2016-01-22 16:39:00

የሕጽበተ እግር ሊጡርጊያ ኅዳሴ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሕማማት ሳምንት ጌታችን ኢየሱስ የደቀ መዛሙርት እግር በማጠብ የሚኖረው መንፈሳዊነት ላይ ያነጣጠረ በተለይ ደግሞ በላቲን ሥርዓት የሚከበረው ሕጽበተ እግር እስካሁን ድረስ እንደ ሥነ ሥርዓቱ መሠረት ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ለሕጽበተ እግር የሚያቀርቡዋቸው ወንዶች ብቻ እንደነበሩ በመጥቀስ፣ ካሁን በኋላ ለሕጽበተ እግር የሚመረጡት ወይንም የሚጠሩት ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶች ጭምር እንዲመረጡ የሚል ሃሳብ በማካተት የሕጽበተ እግር ሥነ ሥርዓቱን እንዲታደስ ማድረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢሳበላ ፒሮ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን የወሰኑትን ሕዳሴ ቲዮሎጊያዊ ስነ ቤተ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረተ ያደረገ ሕጽበተ እግር ትርጉሙ በጥልቀት የሚያብራራ ሲሆን ይኸንን ሓሳብ ሰንደው የቅዱሳት ምሥጢራትና ሥርዓተ አምልኮ ለሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ ማስትሰላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገልጠዋል።

የኢየሱስ ፍቅር አለ ማዋሰንና አለ ምንም ድንበር መኖር

ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ባዘጋጁለት ሰገነት ውስጥ ዓለም ለማዳንና ፍቅሩም አለ ማዋሰን ለሁሉም ለመስጠት ገዛ እራሱን ሥጦታ ያደርጋል በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ በማነጣጠር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጌታችን ኢየሱስ በሕማማት ሳምንት ዕለተ ሓሙስ በላቲን ሥርዓት የሚከበረው ሕጽበተ እግር ላይ ያተኮረው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት እንዲታደስ ወስነው ለብፁዕ ካርዲናል ሳራህ ባስተላለፉት መልእክት በጥልቀት የኅዳሴው ትርጉም እንዳብራሩት ብፁዕ ካርዲናል ሳራህ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ ከተሰየመው የቅዱስ መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁ ልእክት ጋዜጣኛ ፒሮ ይጠቁማሉ።

ሴቶች ጭምር

ቅዱስ አባታችን ከጥልቅ ጥናትና በጸሎት መሠረት የወሰኑት ኅዳሴ በማስመልከት፣ ካሁን በኋላ ይላሉ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት በሚሠሩት ሕጽበተ እግር ወንዶች ብቻ ሳይሆን ሴቶች ጭምር የሚያሳትፍ እንዲሆን በማሳሰብ፣ ሁሉንም የሚያቅፍ ሥርዓት ይሁን። ስለዚህ ሴቶች ባለ ትዳሮች ደናግሎች አረጋውያን ህሙማን የውፉይ ሕይወት አባላት በጠቅላላ ሕዝበ እግዚአብሔር የሚመለከት መሆኑ አለበት፣ የቅዱሳት ምሥጢራትና ሥርዓተ አምልኰ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ይኸንን ኅዳሴ በሁሉም የላቲን ሥርዓት በሚከተሉት ሰበካዎች ባስተላለፈው ሰነድ እንዳሳሰበም ፒሮ ገልጠዋል።

ለሕጽበተ እግር ለሚመረጡት ሥነ ሥርዓቱ በሚገባ ቀድሞ ማስረዳት

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት ሰነድ ለሕጽበተ እግር የሚመረጡት የሥነ ሥርዓቱ ጥልቅ ትርጉም እንዲረዱ ቀድሞ ማሰናዳትና አስተምህሮ መስጠት፣ ስለዚሁ ጉዳይ በተመለከተም የቅዱሳት ምሥጢራትና ሥርዓተ እምልኰ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አርቱር ሮከ ለሕጽበተ እግር የሚመረጡት የሚሰጠው አስተምህሮ ሥነ ሥርዓቱ የሚሠራው የሚመለከት ይሆናል፣ የደቀ መዝሙር ሕይወት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ትእዛዝ ህያው ተዘክሮ መሆን አለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ኅዳሴም ይኸንን በጥልቀት ያብራራል እንዳሉ ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ኅዳሴው በተመለከተ እ.ኤ.አ. ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ኅትመቱ የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታወቁ።

ኅዳሴው ቅዱስ አባታችን የኖሩት ተግባር ነው

እንደሚታወሰውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡ ወዲህ በሕማማት ሳምንት በዕለተ ሓሙስ ሕጽበተ እግር ሲፈጽሙ በተግባር የመሰከሩት ሕዳሴ መሆኑ ፒሮ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.