2015-12-28 16:07:00

ብፁዕ ካርዲናል አናየካን፦ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች የቦኮ ሃራም ጥቃት ሰለባ ናቸው


በናይጀሪያ የሚገኘው የምስልምና ሃይማኖት አክራሪው ታጣቂው ኃይል በአገሪቱ የሚሰነዝረው ጸር ክርስቲያን ጥቃት ከቀን ወደ ከፍ እያደረገ፣ በብዙ ሺሕ የሚገመቱት የአገሪቱ ክርስቲያን ዜጎች ለሞትና ለከፋ የመቁሰል አደጋ ብሎም አለ ቤትን ንብረት ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ እያጋለጠ መሆኑ ጉዳዩ ቀን በቀን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የሚነገር ዜና ነው። ስለዚሁ ጉዳይ በማስመልከትና በዓለ ልደት በናይጀሪያ እንዴት ባለ ሁኔታ መከበሩ በቅርቡ የተገባው የምኅረት ዓመት ምክንያት  በአቡጃን በሚግኘው ካቴድራል ቅዱስ በር የከፈቱት የአቡጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆን አናየካን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በበዓለ ልደት ምክንያት የአገሪቱ የጸጥታ ኃይል አባላት የማኅበረ ክርስቲያን ደህንነትና ጸጥታ ለማስጠበቅ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ዙሪያ ተሰማራተው መታየታቸው ገልጠው፣ በናይጀሪያ ጸረ ክርስቲያን ርእዮተ ዓለም አያስፋፋ ያለው ታጣቂው አክራሪው ኃይል የሚሰነዝረው ጥቃትና የሚያረማምደው ጸረ ሰብአዊ ተግባር በትክክል ማኅበረ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ ነው፣ ሆኖም እነርሱ ለሚያረማምዱት ጸረ ሰብአዊ ተግባር አልቀበልም ለሚል የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጋ ጭምር አደጋ ነው። ስለዚህ አሸባሪያኑ የማኅበረ ክርስቲያንና የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎች ጠላት ናቸው ብለዋል።

በናይጀሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ምንም’ኳ የጸጥታ ኃይልና የመከላከያ ኃይል ስምሪትና ቁጥጥር ጠበቅ ያለ ቢመስልም፣ በክልሉ ያለው የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ እምብዛም ዋስትና ያለው ነው ብሎ ለመናርገር ያዳግታል፣ የቦኮ ሃራም ታጣቂ ኃይል አባላት በጥርናፌ ጥቃት የሚሰነዝሩ ሳይሆን በተለያዩ ክልሎች ተፈናጥረው የሽበራ ጥቃት የሚጥሉ በመሆናቸም ጭምር በትክክል ለይቶ ግብረ መልስ ለመስጠት ያዳግታ፣ ያም ሆኖ ይኽ የጦር መሣሪያ የሰላም መሣሪያ ሊሆን እንደማይችል ሁሉም ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፣ ስለዚህ መስዋዕትነትም ይጠይቅ የውይይት ባህል ማረማመዱ እጅግ ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ አያይዘው፦ በዓለ ልደት የደስታ የሰላም ቀን ነው። ዘንድሮ የተከበረው በዓለ ልደት በዚህ እየትኖረ ባለው የምኅረት ዓመት የተከናወነ በመሆኑም ይቅር መባባል ምህረት የሰላም መሠረት መሆኑ ያረጋግጣል። በናይጀሪያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ልደት በማክበርም መስክረዋለች፣ ይቅርታ መስጠትና መቀበል ነው መፍትሔው፣ ለወዳጅ ይቅር ማለት ቀላል ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለጠላትህ ይቅርታን መሰጠት እጅግ ከበድ ቢልም፣ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅርብ በልልን ነው ጸልታችን፣ ይኽ ደግሞ ጌታ ያስተማረው ጸሎት ነው። እግብር ላይ ማዋሉ ከባድ ነው፣ ሆኖን ይኸንን ጸሎት እግብር ላይ ለማዋል የጌታ ድጋፍ መማጠን ነው። ጌታ ማረኝ ለማለት የሚያበቃኝ እኔ ለሌላው የምሰጠው ይቅርታና ምህረት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.