2016-01-26 09:34:00

“ዘላቅነት ያለውን የእግዚአብሔርን ፍቅር” ለሰው ልጆች ሁሉ ማወጅ ያስፈልጋል።


በፍልፒንስ እየተካሄደ በምገኘው 112ኛ የፍሊፒንስ ጳጳሳት መደበኛ ጉባሄ ላይ ለተገኙት ተሳታፊዎች ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ በላኩት መልዕክት እናዳሳሰቡት “የእግዚአብሔርን ድንቅ ምህረት ለማወጅ የተለያዩ አዳድስ የስብከተ ወንጌል ዘዴዋችን በመጠቀም ከቤተ ክርስትያን የጠፉትን በጎች በመፈልግ ላይ ትኩረታቸውን እንድያደርጉ” ማሳሰባቸውን የፍልፒንስ ጳጳሳት ጉባሄ ጻሓፊ ሶቅራጠስ ቪለጋ አስታውቀዋል።

ዋንኛው የቤተ ክርስትያን ተልዕኮ ልሆን የምገባው “ዘላቅነት ያለውን የእግዚአብሔርን ፍቅር” ለሰው ልጆች ሁሉ ማወጅ መሆን እንዳለበት የገለፁት ቅዱስ አባታችን በተለይም ደግሞ በዝህ በያዝነው ልዩ የምሕረት አመት ኢዩበልዩ የተሰጠንን የምህረት እድል በመጠቀም “የሰው ልጆች ሁሉ ትኩረታቸውን በመሳብና እግዚአብሔር መሓሪ መሆኑን እንድረዱ በማድረግ ወደ እርሱ ቀርበው የአባትነት ፍቅሩን በሕይውታቸው እንድለማመዱ ማገዝ ልሆን የገባል ስሉ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።

በተያያዘ ዜናም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣተር ከጥር 25 እስከ ጥር 31 በፊልፒንስ የምካሄደው 51ኛው የቅዱስ ቁርባን ጉባሄ፣ በኤዥያ አሀጉር ለምደረገው የስብከተ ወንጌል ተልዕኮ ከሌሎች የሓይማኖት ተቋማት ጋር ውይይትን መሰረት ባደረገ መልኩ እንድካሄድ መንገድ የምከፈት መሆኑን የዓለማቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባሄ ዋና ሀላፊ የሆኑት አቡነ ፔትሮ ማሪኒ አስታወቁ።

በዝህ ጉባሄ ላይ ከ71 ሀገራት የተውጣጡ ከአሥር ሺ በላይ ተሳታፊዎችና 8500 ተውካዮች የተገኙ ስሆን 20 ካርዲናሎች፣ በአብዛኛው ከኤዥያና ከሎሎችም አሀጉራት የተውጣቱ 50 ጳጳሳትና የቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ ተወካይ በተገኙበት በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 24.2016 በድመቀት መከፈቱን አቡነ ፔትሮ ማሪኒ አስታውዋል ስል ዘጋቢያችን ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ዘግቡዋል።

በዝህ ጉባሄ ላይ ትኩረት የምሰጠው መሪ ቃል ተስፋ የሚለው ነው ያሉት አቡነ ፔትሮ ማሪኒ ወጣቶች የመጭዉ የቤተ ክርስትያን ተስፋ በመሆናቸው አባላጫውን የውክልና ተሳትፎ ተሰቱዋቸው እንድሳተፉ ተደርጓል ብለዋል።

በማከልም መቶ ሚልዮን ወይም 80% የካቶሊክ እመነት ተከታይ ባለባት ፍልፒንስ ይህንን ጉባሄ ማዘጋጀታችን በዝህ ሀገር የምገኙትን ክርስትያኖች በይበልጥ ክርስቶስን እንድያውቁት እድል የምሰጣቸው ስሆን በተለይም ደግሞ በኤዥያ አሀጉር ለምደረገው የስብከተ ወንጌል ተልዕኮ ከፍተኛ አስተዋፆም የኖረዋል ብለን እናምናለን ብለዋል።

ይህ የቅዱስ ቁርባን ጉባሄ በፍሊፒንስ ሴቡ በተባለች ከተማ እንድከበረ የተፈለገው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1521 የመጀመሪያዎቹ የእስፔን ተወላጅ የሆኑት የወንጌል መልዕከተኞች የወንጌል አስተምሮዋቸውን የጀመሩት በዝህችው ከተማ መሆኑን ለማስታወስ ስሆን በጊዜውም የነበሩት ምዕመናንም እምነቱን ተቀብለው በባህላቸው ውስጥ በማስረፅ እስከ ዛሬ እምነታቸውን ጠብቀው ማኖራቸው ለሌሎችም በኤሽያ አህጉሩ ለምገኙት ሀገሮች ትልቅ ምሳሌ በመሆኗ ጭምር ነው ብለዋል።

በኤሽያ በአሁኑ ወቅት ብዙ ክርስትያኖች በእመነታቸው ምክንያት መከራ እና ስደት ይደርስባቸዋል ለዝህ መፍትሄው ምንድነው ተበልው ለተጥየቁት ጥያቄ ስመልሱ “አለመታደል ሆኖ በኤሽያ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የምትታየው ልክ ከምዕራብ ሀገሮች ጋር ቀጥተኛ የባህል ግንኙነት ያላትና የምራባዊያን እሴት መገለጫ ተደርጋ ስለምትወሰድ በሌሎች በኤሽያ አሀጉር በሚገኙ የምህበረሰብ ክፍልና የእምነት ተቋማት የመገለል አደጋ እያጋጠማት በመሆኑ ይህንን ስጋት ለማስወገድ እመነቱን በባህላችው ውስጥ ማስረጽ ያስፈልጋል ብለው ይህንን የቅዱስ ቁርባን ጉባሄ እድል በመጠቀም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት ጋር በመነጋገር ላይ የተመሰረተ የግጭት አፈታት ዘዴ ተግባራዊ በማድረግ ልዩነታችንን ሰላማዊ በሆነ መልኩ መፍታት ከቻልን ሁላችንም የአንዱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችንን በማስመስከር በሰላም መኖር እንችላለን በለዋል።

በመጨረሻም ከዝህ የቅዱስ ቁርባን ጉባሄ ምን መልካም ፍሬ ልገኝ ይችላል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ስመልሱ “ከሁሉም በፊት ማወቅ የምገባን ነገር ብኖር ይህ እየተከበረ ያለው የቅዱስ ቁርባን ጉባሄ በቤተ ክርስታያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1881 በፈረንሳይ ሀገር በሊሌ ከተማ መከበር የጀመር ስሆን አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ እየተከበረ ያለው የዓለም ትኩረት ወደ ቅዱስ ቁርባን በመሳብ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንን እሴቶች ማስተዋወቅና እምነታችን የተመሰረተው የሰላም ነጉሥ በሆነው በእየሱስ ክርስቶስ ላይ መሆኑንና የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ መሆናቸውን ማሳየት መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.