2016-02-04 10:01:00

ከሕዳር 30. 2014- የካቲት 2.2016 በምንኩስና ሕይወት ለምኖሩ ሁሉ ለዩ የጸሎት አመት..


እንደምታወሰው ቅ.አ. ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከሕዳር 30. 2014- የካቲት 2.2016 በምንኩስና ሕይወት የምኖሮ ሰዎችን ታሳቢ ያደረገ የፀሎት ጊዜ እንድሆን በማሰብ “የቅድስና ሕይወት እንድኖሩ ለተጠሩ ገዳማዊያን ሁሉ ልዩ አመት ሰይመው እንደነበረ ይታወቃል።

ይህ በምንኩስና ሕይወት የምኖሩትን ወንድምና እህቶችን ታሳቢ አድርጎ የቆየው የጸሎት አመት በትላንትናው እላት ማለትም በየካቲት 2.2016 በብዙ ሺ የምቆጠሩ ካህናት፣ደናግላንና የዘረሀ ክህነት ተማሪዋች በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በተመራ ስራተ ቅዳሴ ተጠናቀቀ።

በበዓሉ መዝጊያ ላይ በተደረገው ስራዓተ ቅዳሴ ላይ ተሳትፈው የነበሩ አባ ጆህሪ ለጋዜጠኞች በዓሉን አስመልክቶ እንደገለጽት “ይህ በምንኩስና ሕይወት ለምኖሩ ወንድሞች እና እህቶች ለየት ባለ ሁኔታ ጸሎት እንድደረግ በተሰጠው አመት ውስጥ በመላው አለም በምገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ ሀገረ ስብከቶችና ገዳማት አመቱን በጸሎት መንፈስ ለማሰብና ሰለ ጋዳም ሕይወት ግንዛቤ ለምስጨበጥ ልዩ ልዩ የምንኩስናን ሕየወት አስፈላጊነትን የምገልጽ፣ በቤተ ክርስትያን ወስጥ ያለውን አስተዋጾና የምያጋጥሙትን ተግዳሮቶችን ማህከል ያደረጉ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸው በተለይም ደግሞ ይህ መንፈሳዊ ሕይወት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ በመሆኑ በዝህ ሕይወት የምኖሩ ሁሉ በትህትና፣ በድኽነትና በታዝዞ ለመኖር የገቡትን ቃል በእግዚአብሔር ፀጋ ታግዘው እንድኖሩ ጭምር ግንዛቤን የፈጠረ አመት ሆኖ ተጠናቋል “ ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በበኩላቸው እንዳሳሰቡት “ በምንኩስና ሕይወት የምገኘው ደስታ የምመነጨው መልካም ምሳሌን በሕይወታችን በማሳየት የተቸገሩትንንና በአስቸጋሪ ሁኔት የምኖሩትን ሰዎች ስንረዳና ስንጎበኝ በመሆኑ በተለይም ደግሞ በተለያዩ ማህበራዊ ሁነታዎች ላዘኑትና ለተጎሳቆሉ ሰዎች ሰላምንና ደስታን መፍጠር ስንችል ብቻ ነው” በማለት ገልጸዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ እንደገለጹት “ በገዳም ሕየውት የምኖሩ ሁሉ በጸሎት ሕይወት ታግዘው ለተጠሩበት ዓላማ ታማኝ ሆነው በመኖርና መልካም አርዓያን በማሳየት ወጣቶችን መሳብ ይኖርባቸዋል ብለው በተለይም ደግሞ የገዳም አለቆች በአግባቡ የማስተዳደር ተግባራቸውን በመወጣት በገዳም ለምኖሩ ሁሉ መንፈሳዊ ጥበቃን በማድርገ ሕይወታቸውን ለዝህ አገልግሎት የሰውትን ወንድማችንና እህቶችን በመንከባከብ ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ፊት እንድጉዋዙ ልያበረቷቷቸው ይገባል” በማለት አስተምሮዋቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.