2015-12-16 18:44:00

የር.ሊ.ጳ መልእክት ለዓለም አቀፍ የሰላም ቀን (በጎርጎርዮስ አቁጣጠር ጥር አንድ ቀን 2016)


ፊታችን ወርሀ ጥር መባቻ 2016 በጎርጎርዮስ አቁጣጠር አንድ ቀን ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ተከብሮ እና ተስታውሶ እንደሚውል ይታወቃል። የመጀመርያ የሰላም ጠላት በእግዚአብሔር ካለማመን የተነሳ ሰዎች ለሰዎች የሚያሳዩት ቸልተኝነት እንደሆነ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለዚሁ ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ያስተላለፉት መዕክት ያስገነዝባል።

የቅድስነታቸው ዓለም አቀፍ የሰላም መልዕክቱ በመቀጠል ሰላም የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች ለሰላም ገቢራውነት መጠራታቸው ያሳስባል።

የተያዝነው እና ከሁለት ሳምንታት በኃላ ቦታው ለአዲስ ዓመት 2016 አስረክቦ የሚሳናበተው 2015 ዓመተ ምሕረት በጎርጎርዮስ ዘመን አቁጣጠር ግጭት እና ሽብርተኘት የተላበሰ ሳላምን ያደፈረሰ ዓመተ ምሕረት መሆኑ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም መልዕክት ያስገነዝባል።

ይህ ሆኖ ለተስፋ ምክንያት የሚሆኑ ርእሰ ጉዳዮች መከሰታቸው እና በቅርቡ በፈረንሳይ ፓሪስ ላይ የተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና አዎኣንታዊ ውጤቱ ሊጠቅስ እንደሚችል መልእክቱ አውስተዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለዓለም አቀፉ የሰላም ቀን መልዕክት በማያያዝ ጸረ ሰላም የሆነ የቸልተኘት ጥምረት መሆኑ እና ሰዎችን ቸል ማለት እምነትን በእግዚአብሔር አለ መጣል ስስት እና ግብረ ገብነት አልባ እንደሆነ እና ይህ መገታት ያለበት እንደሆነም መልእክቱ ያመለከታል።

በአንድ ሕብረት ሰብ ችግር የሚከስተው እና የሕይወት እሴቶች ከሥነ ምግባር የሚያስርቅ ሙስና ሲገኝ የአከባቢ ብከላ ትብብር እና መተዛዘን ሲጠፋ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለዓለም አቀፍ የሰላም ቀን የጻፉት መልእክት ያስገነዝባል።

ቸልተኝነትን ለመግታት እና ብሎም ለማስፈጣት የሚቻለው የሰዎች ልብ ከልብ ሲቀየር እንደሆነ እና የእግዚአብሔር ጸጋ ስንቀበል እንደሆነ መልእክቱ ይመክራል።

የትብብር ተግባር ለአንድ ሕብረተ ሰብ አስፈላጊ መሆኑ እና የሰው መብት ተሟጋቾች የግብረ ሰናይ ባለ ሙያዎች ስደተኞችን የሚንከባከቡ ድርጆች መልካም አርአያ መሆናቸው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፊታችን ዓመት ከ15 ቀናት በኃላ ለተያዝነው ዓመት 2015 የሚተካ ለ2016 ዓመተ ምሕረት እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር ወርሀ ጥር አንድ ቀን ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ያሚያስታላልፉት የሰላም መልዕት አስገንዝበዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለሰላም ቀን ያስተላለፉት መልክት በማያያዝ ለዓለም መንግስታት ሁሉ ባስተላለፉት መልእክት በቅርቡ በቤተ ክርስትያን የታወጀው የምህረት ዓመት ተተንተርሰው የድሃ ሀገሮች ዕዳ እንዲሰረዘ እና የሞት ቅጣትም እንዲገታ በመልእታቸው በኩል ተማጽነዋል።

የተያዝነው ዓመትን የሚተካ 2016 ዓመተ ሰላም ፍትሕ እና ልማት እንዲሆን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የሰላም መልእክት ያለውን ከፍተኛ ምኞት አስተጋብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.