2015-12-14 19:03:00

በንስሐ መቀየር ማለት ለፍትሕ እና ለመመተባበር መቆም ማለት ነው፤ ር.ሊ.ጳ


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር እሁድ እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከሚገኝ ህዝበ እግዚአብሔር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት እንደሚደግሙ ይታወሳል። ትናንትናም በቅዱስ ጰጥሮስ ከተገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ጋ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።

ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኃላ ቅድስነታቸው በምህረተ እግዚአብሔር ዓመት መቀየር እንደምያስፈልግ እና መቀየር ማለት ለፍትሕ እና ለመመተባበር መቆም ማለትም እንደሆነ ጠቁመው በፈረንሳይ ፓሪስ ላይ የተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የተረሰውን ስምምንት ገቢራዊ እንዲሆን ተማጽነዋል።

የፓሪሱ ስምምነት ድሆች ማእከል ያደረገ እና የሚረዳቸው እንዲሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል ቅድስነታቸው።

የፓሪስ የአየር ለውጥ ጉባኤ ስምምስነት ላይ ባይደርስ ኖሮ ሌላ ምንም አማራጭ እንዳልነበረ እና የዓለም ቁልፍ ችግር መሆኑ እና ጉባኤው ያሳየው ትብብር የሚደነቅ መሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን መግለጣቸው ተመልክተዋል።

የፓሪሱ ጉባኤ የሙቀት መጠን ከ2.0 ዲግሪ ሴልሽየስ ወይም 3.6 ፋራናይት በታች ለማቆየት ተስማምቶ ስምምነቱ እንደተፈረመ እየተነገረ እንደሆነ የሚታወስ ነው። 

የፓሪሱ ጉባኤ ዓለም አቅፉ ማሕበረ ሰብ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ቁርጠኝነት ያሳየበት የተስፋ ምልክት እና ታሪካዊ እንደሆነ ታዛቢዎች አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። 

ስምምነቱ በ195 ሀገራት እንደተፈረመ ከፓሪስ የተሰራጨ ዜና ያመለክታል።

የእሁዱ ቃለ እግዚአብሔር ጠቅሰው ቅዱስ ዮሐስን መጥምቅ መቀየር እና መርዳት እና መተባበር ያሻል ያለውን አሁንም ህያው መሆኑ አሳስበዋል።

መቀየር መለወጥ ማለት የፍትሕን መንገድ መከተል ክርስትያናዊ ሕይወት መኖር ማለት እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ቅድስነታቸው ክወልደ እግዚአብሔር ምሕረት የምንጠይቅበት ግዜ እንደሆነ ምእመናን እንዳይዘነጉ አሳስበዋል።

ቅድስነታቸው ነገ በምስራቅ አፍሪቃ በኬንያ ናይሮቢ ላይ የሚጀመረው ሀገራት አቀፍ የንግድ ድርጅት ጉባኤ አስታውሰው ሀገራት አቀፍ የንግድ ድርጅቱ ድሆችን ትኩረት የሰጠ የሚረዳ እንዲሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.