2015-12-04 16:14:00

ሁላችን ወንድማማቾች ነን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሕዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባንጕይ በሚገኘው ቅዱስ ሳቨሪዮ ቁምስና ባለው የስደተኞችና ተፈናቃዮች መጠለያ ሰፈር ጎብኝተው እዛው ከተፈናቃዮችና ከስደተኞች ጋር ተገናኝተው ሁሉም ሰላም በመገንባቱ ሂደት ተገቢ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ስለ ሰላም መሥራትና መጸለይ ያስፈልጋል፣ ሰላም አለ ፍቅር፣ አለ ይቅር መባባል አለ ወዳጅነትና መከባበር አለ ምኅረት የማይቻል ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰላም በማረጋገጡ ዓላማ አደራ ይጠመድ፣ ሰላም ከሌለ የሁሉም ተሳትፎ የሚከወን አይሆንም፣ በአገሪቱና በዜጎችዋ መካከል ሰላም እንዲኖር አደራ፣ አለ የጎሳ አለ የባህልና የሃይማኖት የማኅበራዊ ደረጃ ልዩነት ሁሉም በጋራ ስለ ሰላም ይትጋ በሚል ሃሳብ ዙሪያ ንግግር አሰምተው እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪያርት ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ቅዱስ አባታችን በዚህ በመካከለኛይቱ ረፓብሊክ አፍሪቃ ባካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት በአገሪቱ ከሚገኙት የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ መሪና ምእመናን ጋር እንዲሁም በአገሪቱ ከሚገኙት የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና መንፍሳውያን መሪዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን በባንጒይ በሚገኘው መስጊድ በአምስት የምስልምና ሃይማኖት መሪዎች አቀባበል ከተደርገላቸው በኋላ ለምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች አለ ምንም ፍርሃት ወንድማማቾች ነን የሚለውን ቃል ማእከል በማድረግ ባስደመጡት ንግግር፦

ወንድማማቾች በመሆናችን በጋራ ጥላቻን እንቢ እንላለን

የእግዚአብሔር ሰው ነኝ የሚል ሃይማኖት አለኝ እምነት አለኝ የሚል የሰላም ሰው መሆን አለበት፣ የሰላም ሰው አለ መሆን ከሃይማኖትና ከእምነት ጋር የማይጣጣም ተግባር ነው። ከዚያ የእግዚአብሔር ገጽ ከሚያወላግድ ጸያፍ ተግባር ሁላችን እንቆጠበ አደራ ካለ ምንም የግል ጥቅም መሻት የጋራ ጥቅም እናስቀድም፣ ባንድነት የጥላቻን መንፈስ እንቢ እንበል፣ ቂም በቀል አመጽ በተለይ ደግሞ በእግዚአብሔር ሥም ከሚፈጸም አመጽ ገዛ እራሳችን እንቆጥብ። እግዚአብሔር ሰላም ነው ብለዋል።

ሰላም ገንቢዎች የተመሰግኑ ናቸው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለሁሉም ለክርስቲያን ለምስልምናና ለባህላውያን ሃይማኖት ተከታዮች በዚያች አገር በጋራ በሰላም ለመኖር የቻሉ መሆናቸው አስታውሰው፣ በሰላም ጎዳና የሚተጉ ሰላምን የሚገነቡ የተመሰገኑ ናቸው። ለሰላም ገንቢዎች ያላቸው አድናቆትና አክብሮት ገልጠው፣ ልዩነትና ጥላቻ ባላበት ወቅት አለ ምንም ፍርሃት ለማህበራዊ ሰላም የምትተግቡ በመሆናቸሁ ደስ ይበላችሁ በአገራችሁና በአካባቢያችሁ ሰላም የመንገንባት ቅዱስ ተግባር ቀጥሉበት።

ሕዝባዊ ምርጫ የአንድነት ጊዜ ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገሪቱ በቅርቡ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ በማሰብም በዚህ ግጭት በሚታይበት ወቅት ዴሞክራሲ የሰፈነበት ሕዝባዊ ምርጫ የተስፋ ምልክት ነው። ስለዚህ አንድነት የሚያበክር ጊዜ ይሁን ብለው አገራችሁ አለ ምንም የጎሳ የሃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት የሁሉም ዜጎችዋና የልጆቿ ቤት ታደርጉ ዘንድ በርቱ ብለው ያስደመጡት ንግግር አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.