2016-02-03 16:34:00

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከ የካቲት 12 ቀን እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በመክሲኮ ለሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ምክንያት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በተክሳስ የብሮውንሲለ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳኔል ኤ. ፍሎረስና በነው መክሲኮ ለሚገኘው በላስ ኩቸስ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኦስካር ክሩሰስ አማካኝነት እንደሚወከሉ የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ኤ ክሩትዝ ማሳወቃቸው ሲር የዜና አገልግሎት ገለጠ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመክሲኮ የሚያካሂድት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርይዊ ጉብኝት ርእስ ሥር ይፋዊ papafranciscoenmexico.org በሚል አድራሻ ድረ ገጽ መሰራቱ ሲገለጥ፣ ድረ ገጽ በጠቅላላ ቅዱስ አባታችን በአገረ መክሲኮ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዙሪያ የሚያከናውኑት የሚያካሂዱት ግኑኝነቶች የሚያስተላልፉት መልእክቶች የሚያሳርጉት ሥርዓተ ቅዳሴና የሚለግስቱ ስብከት በጠቅላላ ከሐዋርያዊ ዑደት ጋር በተያያዘ መልኩ የሚከናወኑት ሁሉ በማካተት በትክክለኛው ሰዓት በመከታተል በቀጥታ በስዕላዊ መግለጫ ሥር በማስደገፍ የሚዘግብ መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.