2016-02-02 10:13:00

ቤተ ክርስትያን "የድኾች አለኝታ ናት"


እንደ ጎርጎራስዊያን የቀን አቆጣጠር ከጥር 25- ጥር 31.2016 በፍሊፒን “የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው” በምል ከሓዋሪያው ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆላስይስ በ1፣27 በተወሰደ መሪ ቃል እየተካሄደ የነበርው 51ኛው የአለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉብሄ በትናንትናው እለት ተጠናቀቀ።

በዝህ ጉባሄ ላይ ከ71 ሀገራት የተውጣጡ ከአሥር ሺ በላይ ተሳታፊዎችና 8500 ተወካዮች የተገኙ ስሆን 20 ካርዲናሎች፣ በአብዛኛው ከኤዥያና ከሌሎችም አሀጉራት የተውጣቱ 50 ጳጳሳትና የቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ተወካይ በተገኙበት በትላንትንው እለት ተጠናቋል ስል ጋዜጠኛችን ሲን ሎቬት ዘግቡኋል።

በመዝጊያው ሰነ ስረዓት ላይ “የድኾችን እግር ማጠብ፣ ቅዱስ ቁርባንና ክህነት” በምል አርዕስት ላይ ተምርኩዘው የመዝጊያ ንግግር ያደርጉት አባ ሉቺያኖ ፌሎኒ እንዳሳሰቡት “የድሆችን እግር ማጠብ ማለት ልድኾች አገልግሎት መስጠት ብቻ ማለት ሳይሆን ለእነርሱ ያለንን ፍቅርና ክብር መግለጽም ጭምር ነው” ብለው “እግር ማጠብ ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ ስቃዩን ከመጀመሩ በፊት ለሓዋሪያት ያለውን ፍቅር እግር በማጠብ እንደገለጸ ሁሉ እኛም በመንፈስ ድኾች የሆንን ሁላችን ከመንፈሳዊና ሞራላዊ ከሆነ ድኽነት እንድያጥበን ልንፈቅድለት ይገባል” ብለዋል።

ይህንን የፍቅር መግለጫ የሆነውን ትህትናን በመላበስ ጌታ ያስተማረንን አገልግሎት እኛም ድኾችን ከለብ በመነጨ መልኩ በመርዳት ለእነርሱ ያለንን ፍቅር መግለጽ እንዳለብን ቤተ ክርስትያን ታስተምረናለች ብለዋል።

በመቀጠልም “መንግስትና የመንግስት አካላት ሄደው አገልግሎት መስጠት በማይፈልጉበት ቦታ ሁሉ ቀድማ የምትገኘውና ለድኾች አለኝታነቷን የምትገልፀው ቤተ ክርስትያን ናት ካሉ ቡኋል ምዕመናን ተስፋ ሳይቆርጡ ወደፊት እንድጓዙ፣ በእምነት እንዲበረቱ የምትደርግ በድኾች የተመሰረትች የክርስቶስ አካልና የእግዚአብሔርን አንድ ልጅ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ መንፈሳዊ ስጦታ የሆነው ቅዱስ ቁርባን ፀጋንና በረከትን ለሕዝቡ እንድያመጣ በነጻ የምታቀርብ ብቸኛዋ የመንፈስዊ በርከት መፍለቅያ ተቋም ናት” ብለዋል።

በስተመጨረሻም “እኛ በምንሰራበት የፍሊፒንስ ገጠራማ ቦታ የምታየው ድኽነት እጅግ በጣም አስከፊ ነው” ካሉ ቡኋላ በጣም በተጎሳቆለ ሁኔት የምኖሩ ብዙ የምህበረሰብ ክፍሎች መኖራቸውን አመለክተው በተለይም ደግሞ ምንም አዓይነት የህክምና አገልግሎት በሌለበት ሁኔታ የሚኖሩ ሕይወታቸው ለአደጋ የተጋለጠ ብዙ የምሕበረስብ ክሎች መኖራቸውን ጠቁመው፣ ወጣቶች የወደፊት ተስፋቸውን እውን ለማድረግ የምያስችላቸው የትምህርት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ሳያገኙ የምያድጉ በመሆናቸው መጭውን ጊዜያቸውን ጭምር ጨለማ የለበሰ እንዲሆን እና ተስፋ ለምቁረጥ የሚገደዱበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

“በዚህም ሁሉ አስከፊ ሁኔት ውስጥ ግን ቤተ ክርስትያን በተለይም ለድኾች የተቻላትን መንፈሳዊ እና ቁሳዊ እርዳታን በማቅረብ ተስፋቸውን እያለመለመች ትገኛለች” ካሉ ቡኋላ “ተስፋችን የሆነው ጌታችን ኢየሱስን አለምን ለማዳን በመሰረትው ሥጋና ደሙ በእውነት የምገኝበት ቅዱስ ቁርባን የተስፋቸው ሁሉ መሰረት በመሆን በጽናት ወደ ፊት እንድራመዱ መንፈስዊ በረከትን በማፍሰስ የእራሱ የሆነ አስተዋጾ አድርጓል” ስሉ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.