2016-01-30 11:11:00

እግዚአብሔር ለቅሶን ወደ ደስታ ይለውጣል


በዛሬው እለት ማለትም እንደጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 27.2016 ለሳምንታዊ የትምህርተ ክርስቶስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ተሳታፊዎች የእግዚአብሔርን ምህረትን አስመልክቶ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ ገለጹት “የእግዚአብሔር ምህረት በእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ሁል ጊዜ እንደነበረ ጠቅሰው የእስራኤልን ሕዝብ በምህረቱ እየመራና የእርሱ ፀጋ ከእነርሱ ጋር እንደሆነ እድረዱም በማድረግ በሰላምና በእርቅ ወደ ተስፋይቱ ምደር እንዳደረሳቸ ከዮሴፍ እና ከወንድሞቹ ታሪክ መረዳት ይቻላል በለዋል።

በመቀጠልም “ብዙ ከቤተሰብ የራቁና በመኮራረፍ ልይ የምገኙ የማይነጋገሩ እህትና ወንድም ይኖራሉ ብየ ገምታለው” ያሉት ቅዱስ አባታችን ይህ የያዝነው ቅዱሱ የምህረት አመት የሰጠንን እድል በመጠቀም ያለፉትን ቂምና ቁርሾ አስወግደን ሰላምና ፍቅርን ማስፈን ይጠበቅብናል በማለት አሳስበዋል። በኦሪት ዘፀአት 2፣23-25  እንደ ተጠቀሰው “ከብዙ አመት ቡኋላ የግብፅ ንጉሥ ሞተ እስራኤላዊያንም ከባርነት በደረሰባቸው ግፍ ይጮኹ ነበር ከባርነት ቀንበር ለመላቀቅ ያሰሙት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ደረሰ። እግዚአብሔርም የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ ከአብራሃም ከይሳቅ ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አሰበ። እግዚአብሔር እስራኤላዊያንን የመለከት ዘንድ ገደደው” የምለውን በመጥቀስ አስተምሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስ አባታችን ጭቆና፣ ስቃይ፣ ብጥብጥ፣ ጦርነት፣ ባርነትና የሰው ልጆች ለሞት በሚዳረጉበት ወቅት ሁሉ የእግዚአብሔር እጁን አጣጥፎ ልቀመት አይችልም ብለዋል።

ባለፉት አመታትና በተለይም ደግሞ አሁን እኛ በምንገኝበት ዘመን እየታየ ያለው እውነታ የምያሳየው ብዙ አቅመ ደካማ የሆኑት የምህበረሰብ ክፍሎች ጉልበታምና ልበ ደንዳና በሆኑት ጥቂት ሰዎች እየተበደሉ ለስቃይ፣ ለመከራና ልስደት በሚዳረጉበት ወቅት እግዚአብሔር በቸልተኝነት የልጆቹን መከራ አይመልከትም በማለት በአጽኖት ተናግረዋል።

በመቀጠልም “የምህረት አባት የሆነው እግዚአብሔር የተጨነቁትንና የተበደሉትን ድኾች ጩኸት በመስማትና በመከራቸውም ውስጥ ጣልቃ በመግባት፣ ይህንን መከራ እና ስቃይ ወደ ደስታ መለውጥ የምችሉ ልክ በሙሴ በኩል የእስራኤልን ሕዝብ ነጻ እዳወጣና የሕዝቡ መከራ እና ስቃይ በደስታ እንደተለውጠ አሁንም እግዚአብሔር በእኛ ዘመን መልዕክተኞችን በመላክ የምሰቃዩትን ሰዎች እንባ ከአያናቸው ያብሳል ብለዋል።

ሙሴ የተሰጠውን አላፊነት በታማኝነት በመቀበል ፈራኦንን በማሳመን የእስረኤልን ሕዝብ ከባርነት ቀንበር ነጻ እንዳወጣጨው ሁሉና የእስራኤልን ሕዝብ እየመራ ቀይ ባህርን አቋርጠው በማለፍ በበርሃ ውስጥም ጭምር ወደ ነፃነት እንደመራቸው ገልፀው በልጅነቱ ሙሴ በእግዚአብሔር ምህረትና ፀጋ ተጥሎበት ከነበረው ከአባይ ወንዝ እንደተረፈና የእስራኤልን ሕዝብ ለመምራት እንደበቃ ሁሉ፣ ከእግዚአብሄር የተሰጠውን የመምራት ሀላፊነት በአግባቡ በወጣት፣ የእስራኤል ሕዝብ አማላጅ በመሆን ቀይ ባህርን ሕዝቡን ቀይ ባህርን እዲሻገር ባማድረግ የእግዚአብሔር መሀሪ መሆኑን በትግባር ማሳየቱን ገልጸዋል።

እኛም እራሳችን አሁን በያዝነው የምሕረት አመት ልክ እንደ ሙሴ ሰዎችንና እግዚአብሔርን የምያገናኝ ድልድይ በመሆን የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ምህረት ተቋድሽ ሆነው ወደ እርሱ በመቅረብ በሰላም እና በጤና እንዲኖሩ የማድርግ አላፊነት ጠጥሎብናል ብለዋል።

በመጨረሻም “ሁል ጊዜ ለመግደል እና ለማጥፋት፣ ጦርነትን ለማውጅ ከምኳትኑ ሰዎች ዘንድ የእግዚአብሔር በምህረቱ ሕዝቦቹን ለማዳን ሁል ጊዜ ጣልቃ ይገባል ብለው ልክ በበረሃ የእስራኤልን ሕዝቦች በመንከባከብ በፍቅሩም እየመራ ወደ ተስፋይቷ ምድር እንደመራ ሁሉ አሁንም በስቃይ እና በመከራ ላይ የሚገኙትን ሁሉ በፍቅሩ ይጎበኛቸዋል ብለዋል። እኛም ክርስትያኖች ሁላችን በዝህ በያዝነው የምህረት አመት በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታ የምገኙትን ሰዎች እንደ አቅማችን በማገዝ የእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር ሁል ጊዜ ከተጨቆኑትና ከተበደሉ ሰዎች ጋር መሆኑን በማስገንዘብ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንገድ ልንመልስ ያስፈልጋል በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.