2016-01-29 16:36:00

የሞስኮ ፓትሪያርክ፦ የመላ ኦርቶዶሳውያን አቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉዳይ


ከመላ ኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ አበይት የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች በማሳተፍ እ.ኤ.አ. ሰነ ወር 2016 ዓ.ም. ሊካሄድ የተወጠነው ሲኖዶስ ርእስ ዙሪያ በስዊዘርላንድ ካምቢስይ ከተማ በመከረው የቅድመ ሲኖዶስ ጉባኤ የተሳተፉት የመላ ሩሲያና ሞስካ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ወደ ሞስኮ በመልስ ላይ እያሉ ሰኔ ወር የሚካሄደው የመላ ኦርቶዶክሳውያን ኣቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በኢስጣምቡል  ከተማ እንዲካሄድ ከሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የቀረበው ሃሳብ ምንም’ኳ በሙላት ተቀባይነት የተሰጠው ቢሆንም ቅሉ በሲኖዶስ የሚሳተፉትን በሚገባ ለማስተናገድ እንዲቻል የቁስጥንጥያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያላት ሕጋዊነት መብት ጭምር  ግምት በመስጠት በክሬታ እንዲካሄድ እንዲካሄድ ያቀረበቸው ሐሳብ ሙሉ ተቀባይነት ተሰጥቶታል እንዳሉ ጋዜጣዊ ኢንተርፋክስ የተሰየመው የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

ሲኖዶሱ እ.ኤ.አ. ሰነ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ይከፈታል

የመላ ኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በግሪክ ክረታ ደሴት እንዲካሄድ የቁስጥንጥያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያቀረበቸው ሃሳብ ተቀባይነት ያገኘውም ሲኖዶሱ በሚገባ ለማዘጋጀት የሚያበቃ ያላት ሕጋዊነት መብት የተሟላ በመሆኑና እንዲሁም የሲኖዶስ ተካፋይ ልኡካን ሁሉ ለማስተናገድ የሚቻል በመሆኑም ሁሉም ይኸንን እድል ግምት በመስጠት የተስማሙበት ሃሳብ መሆኑ የመላ ሩሲያና ሞስካ ፓትሪያርክ ቃል አቀባይ አለክሳንድር ቮልኮቭ ዳግም በማብራራት ሲኖዶሱም የመላ ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን በዓለ ጰራቅሊጦስ በሚያከብሩበት ሰነ 19 ቀን በይፋ ይጀመራል እንዳሉ ኢንተርፋክስ የዜና አገልግሎት የጠቀሰው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

ይኽ በክረታ የሚካሄደው የመላ ኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ከአንድ ሺሕ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚካሄድ ሲሆን፣ የመላ ኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን የበላይ መፍነሳውያን መሪዎች ሲኖዶስ እንዲካሄድ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. በቁስጥንጥንያ ባካሄዱት ጉባኤ የተስማሙበት ውሳኔ መሆኑም ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ኢንተርፋክስ የሰጠው የዜና ምንጭ ጠቅሶ ያመልክታል።     








All the contents on this site are copyrighted ©.