2016-01-13 16:34:00

በአዲሲቷ ኩባ የኤውሮጳ ኅብረትና የቤተ ክርስቲያን ሚና


በኩባ ላይ ተደንግጎ የነበረው የኤኮኖሚ ማእቅብ እንዲነሳ ኤውሮጳ አበክራ በተለያዩ የውይይት መድረኮች ስትንቀሳቀስ ቆይታለች ዛሬም ቢሆን ኩባ ለኤውሮጳ ኅብረት የታደለች ለውይይት ተካፋይ አገር መሆንዋ የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ጃኒ ፒተላ በኩባ ይፋዊ ጉብኝት አካሂደው ሮማ እንደገቡ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በአዲሲቷ ኩባ የኤውሮጳ ኅብረትና እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ሚና አቢይ መሆኑና የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ለአገራቸው የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ በኩባ ላይ የተደነገገው ረዥም አመታት ያስቆጠረው የኤኮኖሚ ማእቅብ እንዲነሳ ያቀረቡት ታሪካዊ ጥያቄ በእውነቱ ኩባ ወደ ኃዳሴ እንድትል እያነቃቃት መሆኑ የሚመሰክር ነው ብለዋል።

በኅብረት ኤውሮጳና በኵባ መካከል የኤኮኖሚ የባህል የፖሊቲካ ብሎም የሰብአዊ መብትና ክብር ጉዳይ የሚመለከቱ ስምምነቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ግኑኝነቶች እየተከናወኑ ናቸው፣ በኤኮኖሚው መስክ የተለያዩ የኤውሮጳ የኤኮኖሚ ባለ ሃብቶች ኢንዳስትሪዎች በዚያች አገርች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ብዙ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው። በኤውሮጳ በኩል ያለው ሁኔታ ይኸንን ይመስላል ብለው ሆኖም ኵባ ይኸንን የኤውሮጳው የኤኮኖሚ መርሃ ግብር በአገሪቱ በሕግ አማካኝነት ዋስትና ማሰጠት ይኖርባታል። የኤኮኖሚው ማእቀብ ተነስቶ ይኸው ኩባ ለጎብኝ መስህብነቷ እጅግ አድጎ የጎብኝ ቁጥር በአምስት ሚሊዮን ከፍ ብሏል፣ የጎብኝ መስህብ ኤኮኖሚ ያለው መዋቅራዊ ቅርጽ እዳሴ ያሻዋል፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች ግንባታ የባንክ ቤቶች አሰራር ወቅታዊነት እንዲንረው ማድረግ የብድር ካርድ ለመጠቀም የሚቻልባት አገር መሆን ይጠበቅባታል፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ ብዙ ህዳሴ የሚያስፈልጋት አገር መሆንዋ ግልጽ ነው።

ኩባ በኤውሮጳ ላይ ያላት እማኔ በማኅበራዊ በፖለቲካው በኤኮኖሚው መስክ ኤውሮጳ እንደ አብነት የሚመለከት ነው። ይኸንን ጉዳይም በቅርብ በኩባ ባካሄዱት ጉብኝት ለማረጋገጥ መቻላቸው ገልጠው፣ በዚህ አጋጣሚም የቤተ ክርስቲያን ሚና በአዲሲቷ ኩባ ያለው ሚና ምን እንደሚመስል ከሃቫና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦርተጋ ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት ብፁዕ ካርዲናል ኦርተጋ ለኵባ ኅዳሴ ቤተ ክርስቲያን የተጫወተቸውና እየተጫወተችው ያለው ሚና ሰፊና ጥልቅ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በኩባ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት በሰጡት ምዕዳን ባስደመጡት ንግግርና ስብከቶች ኩባ በፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ዴሞክራሲያዊ ኅዳሴ ለመሸኘት የሚደረገው ጥረትና የውጭ ድጋፍ አለ ምንም ተጽእኖ አገርንና ሕዝብ በማይጎዳ ሂደት አማካኝነት መከወን አለበት በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ በኩባ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሚና የሚገልጥ ነው እንዳሉዋቸው አስታውሰው፣ በእውነቱ የኵባ ኤኮኖሚ ጥልቅ ኅዳሴ ያሻዋል፣ ለዚያ ሁሉ ነገር ከመንግሥት በነጻ ማግኘት የለመደ ነጻነት ያልነበረው ሕዝብ ወደ አዲስ የኤኮኖሚ ስልት ማሸጋገር የጡረታ አበል መብት የመሳሰሉት ጉዳዮች ማስጠበቅ ያካተተ የኤኮኖሚ እቅድ እጅግ አስፋልጊ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.