገል ኤኮኖሚ ፖለቲካና ባህል ሰብአዊነት ማእከል በሚያደርግ ባህል እንዲቃወም ምሉእና የተወሃደ ሕንጸት ያሻዋል እንጻሉ ስፐራንዛ ገለጡ።

ይኽ ጳጳሳዊ የአቢያተ ትምህርት ድራዊ ማኅበር ዓላማም በዓለም የሚታየው ውጥረት ሁከት ግጭት ወጣቱ ትውልድ በስነ ጥበብ በግብረአዊ ሙያ በስፖርት በእውቀት ዘርፍ ሁሉ አማካኝነት ሰላም ለመገንባት ማኅበራዊ ምሉእነትና የግኑኝነት ባህል ማነቃቃትና የምንኖርበት ዓለም የሰላም ቤት እንዲሆን በሰላም ባህል ማነጽ የሚል መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.