2016-01-25 16:23:00

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት መልእክት


እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በሶማሊያ ክልል ሰላም እንዲረጋገጥ በጸጥታና ደህንነት ጥበቃ ሥር የሚግኘው በአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ላይ አልሽባብ እስላማዊ አክራሪያው ኃይል በኤል አደ የሰላም አስከባሪው ኃይል ጦር ሠፈር ውስጥ በፈጸመው ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት ሁሉ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእኽት በማስታወስ፦

የሰማዕታቱ ደም አገር የሚያዋህድ በሶማሊያ ሰላም የሚያሰጥ ይሁን

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት አሸባሪው ኃይል በጣለው የአጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ ለሞት አደጋ የተጋለጡት በአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ሥር ተመድበው አገልግሎት የሚሰጡትን ሁሉንም በማሰብ በተለይ ደግሞ የሞት አደጋ የደረሰባቸው የኬንያ የመከላከያ ኃይል አባላት በማሰብ ለሟች ቤተሰብ ከእግዚአብሔር መጽናናቱን ተመኝተው፣ በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው በማረጋገጥ፣ የኬንያ ልጆቾ የከፈሉት መስዋዕትነት ለአገረ ሶማሊያና ሕዝብ ትብብርና ፍቅር የሚመሰክር ነው። የፈሰሰው ደም በኬንያ አገራዊ አንድነት የሚያጠናክር በሶማሊያ ሰላም ተሳክቶ አገራዊ ጥምረት እንዲረጋገጥና አገሪቱ ወደ ሰላም ጎዳና የተያያዘችው ጉዞ ግቡን እንዲመታ የሚደግፍ ይሁን ብለው የኬንያ ሕዝብ ለሟቾች ቤተሰብ ቅርብ እንዲሆን አደራ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በዚያ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጣለው ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ብዛት በይፋ አለ መገለጡ ፊደስ የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ ከተሰጠው ጊዚያዊ መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው የሞት አደጋ ያጋጠማቸው የኬንያ የመከላከያ ኃይል አባላት ሰላሳ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የኬንያ የዜና አውታሮች እንደሚሉትም በሞት ወደ ሞት ሊደርስ እንደሚችል ነው። አንዳንዱ የኬንያ የመከላከያ ኃይል አባላት የሚገኙባቸው የሰላም አስከባሪው ኃይል አባላት በአልሽባብ አሸባሪያን ኃይል እጅ መግባታቸውና የኬንያ ልዩ የመከላከያ ኃይል አባላትም በአል ሺባብ እጅ ገብተዋል የሚባሉትን ነጻ ለማስለቀቅ ልዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያከናወኑ መሆናቸው ይናገራሉ ሲል ፊደስ የዜና አገልግሎት የኬንያ የዜና ምንጮች ጠቅሶ ይናገራል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.