2016-01-26 11:24:00

በአሁኑ ወቅት 10.2 ሚልዮን ሰዎች በዝህ የድርቅ አደጋ ሰላባ ሆነዋል።


በተላንትናው እለት ከአቶ ኔይል ማርስላንድ በዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የስቸኳይ እርዳታ የበላይ ተጠሪ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የተከስተውን የድርቅ አደጋ አስመልክቶ ከጋዜጠኛችን ለከረበላቸው ትያቄ እንደመለሱት “ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጲያ የተከሰተው የእራብ አደጋ ባለፉት 50 አመታት ከታየው በጣም የከፋ መሆኑን ገልፀው የዝህ ደርቅ አደጋ መንስሄው እንደጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ የተከሰትው የዝናብ እጥረት መሆኑን አመልክዋል።

ምን ያህል ሰዎች በዝህ የድርቅ አደጋ ለችግር ተዳረገዋል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ስመልሱም “እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት በአሁኑ ወቅት 10.2 ሚልዮን ሰዎች በዝህ የድርቅ አደጋ የተጎዱ ስሆን በእኛ ግምት ደግሞ ይህ አሀዝ በመጋቢት ወር ላይ 15 ሚልዮን ይደርሳል ብለን እንጠብቃለን ካሉ ቡኋል ይህ አሀዝ የምያሳየው ደግሞ 15% ኢትዮጲያዊያን የዝህ የእራብ አደጋ ሰለባዎች መሆናቸውን ነው” በልዋል።

ኢትዮጲያ ይህንን የእራብ አደጋ መቋቋም እንድትችል የእርሶ ድርጅት ማለትም የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት በአሁኑ ወቅት ምን ዓይነት እገዛ እያደረገ ነው? ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ስመልሱ “በሀገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ መቋቋም እንድቻል የአምሣ ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር መድበን እየተንቀሳቀስን ነው ብለው ይህም ገንዘብ በአብዛኛው የምውለው ለግብርና ሥራና የአርብቶ አደሩን እንስሣት ከሞት ለመታደግ መሆኑን አመልክተው ከሌሎች የእርዳታ ተቋማት ጋር በመተባበርም በዝህ አደጋ የተጎዱትን አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን አቅማችን በፈቀደ መልኩ እየረዳን እንገኛለን” ብለዋል።

እናንተ በምደርጉት እገዛ ከኢትዮጲያ መንግሥት ተብብር ይደርግላችዋል ወይ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ስመልሱ “አዎን ! የኢትዮጲያ መንግስ ለዝህ ለተከሰተው ድርቅ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የመሪነቱን ሚና እየተጫወተ በመሆኑ በጣም ደስ ብሎኛል ብለው እኛም ከመንግሥት አካላት ጋር በተለይም ከግብርና ምንስቴርና ከምመለከታቸው በመስክ ከምገኙ የግብርና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የበኩላችንን እገዛ እያደረግን ነው” ብለዋል።

የዝህ የድርቅ አደጋ መንሴሄው ኤሊኖ ነው ይባላል እርሶ በዝህ ላይ ምን አስተያየት አሎት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ስመልሱ “አሁን የተከሰተው የድርቅ አደጋ መንስሄው በዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት የተከሰትው የኤሊኖ ክስተት የፈጠርው ነው ብለው በዝህ አደጋ የተጎዱት ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ የምገኙ ሀገራት በተለይም ኢትዮጲያና ሱማሊያ የተከሰተው የዝናብ እጥረትም የራሱን የሆነ አስተዋፆ ለደርቁ አደጋ አበርክቷል” ብለው አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.